መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቡዕ እለት በአዋሳ ብሉ ናይል እየተባለ የሚጠራው ሆቴል ባለቤት የሆኑት አቶ ታምራት ፣ ድርጅታቸው እንዲሸጥ በፍርድ ቤት ውሳኔ ማተላለፉን ተከትሎ፣ ውሳኔው እንዲተላለፍ አድርጓል ባሉት ወጣት ጠበቃ ዳንኤል ላይ የግድያ ሙከራ አድርገው ተሰውረዋል። አቶ ታምራት ከአንድ ግለሰብ ጋር ባላቸው የገንዘብ ውዝግብ በመረታታቸው ሆቴላቸው እንዲሸጥ ምክንያት መሆኑን ምንጮች ሲገልጹ፣ ባለሀብቱ የመንግስት ታክስ አልከፈሉም ተብለው ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኙ ወረዳዎች በመሰረተ ልማት በከፍተኛ ደረጃ ወደ ኋላ መቅረታቸውን የወረዳ አመራሮች በግልጽ በማቅረባቸው ከክልልና ዞን ባለስልጣናት ግሳጼ እንደደረሰባቸው ተናገሩ፡፡
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር ዩኒቨርስቲ አመታዊ የተማሪዎች ምረቃ በዓል ብቅ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማርያም ደሳለኝ ህብረተሰቡ ምን ይለናል የሚለውን ለማዳማጥ ከሰሜን ጎንደር ከተሰባሰቡ የወረዳ አመራሮች ጋር ባደረጉት ድንገተኛ ስብሰባ የወረዳ አመራሮች በንባብ እንዲያሰሙት ከየዞን ሃላፊዎች የተሰጣቸውን ማስታወሻና አቅጣጫ ወደጎን በመተው መንግስት እንዲያስተካክላቸው በጠየቁዋቸው ጥያቄዎች ምክንያት ከስብሰባው በኋላ ወከባና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ ለከፍተኛ አመራሮች ...
Read More »“ሰራዊታችን ህብረብሄር ሆኗል” ሲል ኢህአዴግ ገለጸ
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“የመከላከያ ሰራዊቱ ያዛዥነት ቦታዎች በአንድ ብሄር ቁጥጥር ስር ነው” በሚል ተደጋጋሚ ትችት የሚደርስበት ኢህአዴግ፣ ሰራዊቱን ህብረብሄራዊ ማድረጉን ገለጸ። የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች እንዲወያዩበት ተብሎ በኢህአዴግ የተዘጋጀው ሰነድ የትምክት ሃይሎች ” በአገራችን የአንድ ብሄር የበላይነት ያለ ለማስመሰል የማያደርጉት ሙከራ የለም” ካለ በሁዋላ፣ ሰራዊታችን በህገ መንግስቱ መሰረት የተዋቀረ ህብረብሄራዊ ሰራዊት ሆኖ እያለና በመጀመሪያዎቹ አመታት ከትግሉ ...
Read More »ነዋሪዎች የፕሬዚዳንቱን ሪፖርት ተቃወሙ
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ መስከረም 26 ቀን 2007 ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክርቤቶች መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር በአዲስአበባ ባለፈው ዓመት 22ሺ ያህል የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል የሚል ሪፖርት ማቅረባቸው ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓመት በሰኔ ወር በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት 22ሺ ያህል ቤቶች ቀደም ሲል ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች መተላለፉን አስተዳደሩ ይፋ ከማድረጉም በላይ ...
Read More »ማህበረ-ቅዱሳን አደጋ አንዣቦበታል።
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-‹ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠረው ማኅበር ጽንፈኛና አሸባሪ የመሆን ዕድሉ የሰፋ ነው››ሲሉ የኢትዮፐያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ተናሩ። ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ይህን ያሉት ፡ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልፀግ›› በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መስብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረውን ጉባዔ በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግልጽ ...
