የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በምእራብ ጎጃም ዞን በሜጫ ወረዳ ቺቦቼ ቀበሌ የእርሻ መሬታቸውን ለአበባ ልማት በሚል እንዲያስረክቡ ተጠይቀው ፈቃደኛ ያልሆኑ ከ40 ያላነሱ አርሶአደሮች በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። አርሶደሮቹ በአሁኑ ጊዜ ስላሉበት ሁኔታ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። የሜጫ ወረዳ በግብርና ምርቱ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአበባ እርሻ እየተባለ በርካታ አርሶአደሮች መሬታቸውን ...
Read More »ፑቲን ጦራቸው በዩክሬን ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዱን ተናገሩ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሩስያው ፐሬዚዳንት ቭላድሜር ፒቲን ዩክሬን የሚገኘው ጦራቸው በአገሪቱ የሚገኙ ሩስያውያንን ከመጠበቅ ውጭ ምንም እርምጃ አለመውሰዳቸውን ለጋዜጠኖች ተናግረዋል፡፡ በአገሪቱ የሚገኙት ሩሲያውያን እርዳታቸውን ከጠየቁ፣ አገራቸው በዩክሬን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር ማንኛውንም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ግልጽ አድርገዋል። የሩሲያ ጦር የዩክሬንን ግዛት መውረሩን ተከትሎ በምእራባዊያን እና በሩሲያ መካከል ሰሞኑን የተፈጠረው ውዝግብ እንደቀጠለ ሲሆን፣ ፑቲን በሩሲያ ላይ ...
Read More »ሼክ ሁሴን ሙሀመድ አላሙዲ በአለም 61ኛው ባለሃብት ተባሉ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢትዮጵያና ሳውድ አረቢያ ወላጆች የተወለዱት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ባለቤት ሼክ ሙሀመድ አላሙዲን፣ በያዝነው አመት አጠቃላይ ሀብታቸው 15 ቢሊዮን 300 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን ፎርቢስ መጽሄት ይፋ አድርጓል። ሼክ አላሙዲን በነዳጅ፣ በማእድንና በግንባታ ስራዎች ከፍተኛ ሀብት ማካበታቸው ተመልክቷል። ባለሀብቱ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢነቨስትመንት ያላቸው ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያጠሩ በሚያስቀምጡዋቸው ቦታዎች መንግስት እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑ ...
Read More »12 ሺ ቶን ቡና በተጭበርበረ ሰነድ ወደ ውጭ አገር መላኩ ታወቀ
የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቅርቡ በቡና አስተዳደር ላይ የሚታየውን ችግር አስመልክቶ ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ 12 ሺ ቶን ወይም 1 መቶ 20 ሺ ኩንታል ቡና በተጭበረበረ ሰነድ ወደ ውጭ ተልኮ መሸጡን አመልክቷል። ኮሚሽኑ ቡናው በማን በኩል ተሰርቆ እንደተላከ እያጣራ መሆኑን የዘገበው ሪፖርተር፣ የሽያጩ ገንዘብም ወደ አገር ውስጥ አለመግባቱን ገልጿል። ዛሬ ባለው የአለም ...
Read More »የመንግስት ባለስልጣናት ከተመረጡ ጋዜጠኞች ጋር ሊነጋገሩ ነው
የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በታህሳስ 2006 መጨረሻ የኢትዮጵያ ፕሬስ እና የኢትዮጽያ ዜና አገልግሎት ድርጅቶች ያጠኑትና ሰባት የግል መጽሔቶች ላይ ያተኮረ ጥናት ይዘት ላይ የሚወያይና ከፍተኛ የመንግስት ባለልጣናት የሚገኙበት ለጋዜጠኞች የተዘጋጀ ስብሰባ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በአዳማ እንደሚካሄድ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የመንግስት ድጋፍ ያላቸው የጋዜጠኛ ማህበራት ከመንግስት የኮምኑኬሽን ጽ/ቤት ጋር በመተባበር እንዳዘጋጁት በተነገረለት ስብሰባ ላይ ከ100 በላይ የመንግስትና ...
