ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡዕ 200 ኢትዮጵያውያንን የጫኑ 2 ጀልባዎች ከ24 ሰአታት የባህር ላይ ጉዞ በሁዋላ ጅቡቲ በሰላም ደርሰዋል።ኢትዮጵያውያኑ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ወደ አዲስ አበባ ይጓጓዛሉ። በየመን አሁንም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። በአገሮቱ ከሚኖሩት ከ80 ሺ በላይ ስደተኞች መካከል ወደ አገራቸው ለመመለስ ፍላጎት ያሳዩት ከ2 ሺ አይበልጡም። በየመን ያለውን ጦርነት ...
Read More »በቴፒው ግጭት በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን መረጃዎች አመለከቱ
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የቴፒ ወጣቶች ቡድን በአንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ የወሰደውን ድንገተኛ ጥቃት ተከትሎ ሶስት ፖሊሶች ከተገደሉና በርካታ እስረኞች ካመለጡ በሁዋላ፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ታጣቂዎች መሽገውበታል ወዳለው አካባቢ በመሄድ ውጊያ የከፈቱ ሲሆን፣ ወጣት ታጣቂዎች አስቀድመው ዝግጅት አድርገው በመቆየታቸው በርካታ ወታደሮች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል። የኢሳት ምንጮች እንደሚሉት በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲሆኑ፣ ቀላል የመቁሰል ...
Read More »የዋጋ ግሽበት እየጨመረ መሄዱን የመንግስት መረጃ አመለከተ
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማእከላዊ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት በወጣው መረጃ በዚህ አመት የታየው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ7 በመቶ ጭማሪ ሲያሳያስ ፣ የምግብ ያዋጋ ግሽበት 6.9 በመቶ ምግብ ነክ ያልሆኑ ደግሞ 8 .2 በመቶ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል። በዚህ አመት በግንቦት ወር የታየው የዋጋ ግሽበት አምና ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ9.4 ከፍ ብሎአል። የግንቦት ወር 2007 ...
Read More »የቀድሞው የአንድነት አመራር ለ3ኛ ጊዜ የዋስትና ገንዘብ አቅረበ
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው አቶ ዳዊት አስራደ ሰኔ 3/2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ በ5 ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ ዋስትና የተፈቀደለት ቢሆንም ገንዘቡን ካስያዘ በኋላ ዋስትናው እንደተነሳ ተነግሮት በእስር ላይ እንዲቆይ ተደርጓል። ፖሊስ አቶ ዳዊትና ሌሎች ተከሳሾች ምስክሮችን ያባብሉብኛል በሚል ለ14 ቀን ታስረው እንዲቆዩ ቀጠሮ ጠይቆ የነበር ቢሆን ፍርድ ...
Read More »ኢህአዴግ በምርጫው አገኘሁት ያለውን ውጤት ለማብሰር የያዘውን የድጋፍ ሰልፍ እቅድ በፍርሃት ሰረዘ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ለመላ አገሪቱ በወረደ ጊዚያዊ አደረጃጃት፣ በመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንዲሁም በተለያዩ የግንባሩ ጽ/ቤቶች በተሰጠ መመሪያ መሰረት የተዋቀረው የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ኮሚቴ የድጋፍ ሰልፍ የማድረግ እቅዱን ሰርዟል። ምርጫው ፍጹም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መሆኑን ህዝቡ በድጋፍ እንዲመሰክር እና ሚዲያዎቹ በቀጥታ እንዲዘግቡት መመሪያ ከወረዳ በሁዋላ፣ የኢህአዴግ ምክር ቤት ተሰብስቦ ሰላማዊ ሰልፉ እንዲደረግ አይመከርም ሲል በሙሉ ...
Read More »የደህንነት ተቋማት ከፍተኛ በጀት ተመደበላቸው
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ2008 ዓም ከመደበው በጀት ውስጥ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ ፍትህና ደህንነት ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸዋል። የፌዴራል መንግሥት የመደበኛ ወጪ ዝርዝር እንደሚሳየው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 9. 5 ቢሊየን ብር፣ የፌዴራል ፖሊስ 1. 6 ቢሊየን ብር፣ ፍትሕና ደህንነት 3. 5 ቢሊየን ብር ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸዋል፡፡ መከላከያ በ2007 ዓም ከተያዘለት በጀት ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው በጀቱ ...
Read More »ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ሪፖርት አጣጣለችው
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በኤርትራ ይፈጸማሉ ያላቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይፋ እንደሚያደርግ ካስታወቀ በሁዋላ፣ ኤርትራ መልስ ሰጥታለች። የድርጀቱ ሪፖርት በሃሰት የተሞላና ነው ያለው የኤርትራ መንግስት መግለጫ፣ ድርጅቱ ጥቃቱን የሰነዘረው በመንግስት ላይ ሳይሆን ለሰው ልጅ ክብርና ማንነት ከፍተኛ ከበሬታ በሚሰጠው ስልጡን በሆነው ማህበረሰብና ህዝብ ላይ ነው ብሎአል። የኤርትራ መንግስት “የተባበሩት መንግስታት ...
Read More »የኢኮኖሚው መሰረት ነው የተባለው የውጭ ንግድ መክሸፉን ሚኒስትሩ በይፋ ተናገሩ
ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ከአምስት አመት በፊት አውጥቶት በነበረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከወጪ ንግድ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰበስብ ገልጾ ነበር፣ ይሁን የገንዘብ ሚኒስትሩ ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት የታቀደው እቅድ አለመሳካት ብቻ ሳይሆን የውጭ ንግዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መሄዱን ገልጸዋል። አቶ ሱፊያን አህመድ የ2008 በጀት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በፓርላማ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በውጭ ንግድ የትራንስፎሜሽን እቅዱ አልተሳካም ብለዋል። ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ የአባሎቹ መታሰር እንዲቆም ጠየቀ
ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም አረመኔው የአይ ኤስ አይ ኤስ ቡድን በዜጎቻችን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ በራሱ በመንግስት ላይ ተቃውሞ ያሰሙ ዜጎችን በእለቱ በአሰቃቂ ሁኔታ በኃይል ከመደብደብና ከማዋከቡም በተጨማሪ አልፎ ተቃውሞ አነሳስተውብኛል ብሎ ያሰባቸውን በቦታው ያልተገኙ ዜጎችን ጨምሮ ስጋት አድርጎ የሚቆጥራቸውን ...
Read More »የደቡብ ሱዳን ተደራዳሪዎች በአዲስ አበባ ውይይት ጀመሩ
ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሁለት አመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀሩት የደቡብ ሱዳን ግጭት ከዛሬ ነገ መፍትሄ ይፈለግለታል ቢባልም እስካሁን ጦርነቱን የሚያስቆም መፍትሄ ሊገኝ አልቻለም። በቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ዋና መሪነት ሲካሄድ የነበረው ድርድር ለወራት ከተቋረጠ በሁዋላ እንደገና ለማስጀመር የሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች ተወካዮች አዲስ አበባ ገብተዋል። ቀድም ብሎ በተቀመጠው እቅድ መሰረት የፊታችን ሃምሌ ወር ...
Read More »