በጎንደር የሁለት ቀበሌ ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የቀበሌ 6 እና  7 ወጣቶች ዛሬ ግንቦት14፣ 2005 ዓም ባደረጉት ሰልፍ የመብራት፣ የውሀ፣ የስራ አጥነት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አደራጅና የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ሙላት ፍሰሀ ወጣቶቹ ብሶታቸውን ለመሳማት ለሰልፍ መውጣታቸውን ተናግረዋል።

በሰልፉ መጨረሻ ላይ አንዳንድ ወጣቶች በፖሊሶች ሲዋከቡ መታየታቸውን በስፍራው የተገኘው ተባባሪ ዘጋቢያችን ገልጿል።