ሰኔ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፀረ ሰብል ተባይ ወይም ተምች ወረርሽኝ በአማራ በኦሮሚያ ዞን፣ በምስራቅ ጎጃም፣ በደቡብ ጎንደር፣በሰሜንና በደቡብ ወሎ፣ በትግራይ ደቡባዊ ዞን በአላማጣና ራያ አዘቦ ወረዳዎች ቡቃያዎችን እያጠፋ ነው፡፡ በባህላዊ ዘዴዎችና በኬሚካል ርጭት ለመከላከል ሙከራ ቢደረግም ለውጥ አለመምጣቱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የተምች ተባይ ወረርሽኝ በአማራ በምስራቅ ጎጃም በ11 ወረዳዎች ውስጥ በ12 ሺ 849 ሄ/ር የሰብል ማሣ ላይና ...
Read More »ፍርድ ቤት የባንክ ሂሳባቸውን ያገደባቸው የመንግስት ባለስልጣናትና ባለሀብቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቁጥር የኮ/መ/ቁ 134048 ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ 429 የመንግሥት ኃላፊዎችና ባለሃብቶች በመንግሥትና በግል ባንኮች ያላቸው ገንዘብ የታገደባቸው መሆኑን ፣ የአንዳንዶች ደግሞ የድርጅታቸው የባንክ ሂሳብና መኪኖቻቸው እንዲታገድባቸው ትእዛዝ አስተላልፎአል። ይፋ የሆነው ዝርዝር እንደሚያሳየው ከሙስና ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ሰዎች ቤተሰቦች እና ዘመዶች የባንክ ሂሳብ ቁጥር እንዲታገድ ተደርጓል። ከባለሀብቱ ...
Read More »በደቡብ ጎንደር ዞን መምህራን በደህንነት ሀይሎች ታፍነው ተወሰዱ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደብረ ታቦር ከተማ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ መምህራን ትናንት ማታ እና ዛሬ ጠዋት በደህንነት ሐይሎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። መምህር ታደሰ መንግስቴና መምህር ፈቃዱ ጌትነት የሚባሉ በ ፈቀደ እግዚ ኮሌጅ ውስጥ አስተማሪዎች ሲሆኑ መምህር አሸናፊ አለሙ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ...
Read More »የደሴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ከስራ ተባረሩ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአማራ ክልል የአሰተዳደር እና ጸጥታ ዘርፍ ቢሮ በተለያዩ ዞኖች በሚገኙ የጸጥታ ሀይሎች ላይ ግምገማ ሲያደርግ መቆየቱን ተከትሎ የደሴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ደረጀ እንዲባረሩ ተደርጓል። በቅርቡ ኢሳት ይፋ ባደረገው የድምጽ ማስረጃ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ፖሊስ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶችን እየጣሰ መሆኑን፣ የቀንና የሌሊት ዘረፋ ተባብሶ መቀጠሉን እንዲሁም በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶች መፈጸማቸውን ...
Read More »የፊታችን እሁድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካው ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስአበባ ስታዲየም የሚያካሂደው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወሳኝ ግጥሚያን በመሃል ዳኝነት የሚመሩት ግብጻዊ ዳኛ በመሆናቸው ጨዋታው በሰላም የመጠናቀቁ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ስጋት አሳድሯል
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፊታችን እሁድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካው ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስአበባ ስታዲየም የሚያካሂደው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ወሳኝ ግጥሚያን በመሃል ዳኝነት የሚመሩት ግብጻዊ ዳኛ በመሆናቸው ጨዋታው በሰላም የመጠናቀቁ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ስጋት አሳድሯል። ኢትዮጵያ እያስገነባችው ያለችው የአባይ ግድብ አቅጣጫውን እንዲቀይር መደረጉን ተከትሎ በግብጽ ከተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ግብጻዊው ዳኛ በአዲስአበባ ስታዲየም ዛቻ፣ ስድብና ...
