ኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ የወጣን ጅብ ለማስወጣት 5 ጥይቶች ሲተኮሱ አንድ ወጣት ቆሰለ

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው ሰሞኑን  ከምሽቱ አራት ሰዓት  በአንድ  የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤት ሶስተኛ ፎቅ ላይ የተኛውን ጅብ  ለማስወጣት አምስት ጥይቶች ተተኩሰው ጅቡ የተገደለ ሲሆን፤ በአካባቢው የነበረ አንድ ወጣት  ሆዱ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ገብቷል።

ጅቡ በህንጻው ላይ እስከነበረበት ጊዜ ድረስ ፎቁ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች ከቤታቸው ሳይወጡ መቆየታቸውን ፣  እስከ ትናንት ጠዋት  አንዳንድ ወላጆች በዱላ እና በአንዳንድ ነገሮች ጅቡን እየተከላከሉ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላካቸው ተዘግቧል።

ፖሊሶች ጅቡን በ5 ጥይቶች ሲገድሉ ያቆሰሉት ወጣት በሆስፒታል ህክምና  እየተከታተል  ይገኛል::