በኬንያ ምርጫ ኬንያታ በጠባብ ልዩነት እየመሩ ነው

የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት እስካሁን ባለው ቆጠራ የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዚዳንት ልጅ የሆኑት ኡሁሩ ኬንያታ በጠባብ ድምጽ እየመሩ ሲሆን፣ ምናልባትም በእርሳቸውና በሌላው ተቀናቃኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መካከል የድጋሜ ምርጫ ሊካሄድ ይችላል። እስካሁን ባለው ቆጠራ ኬንያታ 50 በመቶ የሚሆን ድምጽ ቢያገኙም፣ ቆጠራው በቀጠለ ቁጥር ኦዲንጋ ልዩነቱን እያጠበቡ መምጣታቸው ይነገርላቸዋል። ኬንያ የዘንድሮውን ምርጫ በሰላም ...

Read More »

የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች ከቤንሻንጉል ክልል እንዲወጡ ታዘዙ

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ የታየው የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮችን የማፈናቀሉ እንቅስቃሴ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ዞን በቡለን ወረዳ በመደገሙ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ አርሶ አደሮች ክልሉን እየለቀቁ እየወጡ ነው። የአይን እማኞች ለኢሳት እንደገለጡት በአሁኑ ሰአት ልጆቻቸውን ይዘው ፣ የቤት እንስሶቻቸውን እየነዱ መንገድ ወደ መራቸው በመጓዝ ላይ የሚገኙት የአማራ ተወላጆች ከ5 ሺ በላይ ናቸው። ...

Read More »

በኢምግሬሽን አዲስ ፓስፓርት ለማውጣት እስከ አምስት ሺ ብር ጉቦ እየተጠየቀ ነው

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-አገሪቱን እየለቀቀ የሚሰደደው ህዝብ ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ  ህዝቡን ማስተናገድ ያልቻሉት የኢምግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ መ/ቤት አንዳንድ ሰራተኞች አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት ወይም ለማሳደስ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዊን ፈጣን አገልግሎት እንሰጣለን በማለት በነፍስ ወከፍ እስከ ብር 5ሺ ብር ጉቦ እየጠየቁ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ መ/ቤቱ ከጊዜ ወደ ግዜ አገልግሎት አሰጣጡ እያሽቆለቆለ ከመምጣቱ ...

Read More »

የፍራፍሬ ዋጋ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-የኢሳት የአዲስ አበባ ወኪል እንደገለጠው ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳየው ብርቱካን በአሁኑ ጊዜ በኪሎ እስከ 30 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፣  አፕል ደግሞ በኪሎ እሰከ 80 ብር እየተሸጠ ነው። የብርቱካን ዋጋ መጨመር ምክንያቱ በውል ባይታወቅም፣ ብርቱካን በሚያመርቱ ቆላማ አካባቢዎች የሚታየው የዝናብ እጥረት ዋነኛው ምክንያት ሳይሆን አይቀርም። በገበያ ላይ የሚቀርቡት ብርቱካኖች የጥራት ...

Read More »

የ ጆሀንስበርግ ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን በውጭ የሚገኘውን ቅዱስ ሲኖዶስ እንደምትደግፍ አስታወቀች

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በደቡብ አፍሪካ በጆሀንስበርግ ከተማ የምትገኘው ጽርሐ አርያም ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን  ለኢሳት በላከችው መግለጫ ”   መንግሥት ራሱ ያወጣውን ሕገ-መንግሥትና ዓለም አቀፉን ሕገ ቤተክርስቲያን በመጣስ በቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊ ሥልጣን ላይ ግልጽ ተጽእኖና ጫና በማድረግ፤ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲካሔድ የቆየው የዕርቀ ሰላም ጥረት ከፍጻሜ እንዲደርስ በማይፈልጉ ጵጵስናን የተከናነቡ ጥቂት ካድሬዎቹ አማካይነት ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ አንድ ...

