የመካከለኛው ምስራቅ እና የምእራብ አገሮች በኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖታዊ ሽኩቻ እንዲፈጠር እንደሚፈልጉ ማረጋገጥ ተችሎአል ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠ/ሩ የፖሊሲ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ስልጠና በመውሰድ ላይ ላሉ የዩኒቨርስቲ መምህራን ነው።

አቶ በረከት በምእራባውያን እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ገንዘብ በሃይማኖት ስም የፖለቲካ አላማ ለማራመድ በሚል ወጪ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። አቶ በረከት በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ትርምስ

እንዲፈጠር ይፈልጋሉ ያሉዋቸውን የምእራብና መካከለኛው ምስራቅ አገራት በስም አልጠቀሱም። አቶ በረከት ሰማያዊ ፓርቲ የአክራሪ ሃይሎችን በመደገፍ የፖለቲካ አላማውን ለማራመድ ያስባል በማለት ወቀሳ አቅርበዋል።