ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያዊያን ዲፕሎማቶች ስራቸውን አጠናቀው ወደአገር ውስጥ ሲመለሱ ከቀረጥ ነጻ ዕቃዎቻቸውን ማስገባትን ጨምሮ ከፍተኛ የደመወዝ ክፍያና ጥቅማጥቅም የሚያስገኝ አዋጅ ተረቀቀ፡፡ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ተረቅቆ በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ ሰሞኑን ለፓርላማው የቀረበው የውጪ ግንኙነት አገልግሎት ረቂቅ አዋጅ ክፍል ስድስት ከ37 እስከ 41 ያሉት አንቀጾች የውጭ ግንኙነት አገልግሎት ሰራተኞችን ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅምና ከለላዎችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን የያዙ ...
Read More »በአጋሮ ሁለት የእስልምና ትምህርት መስጫ መድረሳዎች ተዘጉ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው አርብ በከተማዋ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያሰሙትን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ የበቡኖበር ሂላል መስጂድ እና የከፋበር ቶፊቅ መስጂድ መድረሳዎች መዘገታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት ከተቃውሞው በሁዋላ የከተማዋ አስተዳደር የመስጊዱን ኮሚቴዎችን በመሰብሰብ ኢማሞች እንዲባረሩና ሁለቱ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ አድርጓል። መንግስት በሀይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ አልገባም ቢልም ጣልቃ ለመግባቱ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ አይኖርም ሲሉ ...
Read More »አንድነት መድረክ በቶሎ ወደ ውህደት እንዲያመራ ጠየቀ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመድረክ ስር ያሉ ፓርቲዎች በአስቸኳይ ወደ ውህደት እንዲመጡ አንድነት ለፍትህና ለነፃነት ፓርቲ ጠየቀ። የ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክን የሥራ አፈፃፀም ላለፉት አምስት ወራት ሲገመግም እንደቆየ የገለጸው አንድነት ፓርቲ፤ በመድረክ ስር ያሉ ፓርቲዎች በቶሎ ውህደት እንዲፈጥሩ ነው ጥያቄ ያቀረበው። የ አንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ሚያዚያ 19 ቀን 2005 ዓመተምህረት ያደረገውን ስብሰባ ተከትሎ በሰጠው ...
Read More »በኒውዮርክ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽ/ቤት ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራና በሙርሲዎች ላይ የሚደገረውን መፈናቀል በመቃወም እንዲሁም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የቀጠለውን የሰብዓው መብት ረገጣ በማውገዝ በኒውዮርክ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽ/ቤት ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ። በሰብዓው መብት ረገጣ የሚጠየቁ ባለሥልጣናት ስም ዝርዝር የያዘ ደብዳቤ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስገብተዋል። በተያያዘ ዜና በዊኒፔግ ካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግሥት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚያደርሰውን የማፈናቀል ተግባር በፅኑ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች ስርዓቱን ተለይተው ከሃገር በመክዳት ላይ መሆናቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያስረዳል
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ በተለያዩ ሃገራት በስራ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች ስርዓቱን ተለይተው ከሃገር በመክዳት ላይ መሆናቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያስረዳል :: የቅርብ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 5 ያህል ዲፕሎማቶች ስርዓቱን ከድተው አሜሪካ ገብተዋል:: በውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ውስጥ በከፍተኛ የፓለቲካ አማካሪነት እንዲሁም በኢንስፔክሽን ሃላፊነት በመስራት ላይ የነበሩ ሁለት ዲፕሎማቶች ...
