መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በከተማዋ ከተነሳው ቃጠሎ ጋር በተያያዘ የታሰሩ 7 ሰዎች ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ እንዲለቀቁ ዳኛ የሱፍ ውሳኔ ያስተላለፉ ቢሆንም፣ እስረኞቹ አስፈላጊውን ክፍያ ከፈጸሙ በሁዋላ ከእስር ለመውጣት ሲዘጋጁ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ክንፈ አብዱል ፈታ ” ፍርድ ቤት አቃቢህግና መርማሪ ፖሊስ ባልተገኘበት ሁኔታ ስለሆነ ውሳኔ ያስተላለፈው አትፈቱም” በማለቱ ዛሬ መለቀቅ የነበራቸው እስረኞች ሳይለቀቁ ...
Read More »የደቡብ ሱዳን አማጽያን የነዳጅ ማውጫ ጉድጓዶችን እንደሚቆጣጠሩ አስታወቁ
መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ ማህበረሰብ አማጽያኔኑን ከመንግስት ጋር ለማስታረቅ ደፋ ቀና ሲል ቢከርምም ፣ አማጽያኑ ግን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርን ከስልጣን አስገድዶ ለማውረድ ሲሉ የነዳጅ ማውጫ ቦታዎችን ለመቆጣጠር መወሰናቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል። ነጭ ጦር እየተባለ የሚጠራው ከአማጽያኑ መሪ ሪክ ማቻር ጋር ጥምረት ያለው ቡድን ለመንግስት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኘውን የ ፓሎችን የነዳጅ ጉድጓዶች ለመቆጣጠር ዝግጅት እያደረ ነው። ማቻር ...
Read More »የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የአንድነት ፓርቲን የሰላማዊ ሰልፍ የእውቅና ጥያቄ እንደማይቀበል አስታወቀ
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የከንቲባ ጽህፈት ቤቱ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባዎች ኦፊሰር የሆኑት አቶ ማርቆስ ብዙነህ ለፓርቲው በጻፉት ደብዳቤ ” የአዲስ አበባ አስተዳደር የስብሰባና የሰላማዊ ሰልፍ አሰራር ስነስርአት በርካታ ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲና የመንግስት ተቋማት በሚገኙበት አካባቢ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ የማይቻል በመሆኑ የተጠየቀውን የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ጥያቄ” አልተቀበንነውም ብለዋል። የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ...
Read More »በጉጂና በቦረና መካከል የተፈጠረውን ግጭት የአገር ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብተው ማብረዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ20 በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሞት ምክንያት የሆነውን በጉጂ ዞን የተከሰተውን የጎሳ ግጭት ለማስቆም የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎች ወደ አካባቢው ተንቀሳቀስው የሁለቱን ጎሳዎች ሰዎች ካነጋገሩ በሁዋላ ላለፉት 4 ቀናት የተካሄደው ግችት ሊቆም ችሎአል። ምንም እንኳ ግጭቱ ቢቆምም ውጥረቱ ግን አሁንም እንዳለ ነው። ለግጭቱ መነሳት ምክንያት ሆነዋል የተባሉ የአካባቢው ባለስልጣናት እስካሁን ተጠያቂዎች አለመሆናቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ...
Read More »በሀረር ከተማ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ ድበደባ እየተካሄደባቸው ነው
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የእስር ቤት ምንጮች እንደገለጹት በሀረር ከደረሰው ተደጋጋሚ ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተቃውሞቸውን አሰምተዋል በሚል የታሰሩት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፌደራል ደህንነት መርማሪዎች ከፍተኛ ድብደባ እየተካሄደባቸው ነው:፡ ፖሊስ ጋራጅ ውስጥ የታሰሩት ወጣቶች ከምግብ ተከልክለው ከዘመድ እንዳይገናኙ ተደርገው ” እመኑ” በሚል ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው ነው። ታከሉ ሙላቱ፣ ታገሰ ሙላቱና አዳነ የሚባሉ የጫማ ንግድ ድርጅት ባለቤቶች ...
