ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝት ለአንዳንድ የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች የአደጋ ጥሪ ነው ተባለ

ሐምሌ ፲፬ (አስራአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦባማ በአፍሪካ ለሚያደርጉት ጉዞ በተለይ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው አገሪቱ በሰብአዊ መብት ጥሰቶችና በዲሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር የሌላት በመሆኑ ከዓለምአቀፍ ማኅበረሰቡ ኢትዮጵያን መጎብኘት ማቆም እንዳለባቸው በማሳሰብ ከፍተኛ ወቀሳ እየተሰነዘረባቸው ነው።
በአፍሪካ ስላለው የሰብዓዊመብት አያያዝ ላይ ፕሬዝዳንቱ ትኩረት ሊሰጡት ይገባል።በአንፃሩ ለፀጥታና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ዓላማ ይዘው ወደ አፍሪካ አህጉር የሚያቀኑት ኦባማ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ነጻነት ቀዳሚው አጀንዳቸው አይደለም ሲል ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘግቧል።