ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “መና” የተባለው የግብጽ ዜና አገልግሎት እና “አል አህራምስ” የተባለው የአረብኛ ድረ ገጽ እንደገዘቡት፤ ወደ ሀገራቸው “ዲፖርት” የተደረጉት ኢትዮጰያውያን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ግብጽ በመግባት ወደ እስራኤል ለመሻገር ሲሞክሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ናቸው። ተመላሾቹ ኢትዮጰያውያን ግብጽ ከሱዳን ጋር በምትዋሰንበት ደቡባዊ ድንበር በኩል አድርገው ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ አስዋን ሲገቡ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውን ...
Read More »ብርሃንና ሰላም የጋዜጦችን ይዘት ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ፊርማ አሳታሚዎች እንዲፈርሙ አስገደደ
ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተመሰረተ 92ኛ ዓመቱን የደፈነው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የጋዜጦችን ይዘት ለመቆጣጠር የሚያስችለውን የስምምነት ውል አሳታሚዎች እንዲፈርሙለት አስገዳጅ ሰርኩላር አሰራጭቷል፡ ማተሚያቤቱበማሽንእርጅናምክንያትጋዜጦችንበቀናቸውማተምየማይችልበትደረጃላይየሚገኝሲሆንበዚህምምክንያትጋዜጦችከመውጫቀናቸውከአንድእስከሶስትቀናትዘግይተውበመውጣትላይመሆናቸውንለጉዳዩቅርበትያላቸውወገኖችይገልጻሉ፡፡በዚህምምክንያትአቅምእያዳበሩየመጡጋዜጦችሳይቀርለኪሳራእየተዳረጉየመጡበትሁኔታእየተፈጠረሲሆንአቅምየሌላቸውከገበያለመውጣትእየተገደዱነው፡፡ ማተሚያቤቱባለፈውዓመትየህትመትሥራንበተመለከተየጋራየስምምነትውልይኑረንበሚልያሰራጨውረቂቅገዳቢሕግየጋዜጦችንይዘትአስቀድሞእንዲቆጣጠርዕድልየሚሰጠውናየማይስማማውንጋዜጦችአላትምምለማለትየሚያስችለውበመሆኑበአሳታሚዎችበኩልበተነሳተቃውሞሳይፈረምመቆየቱየሚታወስነው፡፡ በአሁኑወቅትይህንኑ ተቃውሞየገጠመውንውልአሳታሚዎችእንዲፈርሙለት፣ይህካልሆነጋዜጦችንማተምእንደሚያቆምበመግለጽሰሞኑንያሰራጨውደብዳቤበቅርቡበተመሰረተውየአሳታሚዎችማህበርበኩልተቃውሞገጥሞታል፡፡ አሳታሚዎቹከዚህይልቅ ማተሚያቤቱየመንግስትጋዜጦችንካተመበሃላበማሽንተበላሽቶአልስምየግልጋዜጦችበቀናቸውእንዳይወጡየሚያደርገውሃላፊነትየጎደለውአድሎአዊ አሰራርለማረምናአዳዲስማሽኖችንለማስገባትቅድሚያሰጥቶእንዲሠራበመጠየቅላይናቸው፡፡በሁለቱወገኖችበኩልያለውአለመግባባትይህዜናእስከተጠናቀረበትቀንድረስእልባትአላገኘም፡፡ 90 ሚሊዮን ህዝብ በሚኖሩባት ኢትዮጵያጋዜጦችን በተሻለ ሁኔታ ለማተም የሚያስችል ብቸኛው ማተሚያ ቤት ብርሃንና ሰላም ነው።
Read More »የአንበጣ መንጋ በሰሜን ጎንደር አካባቢ መታየቱን ነዋሪዎች ገለጹ
ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያን እየጎበኘ የሚመስለው የአንበጣ መንጋ በደብረ ብርሃን አካባቢ ከታየ በሁዋላ ትናንት እና ዛሬ ሰሜን ጎንደር አካባቢ ባሉ ወረዳዎች መታየቱን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ወቅቱ የሰብል አዝመራ የሌለበት በመሆኑ አንበጣው ጉዳት አለማድረሱን ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል። የአንበጣ መንጋው በአዲስ አበባም የተወሰኑ አካባቢዎች ታይቶ እንደነበር ይታወሳል።
Read More »በአዲስ አበባከ ሚገኙነዋሪዎች መካከል ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ከ70 ሺ በላይ ዜጎች የጎልማሶች ትምህርት ቢያስፈልጋቸውም እያገኙ ያሉት 49ሺ ያህሉ መሆናቸውንከክልሉትምህርትቢሮየተገኘመረጃአመለከተ፡፡
ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጼኃ/ስላሴ ዘመን የፊደል ሰራዊት፣ በዘመነ ደርግ የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ ተብሎ የሚታወቀውና በአሁኑ ወቅት የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት በአዲስ አበባ ደረጃ በ2003 ዓ.ም የተጀመረ ቢሆንም የተማሪውን ፍላጎት ያላማከለ በመሆኑ ውጤታ ማመሆን አልቻለም ፡፡ በነዚህ ወቅቶች አፈጻጸሙ ከ26 እስከ 29 ሺ የነበረ ሲሆን በ2006 ዓ.ም ይህተሻሽሎ ወደ 49 ሺ 272 ጎልማሶችን እንዲማሩ ማድረግ መቻሉን ...
