በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤቶቻችን ሆን ተብሎ በመንግስት ሰዎች እየተቃጠሉብን ነው አሉ

መጋቢት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በትናንትናው እለት ብቻ ሁለት ቦታዎች ላይ በተመሳሳይ ሰአት ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን፣ ድርጊቱ ያበሳጫቸው ወጣቶች ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር መጋጨታቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። የመጀመሪያው የእሳት አደጋ የደረሰው በአባኮራን ሰፈር ፋሲል ሆቴል አጠገብ ከቀኑ 5፡10 ሲሆን፣ ቃጠሎውም እሰከ 7፡30 ድረስ መቆየቱ ታውቋል። አንድ ሰው ጭንቃላቱ አካባቢ ቃጠሎ ሲደርስበት ሌላ አንዲት ወጣት ደግሞ ...

Read More »

ኢህአዴግ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ያሉ ሰራተኞች ድርጅቱን እንዲመርጡ ቃል የሚያስገባ ቅጽ ለአባሎቹ ሰጠ

መጋቢት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚሁ የቃል ኪዳን ቅጽ ላይ ” በከተማዎች የሚካሄደውን የወረዳ፣ የክፍለከተማና የከተማ ምክር ቤት አባላት ምርጫ ነጻ ፣ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና በህዝብ ተአማኒነት ያለው እንዲሆን በማድረግ ድርጅታችን ኢህአዴግ አሸናፊ እን ዲሆን የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ፣ የታላቁ መሪያችንን ጓድ መለስ ዜናዊ ሌጋሲ ለማስቀጠልና ራእዩን ከግብ ለማድረስ የገባሁትን ቃል ተግባራዊ ማድረግ” የሚል ሀረግ ተጽፎ የሚገኝ ሲሆን፣ ” ...

Read More »

በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል ኢትዮጵያውያን ማውገዛቸውን ቀጥለዋል

መጋቢት ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ5 እስከ 10 ሺ የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ አካባቢ ተፈናቅለው ወደ መጡበት የትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉ ኢትዮጵያውያንን ከጫፍ እስከ ጫፍ ማነጋገሩን ቀጥሏል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በመወከል በሩዋንዳ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የፍርድ ሂደት በአቃቢ ህግነት የተሳተፉት    ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በጉራፈርዳ ወረዳ የተፈጸመው አማርኛ ተናጋሪዎችን የማፈናቀል ድርጊት በዘር ማጥራት ወንጀል በማንኛውም ጊዜ ...

Read More »

አቶ ስብሐት ነጋ ኤርትራውያንንና ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ስብሰባ ጠሩ

መጋቢት ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር የሚገኘውና በቀድሞ የህወሃት መስራችና አመራር አባል አቶ ስብሃት ነጋ የሚመራው የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት የፊታችን ቅዳሜ የኢትዮጵያና ኤርትራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ሕዝባዊ ስብሰባ በአዲስአበባ ጠራ፡፡ በትጥቅ ትግሉ ወቅት እና ወደመንግስት ስልጣን ከመጡም በኃላ በመጀመሪያዎቹ 10 ዓመታት ሃይለኛ ፍቅር ውስጥ የነበሩት ሻዕቢያና ...

Read More »

የሳውዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አንድ ባለስልጣን በኢትዮጵያ ጉዳይ የሰጡትን መግለጫ አስተባበለ

መጋቢት ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሳውዲ አረብያ ም/ል የመከላከያ ሚ/ር በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባውን የሀይል ማመንጫ አስመልክቶ  የሰጡት ምገለቻ የሀገሪቱን መንግስት አቋም እንደማይገልፅ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጹን የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ፋና ብሮድካስቲን ዘግቧል። የኢትዮጵያና የሳዑዲ አረቢያ የሁለትዮሽ ግኑኝነት መከባበርንና የጋራ ተጠቃሚነትን እንዲሁም አንዱ በሌላው ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ጣልቃ አለመግባትን መሰረት ያደረገ መሆኑን የገለጠው ድርጅቱ፣ በቅርቡ የሳውዲ ...

