(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 24/2010) በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመር አብዲ ዒሌ የጠየቁት ዋስትና ውድቅ መደረጉ ተገለጸ። ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል። ከአቶ አብዲ ዒሌ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት ሌሎች የቀድሞ የሶማሌ ክልል አመራሮችም ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል። በስም መመሳሰል ታስረው የነበሩት አንድ አመራርም መለቀቃቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አቶ አብዲ ዒሌ ትላንት ...
Read More »አቶ በረከት ስምኦን ተቃውሞ ገጠማቸው
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 23/2010) አቶ በረከት ስምኦን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየሰጧቸው ያሉ አስተያየቶች በማህበራዊ ድረገጾችና በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ ገጠመው። አስተያየት ሰጭዎች እንደሚሉት አቶ በረከት ሕዝቡን ከለውጥ አራማጆች ጋር በማጋጨት የመከፋፈል ስራ እየሰሩ ነው። በቅርቡ ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት አቶ በረከት ስምኦን የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችንና የለውጥ አራማጆችን ማውገዛቸው በሕዝቡ ዘንድ ቁጣን ፈጥሯል። አቶ በረከት በተለይም ከብአዴን አመራር አባላት መካከል ምክትል ጠቅላይ ...
Read More »የመከላከያ ስራዊት ንብረት የሆነ አውሮፕላን ተከስክሶ 18 የሰራዊት አባላት እና ሲቪሎች ህይወታቸው አለፈ
የመከላከያ ስራዊት ንብረት የሆነ አውሮፕላን ተከስክሶ 18 የሰራዊት አባላት እና ሲቪሎች ህይወታቸው አለፈ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ባወጣው መግለጫ የበረራ ቁጥሩ 808 የሆነ የአየር ሃይል አውሮፕላን ለስራ ጉዳይ ከድሬዳዋ ወደ ደብረዘይት እየተጓዘ ለማረፍ 20 ደቂቃዎች ሲቀሩት ኤጂሬ በተባለው ቦታ ላይ ወድቆ የሰዎች ህይወት አልፏል። የአደጋው መንስዔም በባለሙያዎች እየተጣራ መሆኑን አስታውቋል። ...
Read More »ፍርድ ቤት አቶ አብዲ ኢሌና ግብረአበሮቻቸው ያቀረበትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገው
ፍርድ ቤት አቶ አብዲ ኢሌና ግብረአበሮቻቸው ያቀረበትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የቀድመው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሃመድ እና ሌሎች 3 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን የዋስትና መብት ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። 19ኛው የወንጀል ችሎት የተከሳሾችን የዋስትና ጥያቄ ለማየት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጅ የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት ...
Read More »የአዲስ አበባ ህዝብ ብሄር የማይጠቀስበት መታወቂያ ሊያገኝ ነው
የአዲስ አበባ ህዝብ ብሄር የማይጠቀስበት መታወቂያ ሊያገኝ ነው ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) መስተዳድሩ የመታወቂያ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 3/2010ን በማሻሻል፣ ለነዋሪዎች ብሄርን የማይጠቅስ መታወቂያ ለማደል በመዘጋጀት ላይ ነው። ከ27 አመታት በሁዋላ ብሄር ያልተጠቀሰበት መታወቂያ በመያዝ የአዲስ አበባ ህዝብ የመጀመሪያ ይሆናል። መታወቂያ ላይ ብሄርን መጥቀስ ልዩነትን የሚያሰፋ፣ ግለሰቦች በብሄራቸው እየተለዩ ጥቃት እንዲደርስባቸው የሚያደርግና ኢትዮጵያዊነትን አሳንሶ ብሄርን የሚያጎላ ...
Read More »ኦነግና ኦፌኮ ጥምረት ለመመስረት ድርድር ጀመሩ
ኦነግና ኦፌኮ ጥምረት ለመመስረት ድርድር ጀመሩ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ጥምረት እንደሚፈጥሩ የታወቀው፣ አስመራ የሚገኘውን በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራውን የኦነግ አመራር ቡድን ለመቀበል ስለሚደረገው ዝግጅት ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። ኦነግ የትጥቅ ትግሉን በማቆም በሰላማዊ መንገድ ለመታገል እንደወሰነ፣ በቅርቡ ከኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ጋር ባደረገው ውይይት አስታውቆ ...
Read More »አውንግ ሳን ሱ ኪ ከሥልጣናቸው መልቀቅ አለባቸው ተባለ።
አውንግ ሳን ሱ ኪ ከሥልጣናቸው መልቀቅ አለባቸው ተባለ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኃላፊ የሚያንማር መንግስትን ከጀርባ የሚመሩት አውንግ ሳን ሱ ቺ በአስቸኳይ ከስልጣናቸው መልቀቅ አለባቸው አሉ። የቀድሞዋ የነፃነት ታጋይ እና የኖቬል ሽልማት አሸናፊዋ ሳን ሱ ቺ ከስልጣናቸው እንዲወርዱ የተጠየቁት፣በአናሳናዎቹ የሮሂንግያ ሙስሊሞች ላይ ባለፈው ዐመት የሀገሪቱ መከላከያ በፈፀመው ጭፍጨፋ ሳቢያ ነው። የተመዱ ...
Read More »እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሃውልት ሊቆምላቸው ነው
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 23/2010)ለእቴጌ ጣይቱ ብጡል በአዲስ አበባ ሃውልት ሊቆምላቸው ነው። ነገ በአዲስ አበባ አድዋ ድልድይ አካባቢ የሃውልቱ የመሰረት ድንጋይ እንደሚጣልም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። በአስተዳደሩ ቱሪዝምና ባህል ቢሮ የወጣው ደብዳቤ ላይ እንደተመለከተው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማና አርቲስት አለምጸሀይ ወዳጆ የመሰረት ድንጋዩን ያኖራሉ። አዲስ አበባን የቆረቆሩት እቴጌ ጣይቱ ብርሃን ዘ ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት በነበራቸው የተለየ ሚና ...
Read More »አብዲ ዒሌ ፍርድ ቤት ቀረቡ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 23/2010)ባለፈው ሰኞ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ዑመር አብዲ ዒሌ ፍርድ ቤት ቀረቡ። እሳቸውን ጨምሮ አራት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ከፍተኛ ባልስልጣናት ዛሬ ልደታ በሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አቶ አብዲ ዒሌ የጤና ችግር ስለገጠመኝ ጉዳዬን ውጭ ሆኜ ልከታተል ሲሉ የዋስትና መብት መጠየቃቸው ታውቋል። በሌላ በኩል የቀድሞ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ...
Read More »የአቶ በረከት የዝወራ ዘመን አክትሟል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 23/2010)በአቶ በረከት ይዘወር የነበረው የብአዴን የአመራር ዘመን ማክተሙን የአማራ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ገለጹ። ሃላፊው ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ አቶ በረከት የድርጅቱ መስራች በመሆናቸው እናከብራቸዋለን ነገር ግን እሳቸው በሞግዚትነት የሚያሽከረክሩት ድርጅት እንዲሆን ግን አንፈቅድም ብለዋል። አቶ በረከት በስብሰባው ላይ እንዳልገኝ የተደረኩት አመራሮቹን ስለምሞግታቸው ነው ያሉትም ፍጹም የማይመስልና ያኛው ዘመን አክትሞ የሰዎች ሃሳብ በነጻነት የሚስተናገድበት መድረክ መፈጠሩን ሊረዱ ይገባል ...
Read More »