የደቡብ ሱዳን ዜጎች የኢትዮጵያ ጦር ከሱዳን እንዲወጣ ጠየቁ

ግንቦት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ደቡብ ሱዳናውያን ጥያቄ እያቀረቡ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጦር ዜጎቻችን በሰሜን ሱዳኖች ሲገደሉ በቂ መከላከል አላደረገም በማለት ነው።

እንደ ፊረንጆች አቆጣጠር  ሜይ 4፣ 2013 አብየ ውስጥ የአካባቢ የጎሳ ገዚ የነበረው ሚስተር ኲኦል ዴንግ ኲኦል በመሲርያ ጎሳ አባላት በኢትዬጲያ ሰላም አስከባሪ ፊት መገደሉ ይታወሳል። በወቅቱ በተደረገው የተኩስ ልውውጥም ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ተገድለዋል።

ግድያው የኢትዬጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ዋና አዛዝ የሆኑት ሜጀር ጄነራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም ባሉበት የተፈጸመ  መሆኑ ችግሩን የበለጠ እንዳወሳሰበው እየተነገረ ሲሆን በድርጊቱም የተበሳጩ የደቡብ ሱዳን ዜጐች የኢትዬጵያ ጦር ድርጊቱ ሲፈጸም ባለመከላከሉ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ እየጠየቁ ይገኛሉ::

በየወሩ  15 ሺ ዶላር ወይም 300 ሺ ብር የሚጠጋ  ደሞዝ የሚከፈላቸው የሰላም አስከባሪው ዋና አዛዥ የህወሀቱ ነባር ታጋይ ሜጀር ጄኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀል የሚቀርብባቸውን ወቀሳ ለማስተባባል አልቻሉም።

 

የድርጊቱን አሳሳቢነት የተረዱት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪ ሙን ተጨማረ ሃይል ወደ አካባቢው እንዲላክ የጸጥታውን ምክር ቤት ጠይቀዋል::

አብየ ያለው ሰላም አስከባሪ ጦር 4 ሺ  ሺህ እንደ ሆነ ሲገለጽ ባን ኪ ሙን ተጨማረይ 1 ሺ 100 ጦር እንዲላክ ጠይቀዋል::

በደቡብ ሱዳን አንዳንድ አካባቢዎችም አለመረጋጋቱ ጨምሯል። የዴቭድ የየ አማጽያን የደቡብ ሱዳን መንግስትን እየወጋ ሲሆን ቦማ የተባለውን አካባቢ መቆጣጠሩም እየተነገረ ነው:: የደቡብ ሱዳን መንግስትም የሰሜን ሱዳንን መንግስት ለጸጥታው መደፍረስ በተጠያቂነት እየከሰሰ ይገኛል::

ከአንድ ወር በፈት የቀድሞ የኢትዮጵያ ኢታማጆር ሹም ጀኔራል ጻድቃን ገብረትንሳይ በዋና ከተማዋ ጁባ የሚገኘው ቤታቸው እንደተዘረፈና ጠባቂያቸውም እንደተገደለ መዘገቡ ይታወሳል። አብዛኞቹ የህወሀት ታጋዮች በአገሪቱ በብዛት በመግባት ወታደራዊ ምክር እየሰጡ ነው።

ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳን በአብየ ጉዳይ ያላችው የይገባኘል ጥያቄ እየከረረ መሆኑን ከስፍራው የሚወጡ ዘገባወች እየገለጹ የገኛሉ::