Read More »ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት ቀየ መፈናቀላቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ
ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምእራብ ሸዋ ዞን በዳኖ ወረዳ አጂላ ዳሌ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች ለኢሳት እንደገለጹት ከ19 ዓመታት በላይ ከኖሩበት ቀየ በተለያዩ ሰበቦች ሀብትና ንብረታቸውን ተቀምተው ለቀው እንዲወጡ በመደረጋቸው ቤት አልባ ሆነው ለችግር ተዳርገዋል። “መንግስት በአካባቢው እንድንኖር ፈቃድ ሰጥቶን የሚፈለግብንን ግብር እየከፈልን አካባቢውን ስናለማ ነበር” የሚሉት አርሶ አደሮች፣ ሀብትና ንብረት ካፈራን በሁዋላ ” ...
Read More »የዞንዘጠኝ ጦማርያን ተጨማሪጊዜተጠየቀባቸው።
ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እሁድ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የ 28 ቀናት ቀጠሮ የተጠየቀባቸው የዞን 9 ጦማርያን ማህሌትፋንታሁን፣አቤልዋበላናበፍቃዱኃይሉ ናቸው። ጦማርያኑ የዛሬ አስራ አምስት ቀን ፍርድ ቤት ቀርበው ፖሊስ ተጨማሪ የ28 ቀን ቀጠሮ ሲጠይቅባቸው በመሀል ዳኛዋ ውድቅ ተደርጎ የ15 ቀናት ቀጠሮ መሰጠቱ አይዘነጋም። ይሁንና ችሎቱ ከትናንት በስቲያ እሁድ በአራዳ ምድብ ችሎት ሢሰየም ውሳኔውን ያሳለፉት ዳኛ ከቦታው እንዲነሱ ...
Read More »ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን እንደቻለች ተደርጎ መገለጹ አነጋጋሪ ሆኗል
ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የግንቦት 20 በዓል በተከበረበት ወቅት ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በምግብ ሰብል እህል ምርት ራሱዋን መቻሉዋን ተናግረዋል። ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የዋና ዋና ምግብ ሰብሎች ምርት በ2002 ከነበረበት 202 ሚሊየን ኩንታል፣በ2005 ዓ.ምወደ 251 ሚሊየንኩንታልቢያድግምከሚጠበቀውአንጻርእድገቱዝቅተኛመሆኑንይጠቅሳል ፡፡ይህምጠ/ሚኒስትሩ በምግብ ራሳችንችለናልከሚልገለጻቸውጋርየሚጋጭ ሲሆን ኢህአዴግ በባህርዳር ከተማ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ጉባኤ የሰብል ልማት በእድገት ...
Read More »የአሜሪካ ኢምባሲ ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ
ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢምባሲው ማስጠንቀቂያውን ያወጣው አልሸባብ በኢትዮጵያ እና በምእራባዊያን ተቋማት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ፍላጎቱና ችሎታው እንዳለው ተጨባጭ መረጃ እንደደረሰው ከጠቀሰ በሁዋላ ነው። በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢ የሰዎች ምልልስ ተጠናክሮ መቀጠሉን የጠቀሰው ኢምባሲው፣ ጥቃቱ የሚፈጸምበት ቦታና ሰአት በትክክል ባይታወቅም፣ የአሜሪካ ዜጎች የምእራባዊያን ዜጎች በሚሰበሰቡበት በሆቴሎች፣ በምግብ ቤቶች፣ በመጠጥ ቤቶችና በገበያ አዳራሾችና በአምልኮ ቦታዎች ላይ ሁሉ የግል ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በኑር መስኪድ ደማቅ ተቃውሞ አደረጉ
ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሙስሊም የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት በፍትህ እጦት በእስር ቤት መሰቃየት መቀጠላቸውን በመቃወም በአዲስ አበባ በኑር መስጊድ በተደረገው ተቃውሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ መገኘቱን ዘጋቢያችን ገልጻለች። ድምጻችን ይሰማ ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ የተቃውሞው ዋና አላማ የሙስሊሙን ህዝብ ጥያቄ አንግበው በመያዛቸው በእስር እየተሰቃዩ ለሚገኙት መሪዎች ድጋፍ ለመግለጽ ነው መሆኑን ጠቅሷል። በዘገየ ፍትህና በችሎት ...
Read More »ታፍኖ የተወሰደው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ማእከላዊ መታሰሩ ታወቀ
ግንቦት ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቀናት በፊት ከትምህርት ገበታው ታፍኖ ተወስዶ የነበረው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ አመት ተማሪ እና የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነው መልካሙ አምባቸው በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ መታሰሩ ታወቀ። በጎንደር ምዕራብ አርማጨሆ ነዋሪ የሆነውና በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ የአካውንቲግ 1ኛ ዓመት ተማሪ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአንድነት መዋቅር ስራአስፈጻሚ አባል የሆነው ወጣት መልካሙ አምባቸው ...
Read More »