የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች ስርዓቱን ተለይተው ከሃገር በመክዳት ላይ መሆናቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያስረዳል

ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ በተለያዩ ሃገራት በስራ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች ስርዓቱን ተለይተው ከሃገር በመክዳት ላይ መሆናቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያስረዳል ::

የቅርብ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 5 ያህል ዲፕሎማቶች ስርዓቱን ከድተው አሜሪካ ገብተዋል::

በውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ውስጥ በከፍተኛ የፓለቲካ አማካሪነት እንዲሁም በኢንስፔክሽን ሃላፊነት በመስራት ላይ የነበሩ ሁለት ዲፕሎማቶች በቅርቡ ከሃገር ወጥተው ስርዓቱን ከድተው አሜሪካ መግባታቸው የተረጋገጠ ሲሆን በዱባይ የኢትዮጵያ ቆንስላን በማገልገል ላይ የነበሩ ዲፕሎማትም ባለፈው ወር ከስራ ገበታቸው በመጥፋት አሜሪካ መግባታቸው ተረጋግጧል::

ኢሳት ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ እንዲሁም ዲፕሎማቶቹን በአካል አግኝቶ ማነጋገር ጥረት እያደረገ ሲሆን እንደተሳካልን ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን::