የዩጋንዳ መንግስት ግብረ-ሰዶማዊነትን ለመከላከል ያወጣውን ህግ በመቃወም ምእራባዊያን አገራት እርምጃ እየወሰዱ ነው

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕ/ት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ግብረሰዶማዊነትን ለመከላከል ያወጡት ህግ በርካታ የምእራብ አገራትን ያስቆታ ሲሆን፣ በብዙ የአፍሪካ አገራት ደግሞ ድጋፍ ተችሮአቸዋል።

የምእራብ አገራት በሚወስዱት የተቀነባበረ እርምጃ ኖርዌይና ዴንማርክ ለመንግስት በቀጥታ የሚሰጡትን ድጋፍ ሲያቋርጡ፣ የአለም ባንክ ደግሞ ለአገሪቱ የሚሰጠውን የ90 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አግዷል።

የደቡብ አፍሪካው ነጻነት ታጋይ ዴዝሞንድ ቱቱ የኡጋንዳን መንግስት ድርጊት ሲያወግዙ፣ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪም በተመሳሳይ መንገድ ውሳኔውን አውግዘዋል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ኡጋንዳ ወሰደቸው እርምጃ የአገሪቱን የውጭ ኢንቨስትመንት ይጎዳል።

ሙሴቪኒ ከምእራባውያን የደረሰባቸውን ውግዘት ከአፍሪካውያን በሚያገኙት ድጋፍ ሲያካክሱት፣ ኡጋንዳ ራሱዋን የቻለችና እና በምእራባዊያን አገራት የማትሽከረከር አገር መሆኑን ለማሳየት የተወሰደ እርምጃ ነው ብለዋል።