በጅማ ዩኒቨርሲቲ የኦርቶዶክስ አማኞች ከዩኒቨርስቲ አስተዳደሩ ጋር እየተወዛገቡ ነው።

ግንቦት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውዝግቡ መነሻ ተማሪዎች የሰኔ ጾምን ለመጾም በመፈለግ ዩኒቨርሲቲው የጾም ምግብ እንዲያዘጋጅላቸው በመጠየቃቸውና ዩኒቨርስቲው ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ነው፡፡
የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ተማሪዎች ላቀረቡት ጥያቄ ዳቦ እየበላችሁ መጾም ትችላላችሁ የሚል መልስ ሰጥቷቸዋል። ዩኒቨርሲቲው ለስጋ የሚወጣውን በጀት ለሽሮ ቢወጣ ይቀንስ እንደሆን እንጂ ተጨማሪ ወጪ አያስከትልበትም ያሉት
ተማሪዎቹ በግዳጅ እምነታችንን እንድንተው መደረጉ አስቆጥቶናል ብለዋል፡፡ በዩኒቨርስቲው አስተዳደርና በተማሪዎች መካከል ያለው ውዝግብ እስካሁን አልተፈታም።