በአጋሮ ሁለት የእስልምና ትምህርት መስጫ መድረሳዎች ተዘጉ

ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፈው አርብ በከተማዋ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያሰሙትን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ የበቡኖበር ሂላል መስጂድ እና የከፋበር ቶፊቅ መስጂድ መድረሳዎች መዘገታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት ከተቃውሞው በሁዋላ የከተማዋ አስተዳደር የመስጊዱን ኮሚቴዎችን በመሰብሰብ ኢማሞች እንዲባረሩና ሁለቱ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ አድርጓል። መንግስት በሀይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ አልገባም ቢልም ጣልቃ ለመግባቱ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ አይኖርም ሲሉ ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች ገልጸዋል።

መንግስት በሙስሊሙ ላይ የከፈተውን ዘመቻ አጠናክሮ መቀጠሉን በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።