Read More »በአማራ ክልል የተደራጁ የጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት መክሰራቸውን አስታወቁ
መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጥቃቅን እና አነሰተኛ ተደራጅተው ፤በየቀኑ ላባቸውን እያፈሰሱ የሚደክሙ የድሃ ድሃ እናቶች እለቅሶ ርቆ እየተሰማ መሆኑን የክልሉ ዘጋቢያችን ነጋዴዎችን አነጋግራ የሰራቸው ዘገባ ያመለክታል 33 በእድሜ የገፉ እናቶች ” በመንግስት ሌቦች ተዘርፈናል ሲሉ ” እያለቀሱ ብሶታቸውን ገልጸዋል። በአማራ ክልል በስራ አጥ እና የድሃ ድሃ ከተደራጁ 31 ሺ 549 ማህበራት ውስጥ 29 ሺ 572 ሳይጀመሩ ...
Read More »በአሜሪካ ሁለት የተለያዩ ተቃውሞች ተካሄዱ
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተቃውሞ ለማሰማት በሄዱ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰው ሰለሞን ገብረስላሴ፣ በ48 ሰአታት ውስጥ ከአሜሪካ እንዲወጣ ከተደረገ በሁዋላ የመንግስት ደጋፊዎች የአሜሪካን እርምጃ ለመቃወም የጠሩትን ተቃውሞ ለማክሸፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም ተመሳሳይ ተቃውሞ አዘጋጅተዋል። የመንግስት ደጋፊዎች አሜሪካ ለኢምባሲው በቂ ጥበቃ አላደረገችም በሚል ሲቃወሙ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ደግሞ የአሜሪካን እርምጃ ደግፈዋል። የአሜሪካ ...
Read More »አቶ በረከት ስምኦን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪዎችን ማሰልጠናቸውን ቀጥለዋል
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላው አገሪቱ ለሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለመንግስት ሰራተኞች እና ለኢህአዴግ አባላት የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና የዩኒቨርስቲ መምህራንም እንዲወስዱ በመገደዳቸው፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን በቀድሞው የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር እና በአሁኑ የጠ/ሚ የፖሊሲ አማካሪ በአቶ በረከት ስምኦን እንዲሰለጥኑ እየተደረገ ነው። ስልጠናውን የሚወስዱት በታሪክ፣ በፖለቲካል ሳይንስ፣ በሶሺኦሎጂ፣ በጆግራፊ፣ በፊዚክስ እና በመሳሰሉት የትምህርት ዘርፎች የፕሮፌሰርነት ማእረግ ያገኙ፣ የተለያዩ ጥናታዊ ...
Read More »የመካከለኛው ምስራቅ እና የምእራብ አገሮች በኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖታዊ ሽኩቻ እንዲፈጠር እንደሚፈልጉ ማረጋገጥ ተችሎአል ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠ/ሩ የፖሊሲ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ስልጠና በመውሰድ ላይ ላሉ የዩኒቨርስቲ መምህራን ነው። አቶ በረከት በምእራባውያን እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ገንዘብ በሃይማኖት ስም የፖለቲካ አላማ ለማራመድ በሚል ወጪ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ በረከት በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ትርምስ እንዲፈጠር ይፈልጋሉ ያሉዋቸውን የምእራብና መካከለኛው ምስራቅ አገራት በስም ...
Read More »የጎንደር ዩኒቨርስቲ የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተመራቂ ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲው ዲን በደመወዝ ከፍያ ምክንያት ባለመግባባታቸው ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መሆናቸውን ከአካባቢው የተገኙ ምንጮች አመለከቱ፡፡
መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው እስከ 200 የሚደርሱ የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪዎች በመመረቂያ አመታቸው ላይ እንዳሉ ሲመረቁ የሚከፈላቸውን የደመወዝ ግማሽ የሚከፈላቸው ሲሆን የውዝግቡ ዋነኛ ምክንያት የሚከፈላቸው ግማሽ ክፍያ በአዲሱ የደመወዝ ጭማሪ መሰረት አለመሆኑ ነው፡፡ የህክምና ተማሪዎቹ ለአካባቢው አመራሮች ቅሬታቸውን አቅርበው የፓለቲካ አመራሮቹ “ቅሬታችሁ ተገቢ ነው” የሚል መልስ ቢሰጡዋቸውም የዩኒቨርስቲው ዲን ተማሪዎቹን “አመጸኞች ናችሁ፣ብጥብጥ ለማስነሳት አስባችኋል” በሚል ...
Read More »