(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 28/2010) በሊቢያ ትሪፖሊ በእስር ቤት የነበሩ ከ400 በላይ እስረኞች ከእስር ቤት ማምለጣቸው ተሰማ። ለእስረኞቹ ያመለጡት በከተማዋ ትሪፖሊ በተቃዋሚ አንጃዋች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መከሰቱን ተከትሎ ነው ብሏል ቢቢሲ በዘገባው። የእስር ቤት ጠባቂዎቹ ለደህንነትቸው በመስጋት ሲሸሱ እስረኞች ደግሞ የእስር ቤቱን በር በመስበር ለመውጣት መገደዳቸው ታውቋል። አኒ ዛራ በተባለው እስር ቤት ውስጥ ከነበሩት አብዛኛዎቹ የቀድሞው የሊቢያ ፕሬዘዳንት ደጋፊ የነበሩና በ2011 ...
Read More »አንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ለመስተዳድሩ ተመለሰ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 28/2010) አንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ተመለሰ። ድርጅቱ በምርጫ 97 ቅንጅት የአዲስ አበባ ምክር ቤትን ሙሉ በሙሉ ሲያሸንፍ ወደ ፌደራል ከተዘዋወሩ ተቋማት አንዱ ነበር። በምርጫ 97 የአዲስ አበባ ምክር ቤት በቅንጅት ሙሉ በሙሉ መያዙን ተከትሎ በርካታ የአገልግሎት፣የፋይናንስና የጸጥታ ተቋማት ከከተማው መስተዳድር ወደ ፌደራል መንግስት እንዲዘዋወሩ ተደርጓል። ስራውን የለቀቀው የፌደራሉ ፓርላማና የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመጨረሻ ደቂቃ አዲስ ...
Read More »የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 28 /2010) በኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣዎች የስራ ማቆም አድማን ሲመሩ የነበሩ 9 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። ግለሰቦቹ አለምአቀፍ የበረራ ሂደትን ለማስተጓጎል በተለይም ከውጭ ሀገራት የሚመጡ አውሮፕላኖች እንዳያርፉ ጥረት ሲያደርጉ ተገኝተዋል በሚል ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት ተብሏል። በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ዘንድ ሲደረግ የቆየውን የስራ ማቆም አድማ አስተባብረዋል እንዲሁም መርተዋል ተብለው 9 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት አባላት ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 28/2010) የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት አባላት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑ ታወቀ። ትላንት ጎንደር ወሮታ ከተማ የገቡት የሰራዊቱ አባላትም ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽኝ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሊቀመንበሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ዋና ጸሐፊውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ 200 የሚሆኑ የግንባሩ አመራሮችና አባላት የፊታችን እሁድ አዲስ ...
Read More »አክቲቪስት ታማኝ በየነ ባህርዳር ገባ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 28/2010) በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ትላንት ደማቅ አቀባበል የተደረገለት አክቲቪስት ታማኝ በየነ ዛሬ ባህርዳር መግባቱ ታወቀ። ነገ ደግሞ ወደ ጎንደር እንደሚያቀና የተገለጸው ታማኝ በየነ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም ቀጣይ መርሃ ግብሮች ተዘጋጅተውለታል። በብሔራዊ ቲያትር እንዲሁም በሚሊኒየም አዳራሽና በባህርዳር ስታዲየም እንደትላንቱ ሁሉ ኢትዮጵያዊነትን እየሰበከ የቀጠለው ታማኝ በየነ ቅዳሜ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ...
Read More »ኢትዮጵያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ናት ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 28/2010) ኢትዮጵያ ክፋት በተሞላበት የፖለቲካ ችግር ምክንያት አሁንም መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ ገለጹ። የ2010ን የበጎ ሰው ልዩ ሽልማትን ሲቀበሉ አቶ ለማ መገርሳ እንደገለጹት ጥፋትን የሚያስከትለው የክፋት ፖለቲካ እንዲቀር ሁሉም መተባበር ይኖርበታል። አቶ ለማ መገርሳ የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ የሆኑት በተለያዩ ዘርፎች ተሸላሚ ከሆኑ ኢትዮጵያውያን መካከል ነው። የበጎ ሰው ሽልማት ያገኙት ኢትዮጵያውያን በምርጥ መምህርነት፣በጋዜጠኝነት ...
Read More »በቤንሻንጉል በተፈጠረ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት አለፈ
(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 28/2010) በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት አለፈ። በግጭቱ ከ 10 በላይ የቤንሻንጉል ሰዎችና የኦሮሞ ተወላጆች መሞታቸው ታውቋል። ግጭቱ የተፈጠረው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኦዳ ቤልዲግ ወረዳ ደላቲ ከተማ መሆኑም ታውቋል። በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረው ግጭት በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪም ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በመንዲ ...
Read More »በቴፒ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የተቃውወሞ ሰልፍ አደረጉ
በቴፒ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የተቃውወሞ ሰልፍ አደረጉ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከመልካም አስተዳደር፣ ከሙስናና ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች የመንግስት ባለስልጣናት ተገቢውን መልስ አልሰጡንም በሚል ዛሬ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ውለዋል። ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆነው አቶ ሚስጢሩ ሲሳይ እንደገለጸው ሰልፉ የተደረገው እስካሁን ሲንከባለሉ የነበሩ ጥያቄዎች እንዲመለሱ ለመጠየቅ ነው ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት ታጋዮች አባላት ወደ አገራቸው ተመለሱ
የአርበኞች ግንቦት ታጋዮች አባላት ወደ አገራቸው ተመለሱ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ/ም ) ኤርትራ ውስጥ በትጥቅ ትግል ላይ የቆዩ የሰራዊቱ አባላት ትናንት ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በተለያዩ ከተሞች ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት አቀባበል አድርጎላቸዋል። በሁመራ፣ በጎንደርና በወረታ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ አቀባባል አድርገዋል። ለታጋዮች አቀባበል ያደረጉት የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣ በተለያዩ ጎራ የተሰለፉ ወንድማማቾች በተሰለፉበት ...
Read More »የአማራ ሕዝብ ክፉዎች በፈጸሙበት በደልና ግፍ ሳቢያ ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ ዝቅ አይልም ሢል አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ተናገረ።
የአማራ ሕዝብ ክፉዎች በፈጸሙበት በደልና ግፍ ሳቢያ ከኢትዮጵያዊ ማንነቱ ዝቅ አይልም ሢል አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ተናገረ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 28 ቀን 2010 ዓ/ም ) አክቲቪስት ታማኝ ይህን ያለው፣ ዛሬ በባህር ዳር ስታዲዬም አቀባበል ላደረገለት እጅግ በርካታ የባህር ዳርና አካባቢው ሕዝብ ባደረገው ንግግር ነው። የባህ ዳር ስታዲየም አርቲስት ታማኝን ለመቀበል ከየ አቅጣጫው እየተግተለተለ በመጣው የሰው ጎርፍና በፈጣን ፈረሰኞች ከአፍ ...
Read More »