Read More »የኩረጃ መስፋፋት የትምህርት ጥራትን እየጎዳ ነው ተባለ
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሔራዊ ፈተናዎች በተለይ የ8ኛ እና የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተናዎች ላይ ኩረጃ በአሳሳቢ ደረጃ እየተባባሰ መምጣቱን፣ ለትምህርት ጥራት ማሽቆልቆል አንድ ምክንያት እየሆነ መሆኑን የፌዴራል የስነምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን ያካሄደው ጥናት ጠቁሟል፡፡ ሰሞኑን ይፋ ሆነው ይህው ጥናት በኩረጃው ሒደት በተቀነባበረ መልኩ ሁሉም አካላት ማለትም ፈተና አስተባባሪዎች፣ፈታኞች፣ የፈተና ጣቢያ ሃላፊዎች፣ርዕሰመምህራን፣ መምህራን፣ ወላጆች በቀጥታ ይሳተፋሉ፡፡ ...
Read More »በናይጀሪያ መከላከያ ሰራዊቱ ከ600 በላይ ሰዎችን መግደሉን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገለጸ
መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታዋቂው የሰብኢ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ እንደገለጸው የናይጀሪያ መከላከያ ሰራዊት፣ የእስልምና መንግስት ለማቋቋም የሚታገለውን ቦኮ ሃራም የተባለውን ተዋጊ ሃይል ለመውጋት በሚል ሰበብ በከፈተው ጥቃት ከ600 በላይ ዜጎች ተገድለዋል። መከላከያ ሰራዊቱ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በሚወስደው እርምጃ በአለማቀፍ የጦር ወንጀለኝነት ሊጠየቅ እንደሚገባው የገለጸው አምነስቲ፣ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎችም በተመሳሳይ ንጹሃን ላይ የሚወስዱት እርምጃ ...
Read More »በጉጂ እና በቦረና ተወላጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት የማቾች ቁጥር መጨመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ
መጋቢት ፲፰ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ባለፉት 3 ቀናት ከቦረና እና ከጉጂ ጎሳዎች ከ20 ያላነሱ ሰዎች ሲሞቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። ብዙ ቤቶች መቃጠላቸውንና መጠኑ በውል ያልታወቀ ንብረት መውደሙንም ነዋሪዎች ይገልጻሉ። በተለይ ትናንት ብቻ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል በተነሳው ግጭት ከቦረና ከ12 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከጉጂ ደግሞ 8 ሰዎች ተገድለዋል። ኬንያ ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ
መጋቢት ፲፰ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት ሁለት አመታት ሲካሄድ የቆየው፣ ከቅርብ ወራት ወዲህ ቀዝቀዝ ብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ዛሬ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በአንዋር መስጊድ ተካሂዷል። ሙስሊም ኢትዮጵያዊያኑ አላህ ሰላምን እንዲያመጣ ሲማጸኑ አርፍደዋል። የሰላም ሰዎች መሆናቸውን ነጭ ወረቀቶችን በማውለብለብ ያሳዩ ሲሆን ተቃውሞውም ያለምንም የጸጥታ ችግር ተጠናቋል። መንግስት እንቅስቃሴውን በሃይል እንደተቆጣጠረው ሲያውጅ ቢከርምም ...
Read More »በመርአዊ ከተማ ተጨማሪ አርሶደአሮች እየታሰሩ ነው
መጋቢት ፲፰ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ ጎጃም ዞን በሜጫ ወረዳ በእናሸንፋለን ቀበሌ ከአበባ እርሻና ከውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የሚታሰሩ አርሶደሮች ቁጥር መጨመሩን አካባቢው ሰዎች ገልጸዋል። በወረዳው ዋና ከተማ በመርአዊ ከተማ አሁንም የሚታሰሩ አርሶደአሮች መኖራቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ በተለይ ታዳጊ ወጣቶች ከትምህርት ገበታቸው ተለይተው እንዲታሰሩ መደረጉን ገልጸዋል። የመኢአድ የመርአዊ ተወካይ አቶ ስማቸው ምንችል ሰብአዊ መብት ድርጅቶች ...
Read More »