Read More »

በኬንያ ምርጫው እየተጭበረበረ ነው ሲሉ ራይላ ኦዲንጋ ቅሬታ አቀረቡ

የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በምርጫው ከተሸነፉ ዳግም ምርጫ እንዲደረግ አለያም የጥምር መንግስት እንዲቋቋም እንደሚጠይቁ የኬንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ አስጠነቀቁ። እስካሁን የተደረጉት የድምጽ ቆጠራዎች በምርጫው የጆሞ ኬንያታ ልጅ ኡሁሩ ኬንያታ እየመራ እና የ ኦሬንጅ ዲሞክራቲክ ሙቭመንቱ ራይላ ኦዲንጋ በሁለተኝነት እየተከተሉ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። ይህንኑ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ለመጭበርበሩ እና በድምጽ ቆጠራው ሂደት ስርቆት ...

Read More »

ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አንድ ሆኖ መውጣት ተስኖታል ተባለ

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የውስጥ ሽኩቻ መበራከት የተነሳ ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አንድ ሆኖ መውጣት እንደተሳነው የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው። በህወሀት ውስጥ ሁለት ቡድኖች ድርጅቱን ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ መጀመራቸው ከተዘገባ ከወራት በሁዋላ ችግሩ ከመቃለል ይልቅ እየጨመረ መምጣቱን አንድ የቀድሞ የህወሀት ነባር ታጋይ ለኢሳት ዘጋቢ ገልጸዋል። ነባር ታጋዩ፤ በአቶ ስብሀት ነጋ በኩል ባሉ ሰዎች ወደ ድርጅቱ ...

Read More »

ታክሲ ውስጥ በ 1 ብር ከ 35 ሳንቲም ሳቢያ በተፈጠረ ጭቅጭቅ ረዳቱ በጥይት ተመታ

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ከትናንት በስቲያ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ  ኪዱ ገብረሥላሴ በተባለ  የታክሲ ተሳፋሪና በረዳቱ መካከል በተፈጠረ የ1.35 ብር አለመግባባት ምክንያት ረዳቱ በጥይት ተመታ። እንደ ሪፖርተር ዘገባ ድርጊቱ የተፈጸመው ቦሌ መድኃኔዓለም ከሚገኘው ካልዲስ ካፌ ፊት ለፊት ሲሆን፣ ተጠርጣሪው አቶ ኪዱ ገብረ ሥላሴ ወዲያው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡ ነጋ ንጉሡ የተባለው የታክሲው ረዳትም፤ ሃያት ሆስፒታል ለሕክምና ተወስዷል፡፡ ...

Read More »

ፋሽስት ግራዚያኒን ለመቃወም ለሁለተኛ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተጠራ

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በቅርቡ የኢጣልያ መንግስት ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ያስገነባው ሙዚየምና የመናፈሻ ስፍራን ለመቃወም በድጋሚ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተጠራ። እንደ ሰንደቅ ዘገባ የተቃውሞ ሰልፉን የጠሩት ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ ባለ ራዕይ የወጣቶች ማኅበር እና ሰማያዊ ፓርቲ ናቸው። ቀደም ሲል ሦስት በጎፈቃድ አባላት ያሉበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ...

Read More »

ሁለት የኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድራቸውን አቋርጠው ጠፉ

የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ሀአሬጽ የተባለው የእስራኤል ጋዜጣ እንደዘገበው ሁለቱ አትሌቶች የማራቶን ሩጫቸውን በማቋረጥ ነው ባለፈው አርብ ፣ ማርች 1፣ 2013 የጠፉት። ሜላት መኮንን እና ማህሌት ዘለቀ የተባሉ የ24 እና 25 አመት እድሜ ያላቸው አትሌቶች የጠፉት በደቡብ ቴላቪቭ ሲሆን፤ የ እስራኤል ፖሊስ አትሌቶቹ ሆን ብለው እንደጠፉ ገልጿል። ሁለቱም አትሌቶች  ፓስፖርታቸውን  እና ሌሎች እቃዎቻቸውን ሁሉ በመተው በሩጫ ...

Read More »