መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ችግር ለጀርመን ሬዲዮ በመዘገብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በውል ባልታወቀ ምክንያት ሳምንታትን በእስር ለማሳለፍ መገደዱ ታውቋል። ነብዩ በተለይም ከወራት በፊት ከሳውድ አረቢያ በሚፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ ሚዛናዊ ዘገባዎችነ በማቅረብ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ስሜት ለመግዛት ቻለብዙዎች በድፍረቱ የሚያደንቁት ጋዜጠኛ ነው። የነብዩን ቤተሰቦችም ሆነ የጀርመን ድምጽ የአማራኛው ክፍል ሃላፊን ለማግኘት በተደጋጋሚ ...
Read More »በኬንያ ወንዶች ተጨማሪ ሚስቶች እንዲኖራቸው የሚያዘው ህግ በፓርላማው ጸደቀ
መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአመታት ሲያወዛግብ የነበረው ወንዶች ባለ ብዙ ሚስቶች የሚያደርጋቸው ህግ ትናንት በፓርላማ አባላት ሲጸድቅ፣ 30 የሚሆኑ ሴት የፓርላማ አባላት ክርክሩን ረግጠው ወጥተዋል። አንድ የፓርላማ አባል ” ይህ አፍሪካ ነው፣ በአፍሪካ ባህል የአፍሪካ ሴት ስታገባ ፣ ባለቤትህ ሌሎች በመምጣት ላይ ያሉ ሁለት ወይም ሶስት ሴቶች እንዳሉ ታውቃለች፣ ምንም አዲስ ነገር የለውም” ብለዋል። አብዛኞቹ ...
Read More »በሀረር በህዝቡና በአስተዳደሩ መካከል ያለው አለመተማመን መስፋት ወደ ብሄር ግጭት እንዳያመራ ተስግቷል
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሃረር በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የንግድ ቤቶች መቃጠላቸውን ተከትሎ፣ በህዝቡና ክልሉን በሚመራው የሃረሪ ሊግ መካከል የተፈጠረው ከፍተት እየሰፋ መሄድ የብሄር ግጭት ሊያስነሳ ይችላል በማለት ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። ኢሳት ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት ክልሉን የሚያስተዳድረው የሃረሪ ሊግ ” መጤዎች ከከተማችን ውጡ” የሚሉ ቅስቀሳዎችን ከጀርባ ሆኖ በማሰራጨትና የንግድ ቤቶችን በማቃጠል ለዘመናት ...
Read More »አንድነት ፓርቲ የእሪታ ቀን በሚል በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ ነው
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው የተቃውሞ ሰልፉን የሚጠራው በዋና ከተማዋ የሚታዩትን የማህበራዊ አገልግሎቶችን ችግሮች ለመቃወም ነው። “በከተማዋ ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ የወጣባቸው መንገዶች ለምረቃ በበቁ በጥቂት ቀናት ልዩነት መፍረሳቸው፣ የከተማው ነዋሪ ለሚጠቀምባቸው የመጓጓዣ አውታሮች ተለዋጭ መንገድ ባለመዘጋጀቱ ለተጨማሪ ወጪ መዳረጉን፣ ትራንስፖርት ማግኘት በሁሉም አካባቢዎች አስቸጋሪ በመሆኑ የከተማይቱ የሥራ እንቃስቃሴ መዳከሙን፣ መንግሥት ‹‹የምትታለብ ላም›› በማለት ...
Read More »የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሽቆልቆል አሳሳቢ ሆኗል
መጋቢት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስአበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በታሪኩ አይቶ የማያውቀው የአገልግሎት አሰጣጥ መጨናነቅ እንዳጋጠመውና በዚህም ምክንያት ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አንጻር የአገልግሎት ጥራቱ ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱን አንድ ከድርጅቱ የተገኘ ጥናታዊ ጽሁፍ አመለከተ፡፡ አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ለሃያ ዓመታት በዓመት 6 ሚሊየን መንገደኞችን በብቃት ሊያስተናግድ ይችላል ተብሎ የተገነባ ቢሆንም በአስረኛ ዓመቱ የመንገደኞች ...
