መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በባህርዳር የተካሄደው 9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን ድርጅቱን በሚቀጥሉት 5 አመታት እንዲመሩ መርጧቸዋል። የብአዴኑ ሊቀመንበርና የትምህርት ሚንስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። ኢህአዴግ በዚህ ጉባኤ የአመራር ችግር እንደገጠመው በተለይም አመራሩና አባላቱ ተነሳሽነታቸው መቀነሱን ይፋ አድርጓል። ትግሉን ወደፊት ለማስቀጠለም አባላቱና አመራሩ የተከፈለውን መስዋትነት ልብ ሊሉት እንደሚገባ መክሯል። በአገሪቱ ውስጥ የመልካም ...
Read More »የእስልምና ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ የነበሩት ግለሰብ ብአዴን ኮትኩቶ ያሳደጋቸው ሰው መሆናቸው ታወቀ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ ከተካሄደው ምርጫ በፊት የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ የነበሩት ሀጂ መሁመድ ሲራጅ ሙሀመድ ኑር አባታቸው ዋግ ውስጥ ነባር የብአዴን ታጋይ የነበሩ ሲሆን፣ የአቶ ተፈራ ዋልዋ እና የአቶ አዲሱ ለገሰ የቅርብ ሰው እንደነበሩ ከብአዴን ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ግለሰቡ በአወልያ የተጀመረው ተቃውሞ እንዲኮላሽ ከመንግስት ከፍተኛ ተልእኮ በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩና አሁንም የኢትዮጵያ ...
Read More »ፍርድ ቤት ለእነ ጋዜጠኛ ተመስገን ተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ ሰጠ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ኛ ችሎት ዛሬ ከቀኑ 4 ሰአት ላይ በቀድሞው የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና አሁን የ ልእልና ጋዜጣ ዋና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ ላይ ተሰይሞ መዋሉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የቀረቡት 4 ክሶች ቀደም ሲል ፍትህ ጋዜጣ ላይ በጻፋቸው ጽሁፎች እና በአስተናገዳቸው የአምደኞች ...
Read More »የአንድነት ፓርቲ የምእራብ አርማጭሆ አደራጅ ታሰሩ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር የምእራብ አርማጭሆ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አንጋው ተገኘ ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ጎንደር በመሄድ ላይ እያሉ ታች አርማ ጭሆ ወረዳ ሳንጃ ከተማ ላይ ተይዘው መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። ግለሰቡ የተያዙት ከ4 ቀናት በፊት ሲሆን፣ በአሁኑ ሰአት ፍርድ ቤት ሳይቀረቡ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። አቶ አንጋው ተገኝ የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ...
Read More »ባሻ ጥጋቡ ተገኝ አረፉ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሱዳንና የኢትዮጵያ ድንበር በተካለለበት ወቅት መሬታቸውን ለሱዳን እንዲያስረክቡ ሲጠየቁ አሻፈረኝ ብለው የቆዩት የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ባለሀብት ባሻ ጥጋቡ ተገኝ መጋቢት 10፣ 2005 ዓም አርፈዋል። የባለሀብቱ የቀብር ስነስርአት በላይ አርማጭሆ ካን ተንታ ቀበሌ መጋቢት 13 ቀን 2005 ተፈጽሟል። የአካባቢው ባለሀብቶች መሬታቸውን ለሱዳን መንግስት ሲያስረክቡ ፣ ባሻ ጥጋቡ ግን ” የአገሬን መሬት አሳልፌ አለሰጥም” ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት እስክንድር ነጋ የታሰረው በአሸባሪነቱ እንጅ በጋዜጠኝነቱ አይደለም ሲል ለአውሮፓ ህብረት መልስ ሰጠ
መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አገዛዝ በእስር ላይ የሚገኘውን እውቁን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በተመለከተ ከአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ለቀረበት ጥያቄ በጽሁፍ በሰጠው መልስ ” እስክንድር ነጋ የጋዜጠኛነት ስራውን በመስራቱ ሳይሆን አሸባሪ ድርጅቶችን ሲረዳ በመገኘቱ ነው” የተፈረደበት ብሎአል። እስክንድር ነጋ በህቡእ ከሚንቀሳቀሰው ግንቦት7 ከተባለው ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደነበረው፣ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እየሰረጉ ለሚገቡ አሸባሪዎች ስልጠና ይሰጥ እንደነበርና ...
Read More »በማእከላዊ እስር ቤት የታሰሩ ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ ናቸው
መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ከተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ተይዘው የታሰሩ ሙስሊም የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ፣ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ ባለማወቃቸው በቀለብ እና በልብስ እጦት እየተቸገሩ ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ተማሪዎችና መምህራን ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፣ ብዙዎቹ ቶርች ( አሰቃቂ ድብደባ) ተፈጽሞባቸዋል። በአሁኑ ጊዜ የረባ ምግብ አጥተው በመሰቃየት ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ልብሶቻቸው በላያቸው ...
Read More »ሜድሮክ ወርቅ እና ሌሎችም የሼክ አላሙዲ ድርጅቶች የታክስ ጥያቄ ተነሳባቸው
መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለመንግስት ቅርበት ያለው ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ውስጥ ከህወሀት ኩባንያ ከሆነው ኢፈርት በመቀጠል ሁለተኛ የሆነው የሼክ ሙሀመድ አላሙዲ ንብረት ሚድሮክ ኢትዮጵያ ለመንግስት መክፈል የነበረበትን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ክፍያ አላስገባም። ኩባንያው ከሚያስታድራቸው ሆቴሎች ጋር በተያያዘ 632 ሚሊዮን ብር እዳ እንዳለበት ጋዜጣው ዘግቧል። ሚድሮክ ገንዘቡን በአንድ ወር ውስጥ እንዲያስገባ ትእዛዝ እንደደረሰው የኩባንያውን ...
Read More »የአማራ ክልል ተወላጆች የተባረሩት በህገወጥ መንገድ ስለገቡ ነው በማለት ባለስልጣናት ተናገሩ
መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለዓመታት በቤንሻንጉል ክልል ይኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ፦“በሕገወጥ መንገድ ስለገቡ ወደመጡበት መመለስ አለባቸው” ተብለው ከይዞታቸው መፈናቀላቸውን አዲስ አድማስ ዘገበ። በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ በማጣታቸው የተሻለ ሥራ ለመፈለግ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ በመሄድ ኑራቸውን ሲመሩ የቆዩ በርካታ ሰዎች በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች፤ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ ከቀያቸው ...
Read More »ኢህአዴግ 9ኛ ጉባኤውን በባህርዳር ጀመረ
መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“በመለስ አስተምህሮዎች ጠንካራ ድርጅትና የልማት ሀይሎች ንቅናቄ ለህዳሴያችን በሚል” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤ ዋና አላማ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ እየተዳከመና በውስጥ ሽኩቻ እየታመሰ የመጣውን ኢህአዴግን መልሶ ማጠንከር ነው። ግንባሩ በስልጣን ሽኩቻ የሚታመሱት አባላቱ ድርጅቱ የመጣበትን ጉዞ መለስ ብለው እንዲያስታወሱ የሚያደርግ ተውኔት አዘጋጅቶ አሳይቷል። ኢህአዴግ ደርግን ለመጣል ያሰላፈውን ታሪክ፣ የብሄር ብሄረሰቦችን ...
Read More »