የመከላከያ ስራዊት ንብረት የሆነ አውሮፕላን ተከስክሶ 18 የሰራዊት አባላት እና ሲቪሎች ህይወታቸው አለፈ

የመከላከያ ስራዊት ንብረት የሆነ አውሮፕላን ተከስክሶ 18 የሰራዊት አባላት እና ሲቪሎች ህይወታቸው አለፈ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 24 ቀን 2010 ዓ/ም ) የመከላከያ ሰራዊት የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ባወጣው መግለጫ የበረራ ቁጥሩ 808 የሆነ የአየር ሃይል አውሮፕላን ለስራ ጉዳይ ከድሬዳዋ ወደ ደብረዘይት እየተጓዘ ለማረፍ 20 ደቂቃዎች ሲቀሩት ኤጂሬ በተባለው ቦታ ላይ ወድቆ የሰዎች ህይወት አልፏል። የአደጋው መንስዔም በባለሙያዎች እየተጣራ መሆኑን አስታውቋል።
በአደጋው 15 የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና 3 ሲቪሎች ህይወታቸው አልፏል።