ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ አሁንም በእስር ላይ ነው

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ችግር ለጀርመን ሬዲዮ በመዘገብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በውል ባልታወቀ ምክንያት  ሳምንታትን በእስር ለማሳለፍ መገደዱ ታውቋል።

ነብዩ በተለይም ከወራት በፊት ከሳውድ አረቢያ በሚፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ዙሪያ ሚዛናዊ ዘገባዎችነ በማቅረብ የበርካታ ኢትዮጵያውያንን ስሜት ለመግዛት ቻለብዙዎች በድፍረቱ የሚያደንቁት ጋዜጠኛ ነው።

የነብዩን ቤተሰቦችም ሆነ የጀርመን ድምጽ የአማራኛው ክፍል ሃላፊን ለማግኘት በተደጋጋሚ ስልካቸው ላይ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልም። ድርጅቱ የጋዜጠኛውን መታሰር በተመለከተ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጠም።