የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር የትግሉን ሜዳ ተቀላቀለ

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 13 2007 አም) የበክኔል ዩኒቭርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑትና በቅርቡ ከዚሁ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማእረግ የተቀበሉት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በሳምንቱ መጨረሻ ኤርትራ መግባታቸው በኢትዮጵያውያን ዘንድ አብይ መነጋገሪያ ሆኖ ወጥቷል ፤ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የመሪውን ትግል ቦታ መሄድ ይፋ በማድረግ ኢትዮጵያውያን በአቅማቸው መጠን በትግሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል። “እነሆ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ድ/ር ብርሀኑ ነጋ በአካል ...

Read More »

አስራ አራት የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ፕ/ት ኦባማ ኬንያና ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት መሻሻል እንዲያደርጉ ጠየቁ

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቶቹ ለፕ/ት ኦባማ በጻፉት ደብዳቤ ኬንያና ኢትዮጵያ በብሄራዊ ደህንነት ስም የሚያደርሱት የሰብአዊ መብት ረገጣ ፣ አለማቀፍ ህግጋትን መጣስ ብቻ ሳይሆን፣ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት አደጋ ውስጥ እንደሚጥለው ገልጸዋል። ደብዳቤውን የጻፉት፣ አትላንታ ካውንስል፣ ካውንስል ኦን ፎሬን ሪሌሽን፣ ሂውማን ራይትስ ፈርስት፣ ከኒይ ግራጅዌት ሴንተር እና ሲቲ ኮሌጅ ኦፍ ኒዮርክ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የማኬን ኢንስቲቲዩት ...

Read More »

ፍርድ ቤቱ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን እንዲያቀርብ ቀጠሮ ሰጠ

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ድረስ ለተጠቀሱት ተከሳሾች የመከላከያ ምስክር ሆነው አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲቀርቡ ሲል የልደታ ፍርድ ቤት 19 ኛው የወንጀል ችሎት ወሰነ፡፡የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በምስክርነት እንዲያቀርብ ሲል ፍርድ ቤቱ ለሀምሌ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥትዋል። አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ሀምሌ 13 ቀን 2007 ...

Read More »

በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪ ደላሎች ታግተው ገንዘብ እንደሚጠየቁ ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም አስታወቀ

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም በየመን አድርገው በሕገወጥ መንገድ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመግባት ሲሞክሩ በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች ታግተው የአካልና የሞራል ጉዳት የደረሰባቸውን ቁጥራቸው 3 ሺ 478 የሚሆኑ በጎፈቃደኛ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው መመለሱን አስታውቀዋል። የ18 ዓመቱ ወጣት አልማይ ፍፁም ”በመኪና ተጭነን ወደ ሳዑዲ ድንበር እንደተቃረብን ፤ መሳሪያ ያነገቡ ታጣቂዎች ወደ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛ ሆኖ፣ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ሥራ ሠርቷል ማለት እንደማይቻል የቀድሞ ኮሚሽነር አስታወቁ

ሐምሌ ፲፭ (አስራአምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉት አቶ ጌታሁን ካሳ ”የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት ተቋም ሚናውና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ላይ ይጋጠሙት ፈተናዎች” በተሰኘ ጥናታዊ የምርምር ሥራቸው ላይ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተቋም ነፃና ገለልተኛ ሆኖ፣ የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አኳያ ውጤታማ ሥራ ሠርቷል ማለት እንደማይቻል አመልክተዋል፡፡አቶ ጌታሁን ኮሚሽኑ ሰብዓዊ መብትን ለማስተዋወቅና ...

Read More »

በምስራቅ እዝና በሃረሪ ክልል ፖሊሶች መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት እንደ አዲስ ባገረሸው የምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የሃረሪ ክልል ፖሊሶች ግጭት 4 ፖሊሶች በመከላከያ አባላት ታፍነው መወደሳቸውንና እስካሁን የደረሱበት አለመታወቅን የሃረር ወኪላችን ገልጿል። የክልሉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ከሁለቱ ሃይሎች የተውጣጡ መሪዎችን ለማነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም። በሃረሪ ፖሊስና በምስራቅ እዝ የፖሊስ አባላት መካከል ያለው ግጭት የቆየ ሲሆን ፣ አንድ አንድ ...

Read More »

በአርባምንጭ ግንቦት7 ገብቷል በሚል ስጋት ህዝቡ ሲፈተሽ ዋለ

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርባምንጭ ምንጮች እንደገለጹት ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ፖሊስ አባላት በየአንዳንድ ኪሎ ሜትር ርቀት ፍተሻ ሲያደርጉ የታየ ሲሆን፣ አንዳንድ ሰዎች ላቀረቡት ጥያቄ የተሰጣቸው መልስ ” ግንቦት7″ ከተማው ውስጥ ገብቷል የሚል ነው። በከተማውና በዙሪያ ወራዳዎች የሚታየው ፍተሻና ቁጥጥር መጨመሩን ፣ ህዝቡም ግራ ተጋብቶ እንደሚገን ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ባለፈው ቅዳሜ የጋሞን ...

Read More »

የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጠበቃ የሆኑት ለደንበኞቻቸው ያቀረቡት መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ ከ1 እስከ 6ኛ እንዲሁም የ9ኛ ተከሳሽ ጠበቃ የሆኑት አቶ ተማም አባቡልጉ በደንበኞቻቸው ላይ በቀረበባቸው የክስ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት ባለ 10 ገፅ መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጠበቃው አቶ ተማም አባቡልጉ ተከሳሾቹ ሀምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ተይዘው ከሶስት ወር በኋላ ጥቅምት 7 ቀን 2006 ...

Read More »

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት ለአንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች የአደጋ ጥሪ ነው ተባለ

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦባማ በአፍሪካ ለሚያደርጉት ጉዞ በተለይ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው አገሪቱ በሰብአዊ መብት ጥሰቶችና በዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር የሌላት በመሆኑ ከዓለምአቀፍ ማኅበረሰቡ ኢትዮጵያን መጎብኘት ማቆም እንዳለባቸው በማሳሰብ ከፍተኛ ወቀሳ እየተሰነዘረባቸው ነው። በአፍሪካ ስላለው የሰብዓዊመብት አያያዝ ላይ ፕሬዝዳንቱ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል።በአንፃሩ ለፀጥታና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ዓላማ ይዘው ወደ አፍሪካ አህጉር የሚያቀኑት ኦባማ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ነጻነት ቀዳሚው ...

Read More »

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ መግባት በሰራዊቱ ውስጥ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል

ሐምሌ ፲፫ (አስራሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ “ለነጻነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የሚደረገውን ትግል መሬት ላይ ወርዶ መምራት ይገባል” በሚል እምነት በከፍተኛ ውጣ ውረድ ከአሜሪካ ኤርትራ መግባታቸው እንደተሰማ በአርበኞች ግንቦት7 ሰራዊት ውስጥ ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ፣ አስመራ በሚገኘው የድርጅቱ ጽህፈት ቤት አቀባበል ያደረጉላቸው ሻለቃ አክሊሉ መዘነ ተናግረዋል።በዋና ጽህፈት ቤቱ የሚሰሩ የፖለቲካ እና የውጭ ...

Read More »