በአማራ ክልል የተደራጁ የጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራት መክሰራቸውን አስታወቁ

መስከረም ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጥቃቅን እና አነሰተኛ ተደራጅተው ፤በየቀኑ ላባቸውን እያፈሰሱ የሚደክሙ የድሃ ድሃ እናቶች እለቅሶ ርቆ እየተሰማ መሆኑን የክልሉ ዘጋቢያችን ነጋዴዎችን አነጋግራ የሰራቸው ዘገባ ያመለክታል

33 በእድሜ የገፉ እናቶች ” በመንግስት ሌቦች ተዘርፈናል ሲሉ ” እያለቀሱ ብሶታቸውን ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በስራ አጥ እና የድሃ ድሃ ከተደራጁ 31 ሺ 549 ማህበራት  ውስጥ 29 ሺ 572 ሳይጀመሩ ፈርሰዋል፡፡በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስትን ባለስልጣናት አስተያየት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም።