የአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ እና ግብጽ እንዲነጋገሩ ጠየቀ

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ህብረቱ ጥያቄውን ያቀረበው በኮሚሽነሩዋ በዳላሚነ ዙማ አማካኝነት ነው። ሁለቱ አገሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለመፈለግ በጠረጴዛ ዙሪያ ለመነጋገር መዘጋጀት አለባቸው በማለት ኮሚሽነሩዋ ተናግረዋል።

ግብፅ ኢትዮጵያ ላይ እርምጃ እወስዳለው ማለቷን ተከትሎ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በግብጽ ስልጣን የያዙ ሰዎች ” ያበዱ” ካልሆኑ በስተቀር ወደ ጦርነት አያመሩም የሚል መልስ ሰጥተዋል።

በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የቃላት ጦርነት እየጨመረ ሄዷል።