Read More »የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በአቶ አለምነው መኮንን ንግግር ላይ መግለጫ ሳያወጣ ተጠናቀቀ
የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስብሰባውን በባህርዳር ከተማ ሲያካሂድ የሰነበተው የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የንቅናቄው የጽህፈት ቤት ሀላፊ የአማራውን ህዝብ የዘለፉበትን ንግግር ያስተባብላል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ምንም ሳይል ቀርቷል። ንቅናቄው ” ህዝቡ በተቃዋሚዎችና ተባባሪዎቻቸው የሚነዙ አሉባልታዎችን ወደ ጎን በማለት ከብአዴን ጎን ጎን እንዲሰለፍ” የሚል መግለጫ በማውጣት ስብሰባውን አጠናቋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የጠየቅነው አንድ የብአዴን አባል፣ አቶ አለምነው ቀድሞውንም የተናገረው ...
Read More »የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ አብጠለጠለ
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስሪያ ቤቱ በ2013 ሪፖርቱ በአገሪቱ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር አስቀምጧል። በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታዩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል ሃሳብን በነጻነት የመግልጽና የመደራጀት መብት ቀዳሚ መሆኑን ሪፖርቱ ይገልጻል። ዜጎች በዘፈቀደ ይታሰራሉ፣ ይታፈናሉ፣ በእስር ቤት ይሰቃያሉ፣ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ይገደላሉ፣ በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ማስፈራሪያ ይደርስባቸዋል እንዲሁም በእስር ቤት ውስጥ አሰቃቂ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸዋል። ፍርድ ቤቶች ...
Read More »በስዊዘርላንድ እና በኖርዌይ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሄዱ
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊዘርላንድ በርን ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ በርካታ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንግድ ንበረት የሆነ አውሮፓላን በመጥለፍ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ያሳረፈው ሃይለመድህን አበራ አፋጠኝ ፍትህ እንዲያገኝ ጠይቀዋል። “ሃይለመድህን ወንጀለኛ አይደለም፣ ወንጀለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ነው፣ አሸባሪው ወያኔ ነው፣ ህዝቡን አግቶ የያዘው የኢትዮጵያው አሸባሪ መንግስት ነው፣ ዲሞክራሲና ፍትህ ለኢትዮጵያ” የሚለዩና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል። በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲና ...
Read More »ሱዳንና ኢትዮጵያ በድንበር አካባቢ የጋራ ጥምር ሃይል ለማቋቋም ተስማሙ
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር አብዱል ራሂም ሙሀመድ እንዳሉት ሁለቱ አገራት ከየመከላከያ ሰራዊታቸው የተውጣጡ ጥምር ሃይል በማቋቋም በድንበሮች ላይ አሰሳ ማድረግ ይጀምራሉ። ሚኒስትሩ በሁለቱ መንግስታት መካከል የሚደረገው ተከታታይ ውይይት እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ አድርጓቸዋል። ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የመከላከያ ሚኒሰትር ሲራጅ ፈርጌሳ ፈርመዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ የአገሪቱ ዜጎች የትጥቅ ትግል ለማድረግ የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚዎችን ለመቀላቀል በሱዳን ...
Read More »የዩጋንዳ መንግስት ግብረ-ሰዶማዊነትን ለመከላከል ያወጣውን ህግ በመቃወም ምእራባዊያን አገራት እርምጃ እየወሰዱ ነው
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕ/ት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ግብረሰዶማዊነትን ለመከላከል ያወጡት ህግ በርካታ የምእራብ አገራትን ያስቆታ ሲሆን፣ በብዙ የአፍሪካ አገራት ደግሞ ድጋፍ ተችሮአቸዋል። የምእራብ አገራት በሚወስዱት የተቀነባበረ እርምጃ ኖርዌይና ዴንማርክ ለመንግስት በቀጥታ የሚሰጡትን ድጋፍ ሲያቋርጡ፣ የአለም ባንክ ደግሞ ለአገሪቱ የሚሰጠውን የ90 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አግዷል። የደቡብ አፍሪካው ነጻነት ታጋይ ዴዝሞንድ ቱቱ የኡጋንዳን መንግስት ድርጊት ሲያወግዙ፣ የአሜሪካው ...
Read More »