የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት አባላት ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 28/2010) የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት አባላት ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ መሆኑ ታወቀ።

ትላንት ጎንደር ወሮታ ከተማ የገቡት የሰራዊቱ አባላትም ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽኝ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰራዊት አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሊቀመንበሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ዋና ጸሐፊውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ 200 የሚሆኑ የግንባሩ አመራሮችና አባላት የፊታችን እሁድ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።