ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ የወሰነላቸው አቶ ማሙሸት አማረ በ ፖሊስ እምቢተኝነት ተመልሰው ታሰሩ

ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምርጫ ቦርድ ትእዛዝ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ፣ ግንቦት 25/2007 ዓም ፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቁ ቢወስንም ፣ ፖሊስን ግን መልሶ አስሯቸዋል። አቶ ማሙሸት ሚያዚያ 14፣ 2007 በአይ ኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን በማስመልከት ድርጊቱን ለማውገዝና ኢትዮጵያውያኑንም ለመዘከር በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የታየውን ረብሻ አደራጅተዋል በሚል ...

Read More »

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኦርቶዶክስ አማኞች ከዩኒቨርስቲ አስተዳደሩ ጋር እየተወዛገቡ ነው።

ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውዝግቡ መነሻ ተማሪዎች የሰኔ ጾምን ለመጾም በመፈለግ ዩኒቨርሲቲው የጾም ምግብ እንዲያዘጋጅላቸው በመጠየቃቸውና ዩኒቨርስቲው ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ነው፡፡ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ተማሪዎች ላቀረቡት ጥያቄ ዳቦ እየበላችሁ መጾም ትችላላችሁ የሚል መልስ ሰጥቷቸዋል። ዩኒቨርሲቲው ለስጋ የሚወጣውን በጀት ለሽሮ ቢወጣ ይቀንስ እንደሆን እንጂ ተጨማሪ ወጪ አያስከትልበትም ያሉት ተማሪዎቹ በግዳጅ እምነታችንን እንድንተው መደረጉ አስቆጥቶናል ብለዋል፡፡ በዩኒቨርስቲው አስተዳደርና ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት 7 በሜልቦርን አውስትራሊያ የተሳካ የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት አካሄደ

ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 3 ሳምንታት በአውስትራሊና ኒውዚላንድ የተለያዩ ከተሞች የገንዘብ ማሰባሰብ ዘመቻ በማድረግ ላይ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 ባለፈው ዕሁድ ሜይ 31ቀን በሜልበርን ከተማ የተሳካ የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ማካሄዱን ሃና ጋረደው ከስፍራው ከላከችልን ሪፖርት ለመረዳት ተችሎአል በርካታ የሜልበርንና አካባቢዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በዚህ ታላቅ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄን በመወከል የንቅናቄው ...

Read More »

ተጨማሪ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይል ወደ ሶማሌ ክልል መሰማራቱ ተገለጸ

ኢሳት ዜና (ግንቦት 25, 2007) በኢትዮጵያና ጎረቤት ሶማሊያ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰዉን ግጭት ተከትሎ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወታደራዊ ሃይል ወደስፍራው ማሰማራቷ ተገለፀ። በእስካሁኑ የኢትዮጵያ ልዩ ሃይሎችና በሶማሊያ የጎሳ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደዉ ግጭት በትንሹ ከ50 በላይ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፤ የሶማሊያ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ የፀጥታ ሃይሎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል ሲሉ ተቃዉሞ ማሰማታቸውን ሶማሊ ከረትን የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። የጋልጋይዱድ ክልል ሃላፊ የሆኑት ሁሴን አርፎ የኢትዮጵያ ...

Read More »

ከኬንያ ተጠልፈው የነበሩት ሁለቱ የኦብነግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ወደ ናይሮቢ ተመለሱ

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ከኬንያ ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ ተወስደው የነበሩት አቶ ሱሉብ አብዲ አህመድና አቶ አሊ አህመድ ሁሴን ትናንት ምሽት ኬንያ ናይኖቢ መግባታቸውን ለኢሳት ደረሰው መረጃ አመልክቷል። ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች በምን ሁኔታ ወደ ናይኖቢ እንደተመለሱ የታወቀ ነገር የለም። የድርጅቱ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አብድረህማን ሼህ ማህዲ የመሪዎቹን ወደ ናይሮቢ ...