Read More »በዋልድባ ገዳም መናኞችን ማፈናቀልና መደብደቡ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከትንሣኤ በኋላ በርካታ የአማራ ተወላጅ የሆኑ መናኞች እንዲወጡ ታዘዋል። በዋልድባ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ አባት ዛሬ ከኢሳት ጋር በተለይ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጡት በገዳሙ ነዋሪ የነበሩ መናኝን የመንግሥት ታጣቂዎች ከማይፀምሪ መጥተው እንደወሰዷቸው የገለፁ ሲሆን በመሀል መንገድ አውርደው ከደበደቡና ከፍተኛ ጉዳት ካደረሱባቸው በኋላ ያላቸውን ገንዘብና ሰነድ እንደዘረፏቸው አረጋግጠዋል። በዋልድባ የሚገኙ መናኞችና አባቶች የቤተክርስቲያንና የሃገር ...
Read More »የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ተፈጥሯዊ ደን በእሳት መያያዙ ተዘገበ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰደድ እሳቱ ከተነሳ 3ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን የደባርቅ አካባቢ ሕዝብ ያደረገው ጥረት እሳቱን ሊያጠፋው አልቻለም። ዛሬ ኢሳት ያናገራቸው የደባርቅ አካባቢ ነዋሪ እንደገለጡልን ብርቅና ድንቅ አዕዋፍ፣ እንስሳትና ዕፅዋትን ያቀፈው የስሜን ተራራ ብሔራዊ ፓርክ ከክልልና ከፌዴራል እሳት አደጋ መከላከያ እገዛ ካልተደረገ ከፍተኛ አደጋ ላይ ይገኛል። በሳንቃ በር አካባቢ በሚገኘው የፓርኩ ክፍል የተነሳው እሳት በኢትዮጵያ ...
Read More »በጋምቤላ ክልል የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላትን ጨምሮ በ23 ሰዎች ግድያ የተከሰሱ ሞት ተፈረደባቸው
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛ ዐቃቤ ሕግ በ23 ሰዎች ግድያ የከሰሳቸው ዘጠኝ ሰዎች ሲሆኑ ሶስቱ በተገኙበት ስድስቱ ላይ ደግሞ ባልተገኙበት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል:: በሌሎቹ ላይ ደግሞ ከ21 እስከ 9 ዓመት የሚደርስ እስር ወስኖባቸዋል። የዐቃቤ ሕግ የክስ ማመልከቻ እንደሚያብራራው ኡመድ ኡከት የተባለው ፍርደኛ ከግብረ አበሮቹ ጋር በአኙዋክ ዞን አበቦ ወረዳ ድቦንግ ቀበሌ ...
Read More »የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አባል ድርጅቶች በአስቸኳይ እንዲዋሃዱ ተጠየቀ
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት አምስት ወራቶች የመድረክን የሥራ አፈፃፀም ሁኔታ በቅርብ ሲገመግም የነበረው የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ቅዳሜ ሚያዝያ 19 ቀን 2005 ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የአራት ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው መድረክ እንዲዋሃድ ብሏል ሲል ፍኖተ ነፃነት ዘግቧል። ድርጅቱ ላለፉት አራት ዓመታት አሳሳቢ በሆኑና በበርካታ ችግሮች ተተብትቦ የቆየ ቢሆንም ሀገራችን ወደ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማሸጋገር በተደረገው ትግል ውስጥ ...
Read More »የቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለባቡር መስመር ሥራ በሚል (የፊታችን) ሐሙስ ከቦታው ሊነሳ መሆኑ ተገለፀ።
ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሕወሓት ንብረት የሆነው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደዘገበው በ1930ዎቹ ለቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያነት የተሰራውና(አራዳ) ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ የሚገኘው ሐውልት በዚህ ሳምንት ተነስቶ ወደ ጊዜያዊ መቆያ ቦታ ይዛወራል። በአዲስ አበባ በስሜን-ደቡብ አቅጣጫ ለሚሰራው የ650 ሜትር የመሬት ውስጥ የባቡር መተላለፊያ ግንባታ ምክንያት ሐውልቱ በጊዜያዊነት መነሳት አስፈልጎናል ያለው ዋልታ ሐውልቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ቅጥር ግቢ ...
Read More »