በስዊዘርላንድ እና በኖርዌይ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሄዱ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊዘርላንድ በርን ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ በርካታ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንግድ ንበረት የሆነ አውሮፓላን በመጥለፍ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ያሳረፈው ሃይለመድህን አበራ አፋጠኝ ፍትህ እንዲያገኝ ጠይቀዋል።

“ሃይለመድህን ወንጀለኛ አይደለም፣ ወንጀለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ነው፣ አሸባሪው ወያኔ ነው፣ ህዝቡን አግቶ የያዘው የኢትዮጵያው አሸባሪ መንግስት ነው፣ ዲሞክራሲና ፍትህ ለኢትዮጵያ” የሚለዩና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።

በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች ድጋፍ ሰጪ ኮሚቴ ባዘጋጀው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል።

በኖርዌይ ኦስሎ በስዊዘርላንድ ኢምባሲ ፊት ለፊት በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኘው ባልደረባችን ደረጃ ሃብተወልድ፣ ኢትዮጵያውያኑ የሃይለመድህን አበራ የጥገኝነት ጥያቄ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጠው መጠየቃቸውን ገልጿል