በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ ተብሎ በመንግስት የተጠራውን ስብሰባ ተቃወሙ

መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-ነዋሪነታቸው ፍራንክፈርት የሆኑ ኢትዮጵያውያን መንግስት በሙዚቃ ድግስ ስም አድርጎ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ ለማሰባሰብ ማቀዱን ከሰሙ በሁዋላ ወደ ስብሰባ አዳራሹ በመግባት  ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቶ እንደነበር በስፍራው የተገኙ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ” ከአባይ በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው በደል ይገደብ” በሚል ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ተውቋል።