Read More »በኩዌይት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ናቸው
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ውጥረቱ የተጀመረው አንዲት ኢትዮጵያዊት አንድ የአገሪቱን ባለስልጣን ልጅ መግደሉዋን ተከትሎ ነው። ኢትዮጵያዊቷ ግድያውን የፈጸመችበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማወቅ ባይቻልም፣ ገዳዩዋን በቅርብ እናውቃለን ከሚሉ ወገኖች የተገኘው መረጃ በቂም በቀል ተብሎ የተደረገ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ይገልጻሉ። ከሶስት አመት በፊት ወደ ኩዌት የገባችው ወጣት በመጀመሪያው ወር በአሰሪዋ ልጅ መደፈሩዋን ለመበቀል በሚል የባለስልጣኑን ልጅ ለመግደል እንደተነሳሳች መግለጿን ...
Read More »የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በዋስ ተፈቱ
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 10 የፓርቲው ሴት እና ወንድ አመራሮች ያለፉትን 11 ቀናት በእስር ቤት ካሳለፉ በሁዋላ ፖሊስ እያንዳንዳቸውን በ3 ሺ ብር ዋስ ለቋቸዋል። ምንም እንኳ አቃቢ ህግ ክስ ለመመስረት የሚያስችል በቂ ማስረጃ የለኝም ቢልም፣ ፖሊስ እስረኞችን በነጻ ከመልቀቅ በዋስ መልቀቅን መርጧል። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃ እንደሚሉት እስረኞቹ በነጻ ካልሆነ በዋስ አንፈታም የሚል አቋም ...
Read More »ነጋዴዎች በግብር ስርአቱ መማረራቸውን ተናገሩ
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነጋዴዎች ምሬታቸውን የገለጹት ሰሞኑን በግብር አከፋፈል ዙሪያ ላይ በባህር ዳር ከተማ የኢፌዴሪ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ባካሄደው ስብሰባ ላይ ነው፡፡ በስብሰባው ላይ በአማራ ከልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት አማካኝነት የተካሄደ ጥናት የቀረበ ሲሆን፣ በጥናቱምው በግብር ሰብሳቢውና በግብር ከፋዩ መካከል ያለው ግንኙነት መሻከሩ ተመልክቷል፡፡ የግብር ስርአቱ አገልግሎት አሰጣጥ የፍትሀዊነት ችግሮች ያሉበት በመሆኑ በነጋዴውና በመንግስት ...
Read More »በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው
መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ውስጥና በዙሪያዋ ዋና መግቢያ በሮች በሚገኙ ከተሞች በየቀኑ የሚከሰተውን ከፍተኛ ቁጥር ያለው የትራፊክ አደጋ ተከትሎ በአንድ ክፍለ ከተማ ብቻ 3 ሰዎች በየቀኑ እንደሚሞቱ ለማዎቅ ተችሏል፡፡ በረ/ኢ/ር አሰፋ መዝገቡ በኩል ከመንግስት ሚዲያዎች በየቀኑ እንደሚገለጸው በከተማዋ የሚከሰተው የትራፊክ አደጋ ቁጥር ከመቼውም በተለየ እየጨመረ ሲሆን ለዚህም እንደምክንያት የሚቀርበው ለመንገደኛ ቅድሚያ መከልከል፣ርቀትን ጠብቆ ...
Read More »በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጉዳይ በድጋሜ ተቀጠረ
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ ሩጫ ላይ ተቃውሞ አሰምታችሁዋል በሚል ከአስር በላይ ቀናትን በእስር ያሳለፉት የሰማያዊ ፓርቲ 7 ሴት እና 3 ወንድ አመራሮች መጋቢት 5 ቀን 2006 ዓም ጉዳያቸው ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚታይና ለዛሬ መጋቢት 9 ውሳኔ እንደሚሰጣቸው በዳኛው ተገልጾ የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ጉዳዩ በመደበኛ ፍርድ ቤት እንዲታይ በመጠየቁ ፍርድ ቤቱ ...
Read More »