Read More »

የመንግስትና የፖሊስን መልካም ስም አጥፍተዋል የተባሉ ወጣቶች ተፈረደባቸው

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን ዘግናኝ እርምጃ ለማውገዝ በተጠራ ሰልፍ ላይ የመንግስትንና የፖሊስን ስም አጥፍተዋል የተባሉ ወጣቶች በእስርና በገንዘብ ተቀጥተዋል። አስማማው ወልዴ፣ የማነ ወርቅነህ፣ ስንታየሁ ታሪኩ፣ ያሲን ቃሲምና ይግረማቸው አበበ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓም ጠ/.ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ጠ/ሚኒስትሩን መሳደባቸውን በክሱ ላይ ...

Read More »

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች አዲስ የተረቀቀውንና የፕሮቪደንት ፈንድ የሚያሳጣቸውን ሕግ በመቃወም ገንዘባቸውን እያወጡ ነው።

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅን በማሻሻል ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ፕሮቪደንት ፈንድ ሲያጠራቅሙ የቆዩ የግል ሠራተኞችን በጡረታ እንዲታቀፉ በማድረግ ሰበብ ፕሮቪደንት ፈንዳቸውን ለመውረስ የሚያስችል ሕግ ሰሞኑን ለፓርላማ መቅረቡ ከተሰማ ወዲህ በርካታ ሠራተኞች ከአሰሪዎቻቸው ጋር በመነጋገር ገንዘባቸውን ሕጉ ከመተግበሩ በፊት እያወጡ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡ ፓርላማው የቀረበለት የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 715/2003 ...

Read More »

በአማራ ክልል የጀልባ አገልግሎት ሰጪ ነጋዴዎች ለረዢም ጊዜ በመታገዳቸው ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ

ግንቦት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጣና ሃይቅ ላይ በቱሪስት ጀልባ ትራንስፖርት የሚያገለግሉ የጀልባ ባለሃብቶችና ካፒቴኖች፣ “የአማራ ክልል ንግድና ትራንስፖርት ቢሮ ‘ህገ ወጥ’ ናችሁ በሚል ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ አስራ ሰባት ጀልባዎችን ከሶስት ወር በላይ በማሰሩ ቤተሰቦቻቸውንና ራሳቸውን ለማስተዳደር መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡ ሶስት መቶ ያህል ቤተሰብ የሚያስተዳድሩት ቅሬታ አቅራቢዎች ፣ ለአመታት በስራው ላይ ሲቆዩ በደንበኞች ዘንድ ታማኝነትን ከማትረፋቸውም በላይ ...

Read More »

የመንግስት ወታደሮች በሞያሌና በኦጋዴን ሃይላቸውን እያጠናከሩ ነው

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሁለት ሳምንታት የኢትዮጵያ እና የኬንያ ድንበር የተለያዩ ግጭቶችን አስተናግዷል እንደ አይን ምስክሮች ገለጻ። ዩኒፎርም የለበሱ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ኬንያ በመግባት የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር አባላትን ለማደን ቢሞክሩም እስካሁን አልተሳካላቸውም። የመንግስት ወታደሮች ወደ ኬንያ ሞያሌ ከተማ በመግባት ቦሩ ሁካ የተባለ የ55 ዓመት የትምህርት ቤት ዘበኛ በጥይት በሳስተው ገድለውታል። ነዋሪዎች የኦነግ አባላት ...

Read More »

ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር አብራችሁዋል በሚል የተያዙት ክስ ተመሰረተባቸው

ግንቦት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን ማክሰኝት ከተማ ነዋሪ መሆናቸው የተነገረው አቶ ዘመነ ምህረቱ እና ሌሎች የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሰረታባቸው ሪፖርተር ዘግቧል። አቶ ዘመነ የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት መሆናቸው በክሱ የተመለከተ መሆኑን የዘገበው ጋዜጣው፣ መስከረም 18፣ 2007 ዓም በጎንደር በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት ውስጥ አባላትን በመሰብሰብ ” የወያኔ መንግስት መውደቂያው ደርሷል። አንድ የቶር አውሮፕላን፣ ...

Read More »