ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ( ኦብነግ) ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ትናንት ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከልዩ ሚሊሺያ ጋር በመተባበር በወሰደው እርምጃ አቶ ማካሊ ሙስጠፋ ሀሰን፣ አቶ ሻፊ አው ካሊፍ፣ አቶ አብዱላሂ አብዲ፣ አቶ ሻኩል አብዲ፣ አቶ ፋራህ ሙሀመድ፣ አቶ አብዲሀይ ሼክ አህመድኑር እና አቶ አብድራሺ ሻፊቺች የተባሉትን ...
Read More »በጎንደር የሁለት ቀበሌ ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀበሌ 6 እና 7 ወጣቶች ዛሬ ግንቦት14፣ 2005 ዓም ባደረጉት ሰልፍ የመብራት፣ የውሀ፣ የስራ አጥነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አደራጅና የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ሙላት ፍሰሀ ወጣቶቹ ብሶታቸውን ለመሳማት ለሰልፍ መውጣታቸውን ተናግረዋል። በሰልፉ መጨረሻ ላይ አንዳንድ ወጣቶች በፖሊሶች ሲዋከቡ መታየታቸውን በስፍራው የተገኘው ...
Read More »የባለራእይ ወጣቶች ማህበር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ታሰረ
ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ ግንቦት14፣ 2005 ጧት ላይ በደህንነቶች ተይዞ መወሰዱን የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ሀብታሙ አያሌው ለኢሳት ገልጿል። ወጣት ብርሀኑ ሰማያዊ ፓርቲ ከጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መታሰሩን ወጣት ሀብታሙ ገልጿል። ወጣት ሀብታሙ ከሌሎች የማህበሩ አባላት ጋር በመሆን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቢሄዱም፣ እስረኛውን ሊያገኙት እንዳልቻሉ ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ...
Read More »ሰሞኑን በደሴ ከተማ ሩቂያ እየተባለ በሚጠራው አዳራሽ በተደረገው ስብሰባ ህዝቡ ስሜቱን በድፍረት ሲገልጽ ዋለ
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ስብሰባው ከማንኛውም የድምጽና የምስል ቀረጻ ነጻ እንዲሆን ቢደረግም ኢሳት በደሴ ከተማ ከሚኖሩ ወጣቶች ጋር በመተባበር ስብሰባውን ለመቅረጽ ችሎአል። በዚህ ስብሰባ ላይ ከመልካም አስተዳዳር እና ከንግድ ጋር በተያያዘ የከተማዋ ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ትችቶችን እና ምስጋናዎችን አቅርበዋል። አብዛኞቹ ተናገሪዎች በከተማው ፖሊስ ላይ ከፍተኛ ነቀፌታ አሰምተዋል። መንግስቱ ዘገየ የተባሉ የአማራ ክልል ...
Read More »በጣና ሀይቅ ላይ የደረሰው የጀልባ መገልበጥ መንስኤ አልታወቀም
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ፋሲለደስ እየተባለ የሚጠራው ጀልባ ከቁንዝላ ወደ ደልጊ 102 ሰዎችን አሳፋሮ ሲጓዝ በመስጠሙ አምስት ሰዎች መሞታቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያና አንድ የጣና ሀይቅ ትራንሰፖርት ሀላፊ ገልጸው፣ የአደጋው መንሰኤም በመጣራት ላይ ነው ብለዋል። አደጋው የተከሰተው ጀልባው ደልጊ ለመድረስ ከ150 እስከ 170 ሜትር ሲቀረው ነው። የአካባቢው ህዝብ ተረባርቦ አብዛኞቹን ተሳፋሪዎች ለማውጣት እንደቻለ የጣና ...
