መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዘፈቀደ የሚካሄዱ እስሮችን የሚከታተለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካል የሆነው ፍሪደም ናው የተባለው ተቋም እንደገለጸው ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን አስሮ እስካሁን ማቆየቱ አለማቀፍ ህግን የሚጻረር ነው ። አምስት ገለልተኛ ፓናሊስቶች የጋዜጠኛ እስክንድርን እስር በመመርመር፣ እስሩ ህገወጥ መሆኑን በመግለጽ፣ ጋዜጠኛው በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጋዜጠኛው አያያዝ እና የፍርድ ሂደት አለማቀፍ ...
Read More »አቶ ናትናኤል መኮንን የረሀብ አድማ ጀመሩ
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአቶ አንዱአለም አራጌ መዝገብ በሽብረተኝነት ወንጀል ተከሰው 18 አመት እስራት የተፈረደባቸው አቶ ናትናኤል መኮንን የረሀብ አድማ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። አቶ ናትናኤል አድማውን የጀመሩት ቤተሰቦቻቸውን ለአንድ ወር ያክል እንዳይጠቁ በእስር ቤቱ ሀላፊዎች ማእቀብ ከተጣለባቸው በሁዋላ ነው። በአቶ ናትናኤል ላይ የተጣለው ማእቀብ ፣ ከእስር ቤቱ ሀላፊዎች ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ነው። ባለቤታቸውን ልጆቻቸውን በመያዝ ...
Read More »በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ ተብሎ በመንግስት የተጠራውን ስብሰባ ተቃወሙ
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነዋሪነታቸው ፍራንክፈርት የሆኑ ኢትዮጵያውያን መንግስት በሙዚቃ ድግስ ስም አድርጎ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ ለማሰባሰብ ማቀዱን ከሰሙ በሁዋላ ወደ ስብሰባ አዳራሹ በመግባት ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቶ እንደነበር በስፍራው የተገኙ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ” ከአባይ በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው በደል ይገደብ” በሚል ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ተውቋል።
Read More »33 የፖለቲካ ድርጅቶች ስለመጪው ምርጫ ህገወጥነት ህዝቡን ሊያወያዩ ነው
መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ራሳቸውን ከምርጫው ያገለሉ 33ቱ የአዳማ ፔትሽን ፈራሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በመጪው እሁድ መጋቢት 29 ቀን 2005 ዓም ህዝቡን ለውይይት ጠርተዋል። ከህዝቡ ጋር የሚደረገው ውይይት በአንድነት ፣ በመድረክ፣ በሰማያዊ እና በመኢአድ ፓርቲዎች አዳራሾች ከ ቀኑ 8 ሰአት ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን፣ የስብሰባው አላማም መጪው ምርጫው ህገወጥ መሆኑን ለህዝቡ ለማስረዳት ነው። በሌላ ...
Read More »መንግስት የክልል ነዋሪዎችን በአዲስ አበባ ምርጫ ሊያሳትፍ ነው
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአዲስ አበባና የወረዳ ምርጫዎች የተመዘገበው መራጭ ቁጥር ከተጠበቀው በታች መውረዱ ያሰጋው መንግስት ፣ ከክልል ከተሞች የራሱ ደጋፊ አባላትን በማምጣት በምርጫው እንዲሳተፉ ዛሬ ስልጠና ሲሰጥ ውሎአል። ከክልል የመጡት ሰዎች በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ የስልጠና ጣቢያዎች በመጪው ምርጫ እንዴት ድምጽ እንደሚሰጡ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በነጻነት ትምህርት ቤት ...
Read More »9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ “ተረት ተረት” የሞላበት ነበር ሲሉ የቀድሞው የፓርላማ አባል ተናገሩ
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞው የፓርላማ አባል፣ የመድረክ ስራ አስፈጻሚና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ገብሩ ገብረማርያም ለኢሳት እንደተናገሩት የኢህአዴግ 9ኛው ጉባኤ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ተረት ተረት መሆናቸውን ገልጸዋል። “እኛ ትናንት የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሙስና መዘፈቃቸውን፣ የሚዲያ ጉዳይ መነጠቁ የዲሞክራሲ ግንባታን የሚገድል መሆኑን” ስንነግራቸው ከቆየን በሁዋላ እነሱ ዛሬ መልሰው ይነግሩናል ያሉት አቶ ገብሩ፣ ተተካካን ይሉና ...
Read More »አዲስ ቤተመንግስት ሊገነባ ነው ተባለ
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህአዴግ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል ግቢ ውስጥ አዲስ ቤተመንግሥት ሊገነባ መሆኑን ምንጮችን በመጥቀስ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ገልጿል። የስብሰባ ማዕከል ያለበት ቦታ ለቤተመንግሥቱ ግንባታ የተመረጠው፣ ቦታው ከመሐል ከተማ ወጣ በማለቱ፣ ዙሪያ ገባው ለደህንነት ምቹ ስለሆነ፣ መንግሥት ከምኒሊክ ቤተመንግሥት ወጥቶ የራሱን አዲስ ታሪክ ለመስራት በመፈለጉ ነው ተብሎአል። በስብሰባ ማዕከል ዙሪያ የሚገኙ የድሃ መኖሪያ ...
Read More »የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የገዢው ፓርቲ አባላት እንዲሆኑ እየተጠየቁ ነው
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን በግድ የፓርቲ አባል እያደረገ ያጠመቀው ኢህአዴግ አሁን ደግሞ በአካል ጠና ያሉትን ታዳጊ ወጣት የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን የአባልነት ፎርም እያስሞላ እንደሚገኝ ምንጮች አስታወቁ፡፡ ታዳጊ ወጣቶች በጠርናፊ መምህራን በኩል እየተመለመሉ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በዚህ ሳምንት በመላ አዲስ አበባ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚማሩትን ታዳጊ ወጣቶች በግማሽ ቀን ሥልጠና የመግባቢያ ዝግጅት ...
Read More »የኬንያ ጠ/ፍርድ ቤት ምርጫው ትክክለኛ መሆኑን አረጋገጠ
መጋቢት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ወር በተካሄደው የኬንያ ምርጫ ፣ በስልጣን ላይ ያሉት ጠቅላይ ሚ/ር ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት ያቀረቡትን ክስ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል። ዳኛ ዊሊ ሙቲንጋ ምርጫው ትክክለኛ መሆኑን፣ አሁሩ ኬንያታም ምርጫውን ማሸነፋቸውን ገልጸዋል። ተሸናፊው እጩ ፕሬዚዳንት ሚ/ር ኦዲንጋ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አከብራለሁ ብለዋል። ዳኛው ሁሉም ኬንያውያን ለአገሪቱ ሰላምና ደህንነት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መክረዋል። ...
Read More »የመንግስት ባለስልጣናት እያስፈራሩዋቸው መሆኑን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት ተፈናቃዮች ተናገሩ
መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት አማራ ተወላጅ አርሶደአሮች ከክልሉ ዋና ከተማ እና ከዞኑ የተውጣጡ ባለስልጣናት ዛሬ ሰብስበው ያነጋገሩን ቢሆንም ፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ መልስ ሰጥተውናል በማለት ለኢሳት ተናግረዋል። አርሶአደሮቹ እንደሚሉት ባለስልጣናቱ ከተማውን ለቀው ወደ ወረዳቸው እንዲሄዱ፣ የተቀሙትን ሀብትና ንብረት በተመለከተ ጥያቄ ሲያቀርቡም ” ቀድሞ ማን ሂዱ አላችሁ ...
Read More »