የደሴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ከስራ ተባረሩ

ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአማራ ክልል  የአሰተዳደር እና ጸጥታ ዘርፍ ቢሮ በተለያዩ ዞኖች በሚገኙ የጸጥታ ሀይሎች ላይ ግምገማ ሲያደርግ መቆየቱን ተከትሎ የደሴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ደረጀ እንዲባረሩ ተደርጓል።

በቅርቡ ኢሳት ይፋ ባደረገው የድምጽ ማስረጃ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች ፖሊስ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶችን እየጣሰ መሆኑን፣ የቀንና የሌሊት ዘረፋ ተባብሶ መቀጠሉን እንዲሁም በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶች መፈጸማቸውን መግለጻቸው ይታወሳል::

በግምገማ ወቅት በኮማንደር ደረጀ ላይ ከቀረቡት ትችቶች መካከል ” የከተማውን ህዝብ ማንገላታት ፤ በማን አለብኝነት ወጣቱን ማሰር እና መፍታት ፤ጠበቆችን ለሙስሊሞች ለምን ትቆማላችሁ የአሸባሪ ከለላ ናችሁ በማለት ማንገላታት፤ጉዳዩችን መደበቅ የሚሉት እንደሚገኙበት የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

ኮማንደሩን ከስራ በማሰናበት የደሴ ህዝብ የሰብአዊ መብት ጥሰት አይቆምም በማለት አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ጠበቃ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል የአስተዳደርና የጸጥታ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ አየለ አናውጤ የፖሊስ አዛዡ የተለያዩ ትችቶች እና ክሶች ቀርበውበት ከሃለፊነት እንዲነሱ መደረጉን ለኢሳት ተናግረዋል።

የክልሉ ህዝብ በየጊዜው በሚያሰማው አቤቱታ የተነሳ የጸጥታ ተቋሙ እንዲገመገም መደረጉን አቶ አየለ