Read More »

በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥራት ወንጀል ሊያስጠይቅ እንደሚችል አንድ ታዋቂ ምሁር ገለጹ

መጋቢት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት በሩዋንዳ የተካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአቃቢህግነት በመምራት  የሚታወቁት የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ ሀይለማርያም ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት ከዚህ ቀደም በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ፣ አሁን ደግሞ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው ወንጀል በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ የሚችል ዘር ማጥራት ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል። ምሁሩ እንዳሉት ድርጊቱ የዘር ማጥፋት ...

Read More »

የፍኖተ ሰላም ባለስልጣናት ለተፈናቃዮች መጠለያ አዘጋጅተን ሰጥተናል አሉ

መጋቢት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ ሰፍረው የሚገኙት የአማራ ተወላጆች በቂ መጠለያ፣ በቂ ህክምናና በቂ ምግብ ማግኘታቸውን የዞኑ የምግብ ዋስትና እና የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ገልጸዋል። ው አቶ ያዛቸው በላይ ለኢሳት እንደገለጡት በከተማው የሚገኙት ተፈናቃዮች ለህክምና በሚመች ቦታ የኮብል ስቶን ድንጋይ ማምረቻ በነበረ ግቢው ውስጥ እንዲሰፍሩ ተደርጓል። አቶ ያዛቸው እንዳሉት ...

Read More »

የሙስሊም መሪዎች የፍርድ ቤት ሂደት ብዙ ጥያቄዎችን እንደሚያስነሳ ሂውማን ራይትስወች ገለጠ

መጋቢት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ባወጣው መገለጫ በ29 የሙስሊም መሪዎች ላይ የተጀመረው የፍርድ ሂደት ለ40 ቀናት ከተቋረጠ በሁዋላ ዛሬ የሚጀመር ቢሆንም እስካሁን የነበረው የፍርድ ሂደት ተአማኒ እንዳልነበር ገልጿል። መሪዎቹ በእስር ቤት እያሉ ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ በቂ የሆነ የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ አለመደረጉንና የፍርድ ሂደቱ ከሚዲያ፣ እና ከሌሎች ታዛቢ አካላት ውጭ እንዲካሄድ መደረጉን ጠቅሷል። የድርጅቱ የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ...

Read More »

የመንግስት መ/ቤቶች ሐብትና ንብረት በትክክል አለመታወቁ ለብክነትና ለሌብነት እንዲዳረግ ምክንያት ነው ተባለ

መጋቢት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የፌዴራል መ/ቤቶች ሐብትና ንብረት በትክክል አለመታወቁ ለብክነትና ለሌብነት እንዲዳረግ ምክንያት መሆኑን ከፌዴራል የመንግስት ግዥ አስተዳደር የተገኘ ሰነድ ጠቆመ፡፡ የመንግስት የሐብትና ንብረቱ መጠን በትክክል አለመታወቅና ተመዝግቦ አለመያዙ ለጉዳትና ለብክነት በር ከፍቶ መቆየቱን ሰነዱ ጠቁሞ በመንግስት ንብረት አስተዳደር ያለውን ጉድለት ለመሸፈን ኤጀንሲው ተቋቁሞ ወደስራ ሊገባ መቻሉን ተመልክቷል፡፡ የመንግስት ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር ...

Read More »

በሐይል ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ችግራችን ተባብሶአል ይላሉ

መጋቢት ፳፫ (ሀያ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በፍኖተሰላም እና በባህርዳር ከተማ ያለመጠለያ ተበትነው የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ፣ የክልላቸው ባለስልጣናትም ሆኑ የፌደራል መንግስቱ መፍትሄ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ገለጸዋል። በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሰፍረው የነበሩ ከ3 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ከመሀል ከተማ እንዲወጡ ተደርገው፣  ባከል እየባለች በምትጠራ ገጠራማ ቀበሌ አንድ ጫካ ውስጥ እንዲሰፍሩ መገደዳቸውን በባከል ቀበሌ ...

Read More »