በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ ከ60 በላይ ቤቶችና ድርጅቶች ይፍረሱ መባሉ ውዝግብ አስነሳ

ማጋቢት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በንፋስ ስልከ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፣ ከለቡ አካባቢ ተነስቶ በቱሉ ዲምቱ አድርጎ አዳማ ድረስ ይሠራል በተባለው መንገድ ምክንያት፣ ከ60 የሚበልጡ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች እንደሚፈርሱ በመገለጹ፣ ነዋሪዎችና ክፍለ ከተማው እየተወዛገቡ መሆናቸውን ሪፖርተር ዘገበ። የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማትን ለመገንባት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር   በ1994 ዓ.ም ያቀረቡት  ጥያቄ  ተቀባይነት አግኝቶ በ1997 ዓ.ም.  የአካባቢውን ...

Read More »

ዩክሬን 60 ሺህ ያህል ጠንካራ የመከላከያ ሀይል እንድትገነባ የአገሪቱ ፓርላማ አዋጅ አጸደቀ።

ማጋቢት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱ የመከላከያ አዋጅ ግንባታ የጸደቀው  ሩሲያ በአወሳጋቢዋ ክሪሚያ  የፊታችን እሁድ ሪፈረንደም ለማካሄድ በተሰናዳችበት ወቅት ነው። ክሪሚያ በአሁኑ ሰዓት በሩሲያ የጦር ሀይል ስር የምትገኝ ሲሆን፣ በመጪው እሁድ በሚካሄደው ሪፈረንደም ነዋሪዎቿ በሩሲያ ስር መተዳደር እንደሚፈልጉና እንደማይፈልጉ ድምፃቸውን ይሰጣሉ። ፕሬሲዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፦ በየክሬን በተፈጠረው ቀውስ ሩሲያ ተጠያቂ እንዳልሆነች በተደጋጋሚ እየገለፁ ይገኛሉ። ፑቲን ይህን ቢሉም  ...

Read More »

በሃረር ከተማ የተከሰተውን የእሳት አደጋ ተከትሎ ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ነዋሪዎች ተናገሩ

ማጋቢት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት ስልክ በመደወል እንደገለጹት ከቃጠሎው በሁዋላ በከተማው የሚታየው ድባብ አስፈሪ ነው። በቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከመስተዳድሩ ምንም አይነት የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት አለመቻላቸው የህዝቡ ቁጣ እንዲጨምር አድርጎታል። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠረውን ንብረት ያወደመውን እሳት የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ሆን ብለው አስነስተውታል በሚል ትችት እየቀረበባቸው ነው። መስተዳድሩ በአፋጣኝ ለወደመው ንብረት ተገቢውን ግምትና ካሳ ...

Read More »

የፕሬዚዳንቱን ስልጣን የሚሽር ረቂቅ ህግ ለፓርላማ ቀረበ

ማጋቢት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሁን በስራ ላይ የሚገኘውን የይቅርታ ስነስርዓት አዋጅ ቁጥር 395/1996 አዋጅ የሚያሻሻልና የኢትዮጵያን ፕሬዚደንት ስልጣን  የሚቀንስ ረቂቅ አዋጅ  ለፓርላማ ቀረበ፡፡ በፍትህ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በሚኒስትሮች ም/ቤት ታይቶ ወደፓርላማ የተመራው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያሳየው አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ የፍትህ ሚኒስቴር ይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት ይቅርታ የጠየቁ ታራሚዎችን ጉዳይ መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ ለፕሬዚደንቱ ሲቀርብ በፕሬዚደንቱ ውሳኔ ይቅርታው ...

Read More »

ወደ ክልል ተዘዋውረው የሚሰሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች እየተያዙ ነው

ማጋቢት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ ሾፌሮች ለኢሳት እንደገለጹት በባህርዳር ከተማ ወደ ሌሎች ክልሎች ወይም ተዘዋውረው በመስራት ላይ ያሉ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ የታክሲ አሽከርካሪዎች ታስረው 10 ሺ ብር የሚደርስ ቅጣት እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው። በአገራችን እንደልባችን ከክልል ክልል ተዘዋውረን እንዳንሰራ በፖሊሶች ታግደናል የሚሉት ሾፌሮች፣ ለምን ብሎ የጠየቀ ሰው ድብደባ እንደሚፈጸምባቸው ይናገራሉ በሌላ በኩል ደግሞ በሸዋ ሮቢት ከተማ የሚገኙ ...

