የጎንደር ዩኒቨርስቲ የመጨረሻ ዓመት የህክምና  ተመራቂ ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲው ዲን በደመወዝ ከፍያ ምክንያት ባለመግባባታቸው ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መሆናቸውን ከአካባቢው የተገኙ ምንጮች አመለከቱ፡፡

መስከረም ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው እስከ 200 የሚደርሱ የመጨረሻ ዓመት የህክምና  ተማሪዎች በመመረቂያ አመታቸው ላይ እንዳሉ ሲመረቁ የሚከፈላቸውን የደመወዝ ግማሽ የሚከፈላቸው ሲሆን የውዝግቡ ዋነኛ ምክንያት የሚከፈላቸው

ግማሽ ክፍያ በአዲሱ የደመወዝ ጭማሪ መሰረት አለመሆኑ ነው፡፡ የህክምና ተማሪዎቹ ለአካባቢው  አመራሮች  ቅሬታቸውን አቅርበው የፓለቲካ አመራሮቹ “ቅሬታችሁ ተገቢ ነው” የሚል መልስ ቢሰጡዋቸውም የዩኒቨርስቲው ዲን  ተማሪዎቹን “አመጸኞች ናችሁ፣ብጥብጥ

ለማስነሳት አስባችኋል” በሚል   እያስፈሯሯቸው እንደሆነ ለማዎቅ ተችሎአል፡፡