የደቡብ ሱዳን አማጽያን የነዳጅ ማውጫ ጉድጓዶችን እንደሚቆጣጠሩ አስታወቁ

መጋቢት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ ማህበረሰብ አማጽያኔኑን ከመንግስት ጋር ለማስታረቅ ደፋ ቀና ሲል ቢከርምም ፣ አማጽያኑ ግን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርን ከስልጣን አስገድዶ ለማውረድ ሲሉ የነዳጅ ማውጫ ቦታዎችን ለመቆጣጠር መወሰናቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል።

ነጭ ጦር እየተባለ የሚጠራው ከአማጽያኑ መሪ ሪክ ማቻር ጋር ጥምረት ያለው ቡድን ለመንግስት ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኘውን የ ፓሎችን የነዳጅ ጉድጓዶች ለመቆጣጠር ዝግጅት እያደረ ነው።

ማቻር ” የነዳጅ ጉድጓዶችን በመቆጣጠር የሳልቫኪር መንግስት እንዲወድቅ እናደርገዋለን” በማለት ዝተዋል። ደቡብ ሱዳን በቀን እስከ 150 ሺ በርሜል ነዳጅ በመሸጥ እስከ 15 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ታገኛለች።

የሳልቫኪር መንግስት ለአማጽያኑ ዛቻ የሰጠው መልስ የለም።