Read More »

የካርቱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ጀመሩ

ማጋቢት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ200 ያላነሱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በዳርፉር የተነሳውን ግጭት በመቃወም ወደ አደባባይ ሲወጡ ፖሊስ በሃይል ለመቆጣጠር ሙከራ አድርጓል። አንድ ተማሪ መሞቱንና ሌላ አንድ ተማሪ መቁሰሉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ተማሪዎቹ ከግቢያቸው ለመውጣት አደረጉት ሙከራ በፖሊስ ቁጥጥር ሲል እንዲውል መደረጉን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርን የሚቃወሙ ታጠቂዎች ጋብ ብሎ የነበረውን የዳርፉር ግጭት መጀመራቸው ታውቋል። በአለማቀፍ ፍርድ ...

Read More »

በሀረር ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ታሰሩ

ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀረር ባለፈው እሁድ ምሽት የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ ለተቃውሞ አደባባይ የወጣው ህዝብ በፖሊስ ከተበተነ በሁዋላ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች መታሰራቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከትናናት ጀምሮ ፖሊሶች መንገድ ላይ ያገኙዋቸውን ወጣቶች እያፈሱ እንዲሁም ከቤታቸው እያወጡ ወደ እስር ቤት ወስደዋቸዋል። በዛሬው እለት በቃጠሎው የደረሰውን ጉዳት አቤት ለማለት የተሰባሰቡ 15 ወጣቶች በፖሊሶች ተይዘው መታሰራቸውን አንድ ...

Read More »

በጅጅጋ 300 እስረኞች መንገድ ላይ ተጣሉ

ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጅጅጋ እስር ቤት ውስጥ ታስረው ከነበሩ ቁጥራቸው በውል ከማይታወቅ እስረኞች መካከል 300 ያክሉ ከአራት ቀናት በፊት በጅጅጋ መንገድ ላይ መጣላቸው ታውቀ። የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ያላከውን መረጃ በመንተራስ ኢሳት ባደረገው ማጣራት፣ ባለፈው ሃሙስ ለአርብ አጥቢያ አካላቸው በምግብ እጦት የከሳ፣ አይናቸው የታወረ፣ እግሮቻቸው ሽባ የሆኑ፣ የአእምሮ መታወክ የደረሰባቸውና አሰቃቂ የእስር ቤት ህይወት እንዳሳለፉ ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት – “የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት!” የተሰኘውን ንቅናቄ አስመልክቶ ከአንድነት ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያየ።

ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍኖተ ነፃነት እንደዘገበው-በኢትዮጵያ የአዉሮፓ ሕብረት ልኡካን ቡድን መሪ አምባሳደር ቻንታል ሔበሬሽ፣ በአዉሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ እና የሕንድ ዉቂያኖስ አካባቢ ዴስክ ኦፌሴር ቪክቶሪያ ጋርሲያ ጉሌን እና ቶማስ ሁይገባርቴስ የተሰኙ ፣ የአዉሮፓ ሕብረት ሃላፊ ፣-ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር ሰፊ ዉይይት አድርገዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ስላለው የዲሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ ከጠ/ሚኒስተር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ጦር በአልሸባብ ላይ የተጠናከረ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የንቅናቄው መሪ በኢትዮጵያ ላይ ጅሃድ አወጁ

ማጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአልሸባብ መሪ አህመድ ጎዳኔ በቅጽል ስማቸው ሙክታር አቡ አል ዙቢያር ” ለአሜሪካ መንግስት ጥቅም የሚዋጉት የሞቃዲሾ መንግስትና የኢትዮጵያ ጦር በጦርነቱ ድል ይሆናሉ “ብለዋል። “ሶማሊዎች ሃይማኖታችሁ ተደፍሯል፣ መሬታችሁ ተከፋፍሏል፣ ንብረታችሁ ተዘርፏል፣ ድላችን በጅሃድ ላይ የተመሰረተ ነው ” ሲሉ ሚ/ር ጎዳኔ ተናግረዋል። ወደብ አልባ የሆነችው ኢትዮጵያ  ወደብ ለማገኘት ስትል ሶማሊያን መውረሩዋን የሚናገሩት የአልሸባቡ መሪ ...

Read More »