Read More »ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በቤንሻንጉል ተፈናቃዮች ዙሪያ ተቃዋሚዎችንና ሚዲያዎችን ወቀሱ
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ጋር በተያያዘ ሕገወጥ ድርጊት ፈጽመዋል የተባሉ 35 ተጠርጣሪዎች ከመንግስታዊ ኃላፊነታቸው መባረራቸውን ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም አስታወቁ፡፡ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር የመ/ቤታቸውን የ2005 የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ዛሬ ለፓርላማው ሲያቀርቡ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለ3ሺ 248 ያህል የአማራ ተወላጆች መፈናቀል ምክንያት እንደሆኑ የተደረሰባቸው 35 ተጠርጣሪዎች ከያዙት ኃላፊነታቸው እንዲሰናበቱ ...
Read More »በጣና ሀይቅ ላይ አንድ ጀልባ ሰጥሞ ከ10 ያላነሱ ሰዎች ሞቱ
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጣና ሃይቅ ላይ ከ 100 በላይ መንገደኞችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረ ፋሲለደስ እየተባለ የሚጠራው ጀልባ በማእበል ተመቶ በመስጠሙ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ከ10 ያላነሱ ሰዎች መሞታቸን ለማወቅ ተችሎአል። የአደጋው መንስኤም ከባድ ዝናብን ተከትሎ በተከሰተ ማእበል መሆኑን ነው አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የጠየቁ የድርጅቱ ሰራተ ለኢሳት የገለጹት ። ይሁን እንጀ ኢሳት ትክክለኛውን ምክንያት ...
Read More »በአትዮጵያ የሚታየው የሀኪሞች እጥረት እየጨመረ ነው
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጽያ ሐኪሞችን የማሰልጠኑ ስራ ከታሰበው ግብ አኳያ አፈጻጸሙ ደካማና አሁንም የባለሙያ እጥረት በከፍተኛ ደረጃ እየታየ መሆኑን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘ ሰነድ አመለከተ፡፡ በጤና ዘርፍ ከሰው ኃይል አኳያ ከፍተኛ እጥረት እየታየ ያለው በሐኪሞች፣በአዋላጅ ነርሶች እና በሰመመን ሰጪ ነርሶች ደረጃ ያለው ነው ያለው ሰነዱ ባለፉት ጊዜያት በመደበኛ ፕሮግራም ሐኪሞችን ለማሰልጠን የሚወስደው ጊዜ ረጅም ከመሆኑና ...
Read More »በደሴ ዙሪያ አንድ ህዝብን ያሰቃያል የተባለ ሹም ተገደለ
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት6 ቀን 2005 ዓም ከቀኑ ስድስት ሰአት ላይ ሙሀመድ የሱፍ የተባለ የደሴ ከተማ ቀበሌ 12 ነዋሪ የ ቀበሌያቸውን የመሬት አስተዳደር ሹም አቶ አህመድ እንድሪስን በ2 ጥይቶች በመግደል ማምለጡ ታውቋል። ገዳይ አቶ ሙሀመድ የጦር መሳሪያ ከሌላ ታጣቂ ላይ በመቀማት ነው የቀበሌ ሹሙን ገድለው የተሰወሩት። ሟቹ ባለስልጣን የአካባቢውን አርሶአደሮች መሬት በመቀማት፣ ማዳበሪያ በግድ እንዲወስዱ ...
Read More »በምዕራብ ጎጃም ሜጫ ወረዳ ሰዎች በግፍ እየታሰሩ ነው
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍኖተ ነጻነት እንደዘገበው ሚያዚያ 18 ቀን 2005ዓ.ም. በሜጫ ወረዳ መራዊ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች መካከል አቶ አንሙት እና አቶ መንግስት በቀለ የተባሉ ወጣቶች በሌሊት በታጣቂዎች ታፍነው ተወስደዋል። ግንቦት 3 ቀን 2005ዓ.ም. ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት መኮንን አድማስ በሚባል የፀጥታ ኃላፊ እና ወ/ሮ አሰለፈ ከበደ በሚባሉ የወረዳው ካቢኔ በመራዊ ከተማ ነዋሪ የሆኑትን ወ/ሮ ሙሉ ሲሳይን ...
Read More »