በአሜሪካ ሁለት የተለያዩ ተቃውሞች ተካሄዱ

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ አሜሪካ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተቃውሞ ለማሰማት በሄዱ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥይት የተኮሰው ሰለሞን ገብረስላሴ፣  በ48 ሰአታት ውስጥ ከአሜሪካ እንዲወጣ ከተደረገ በሁዋላ የመንግስት ደጋፊዎች

የአሜሪካን እርምጃ ለመቃወም የጠሩትን ተቃውሞ ለማክሸፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም ተመሳሳይ ተቃውሞ አዘጋጅተዋል። የመንግስት ደጋፊዎች አሜሪካ ለኢምባሲው በቂ ጥበቃ አላደረገችም በሚል ሲቃወሙ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ደግሞ የአሜሪካን እርምጃ ደግፈዋል።

የአሜሪካ መንግስት የዲፕሎማቲክ ከለላ ያለውን የደህንነት ሰራተኛ ከአገር ካባረረ በሁዋላ ኢትዮጵያ አጸፋዊ እርምጃ ሳትወስድ ፣ ውሳኔውን ለመቀበል ተገዳለች። የኢትዮጵያ መንግስት ዝምታ እንደ ትልቅ የዲፐሎማሲ ሽንፈት እንደሚቆጠር በማህበራዊ ድረገጾች ላይ የሚሰጡ

አስተያየቶች ያመለክታሉ።