Read More »ወደሶማሌ ክልል ተጉዞ የነበረው የአርቲስቶችና የጋዜጠኞች ቡድን በክልሉ አስተማማኝ ሰላም እንዳለ ምስክርነቱን በመስጠት የአንድ ሳምንት ጉዞውን ሰኞ ዕለት አጠናቀቀ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቡድኑ ከጎዴ ተነስቶ በቀብሪደህር፣ በደገሃቡር፣ በቀብሪበይህ፣ በጂጂጋ አድርጎ ወደሐረር በመግባት የሳምንት ጉዞውን በድሬዳዋ ከተማ ባለፈው እሁድ አጠናቋል፡፡ በጉዞው ወቅት በአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት የተጓዘው የዚሁ ቡድን አባላት ከሆኑት መካከል፤ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፣ደበሽ ተመስገን፣ጥላሁን ጉግሳ፣ችሮታው ከልካይ፣አብራር አብዶ፣ አበበ ባልቻና የመሳሰሉ አርቲስቶችና ጸሐፊዎች “በሶማሌ ክልል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም አለ” በሚል ምስክርነት የሰጡ ...
Read More »የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ እና ግብጽ እንዲነጋገሩ ጠየቀ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ህብረቱ ጥያቄውን ያቀረበው በኮሚሽነሩዋ በዳላሚነ ዙማ አማካኝነት ነው። ሁለቱ አገሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለመፈለግ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመነጋገር መዘጋጀት አለባቸው በማለት ኮሚሽነሩዋ ተናግረዋል። ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እወስዳለው ማለቷን ተከትሎ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግብጽ ስልጣን የያዙ ሰዎች ” ያበዱ” ካልሆኑ በስተቀር ወደ ጦርነት አያመሩም የሚል መልስ ሰጥተዋል። በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የቃላት ጦርነት ...
Read More »በሻሸመኔ ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል ተፈጸመ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቁጥራቸው 13 የሚጠጋ የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት አቶ በየነ ሞርሲ፣ ሳምሶን ራቦ፣ አበራ መቲቦ እንዲሁም በማዘጋጃ ቤት ውስጥ ሀላፊ የሆነ አቶ ዳዊት ደጮ የተባሉት ግለሰቦች ” አብዲ ሁንዳ” እና ሀምሌት የተባሉ የቤትና የንግድ ማህበሮችን መስርተናል በሚል ከግለሰቦቹ በነፍስ ወከፍ እስከ ከ10 ሺ ብር በድምሩ ከ194 ሺ ብር ያላነሰ ገንዘብ ተቀብለዋል። ግለሰቦቹ የኦሮሚያ ...
Read More »ኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ የወጣን ጅብ ለማስወጣት 5 ጥይቶች ሲተኮሱ አንድ ወጣት ቆሰለ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው ሰሞኑን ከምሽቱ አራት ሰዓት በአንድ የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት ሶስተኛ ፎቅ ላይ የተኛውን ጅብ ለማስወጣት አምስት ጥይቶች ተተኩሰው ጅቡ የተገደለ ሲሆን፤ በአካባቢው የነበረ አንድ ወጣት ሆዱ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ገብቷል። ጅቡ በህንጻው ላይ እስከነበረበት ጊዜ ድረስ ፎቁ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች ከቤታቸው ሳይወጡ መቆየታቸውን ፣ እስከ ትናንት ጠዋት አንዳንድ ወላጆች በዱላ እና ...
Read More »ኢትዮጵያና ግብጽ የቃላት ጦርነት ጀምረዋል
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሁለቱ አገሮች መካከል መተነኳኮሱ እየባሰ የመጣው ዘንድሮ ግንቦት 20 ቀን የተከበረውን የገዥውን ፓርቲ በኣል ምክንያት በማድረግ ኢትዮጵያ ፦” የ አባይ ወንዝን የተፋሰስ አቅጣጫ አስቀየስኩ” ብላ ማወጇን ተከትሎ ነው። ይህን ተከትሎ በተለይ የግብጽ መንግስት -ከተቃዋሚዎቹ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ላይ እስከ ወታደራዊ ጥቃት ድረስ የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ የመከሩበት ስብሰባ በይፋ ታየ፤ ይሁንና የግብጽ መንግስት-ከተቃዋሚዎቹ ጋር ...
Read More »