የአንበጣ መንጋ በሰሜን ጎንደር አካባቢ መታየቱን ነዋሪዎች  ገለጹ

ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያን እየጎበኘ የሚመስለው የአንበጣ መንጋ በደብረ ብርሃን አካባቢ ከታየ በሁዋላ ትናንት እና ዛሬ ሰሜን ጎንደር አካባቢ ባሉ ወረዳዎች መታየቱን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

ወቅቱ የሰብል አዝመራ የሌለበት በመሆኑ አንበጣው ጉዳት አለማድረሱን ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል።

የአንበጣ መንጋው በአዲስ አበባም የተወሰኑ አካባቢዎች ታይቶ እንደነበር ይታወሳል።