የአዲስ አበባ መንገዶች በጎርፍ እየተጥለቀለቁ ነው

ሐምሌ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የፍሳሽ ማስወገጃ ትቦዎች የሌላቸው እስኪመስል ድረስ እግረኞች ብቻ ሳይሆኑ አሽከርካሪዎችም ጭምር መንገድ ለማቋረጥ ሲሳናቸው ተስተውሏል። በርካታ የአዲስ አበባ መንገዶች ከዓመት እስከ ዓመት ተመሳሳይ ችግሮች ቢስተዋልባቸውም መንገድ ትራንስፓርት የፍሳሽ ማስወገጃዎችን በመስራትና የተበላሹትን ጠግኖ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ አልቻለም። የከተማው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ቢያሰሙም ችግራቸውን ሰምቶ መፍትሔ የሚሰጣቸው አካል ግን እስከ ...

Read More »

ፕሬዚዳንት ኦባማ በሰላም አስከባሪ ስም ተሸፍኖ የቀረበውን ተቃዋሚዎችን በሽብርተኝነት የሚፈርጀውን ጥያቄ ሳይቀበሉት ቀሩ

ሐምሌ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕ/ት ባራክ ኦባማ ከአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ በውጭ አገር በተለይም በአሜሪካ የተቀመጠ ተቃዋሚ ድርጅት በሽብረተኝነት እንዲፈረጅ የቀረበውን ጥያቄ ሳይቀበሉት ቀርተዋል። አቶ ሃይለማርያም ” ሽብርተኝነትን በመዋጋት እንዲሁም ሰራዊታችንን በጸጥታ አስከባሪነት ስም ለመላክ የማንችልበት ደረጃ ላይ እየደረሰን ነው” የሚል ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን፣ ለዚህም የሰጡት ምክንያት “በኤርትራ በኩል የሚነሱ ታጣቂ ሃይሎች የፈጠሩትን ...

Read More »

በሙስና የሚዘጉ የፍርድ ቤት መዝገቦች በዝተዋል ተባለ

ሐምሌ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ12ኛው የፍትህ ሚኒስቴርና የክልል ፍትህ ቢሮዎች የጋራ መድረክ ላይ እንደተነገረው በበጀት አመቱ የተቋረጡ መዝገቦች በሙሉ ኦዲት ተደርገው ሲጣሩ፣ በአጠቃላይ የፍርድ ቤት መዝገቦች የተዘጉት በክራይ ሰብሳቢነት፣በዝምድናና በተያያዙ የገንዘብ ጉዳዮች መሆኑን የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናግረዋል። የደቡብ ክልል የፍትህ ቢሮ ኃላፊ በክልላቸው በስፋት በሚታየው ህገወጥ የሰወች ዝውውር ላይ በሰጡት አስተያየት ፣ በርካታ ወጣቶች ወደ ደቡብ ...

Read More »

በአዲስ አበባ የሲኤምሲ አካባቢ ነዋሪዎች በድጋሚ ልንፈናቀል ነው አሉ

ሐምሌ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚኖሩ 43 አባወራዎች ከ200 በላይ ቤተሰቦች ቀደም ብለው ይኖሩበት የነበረውን ቀያቸውን በልማት ምክንያት ለቀው በተጠቀሰው ወረዳ እየኖሩ ቢሆንም በመንገድ ግንባታ ምክንያት ሕገወጥ ገንቢዎችን ለማዳን ተብሎ እነሱ በድጋሚ ሊፈናቀሉ መሆኑን በመጥቀስ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲታደጓቸው የተማፅኖ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡ ይመለከታቸዋል ላሏቸው የመንግስት ተቋማት ...

Read More »

ኢትዮጵያዊው ወጣት በአውስትራሊያ ፖሊስ አሰቃቂ ድብደባና የዘረኝነት መድሎ እንደተፈፀመበት በመግለፅ ክስ መሰረተ

ሐምሌ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውስትራሊያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ኢትዮጵያዊው ወጣት ናስር ባሬ በሁለት የፖሊስ ባልደረቦች አካላዊ ጥቃትና የዘር መድሎ ተፈፅሞብኛል ብሎ ያቀረበው ክስ በወንጀል መርማሪዎች እንዲጣራ ትዕዛዝ አስተላልፏል አቶ ናስር ”ሁለት ፖሊሶች ከፍሳሽ ትቦ ላይ አጋድመው ረገጡኝ ጥርሶቼ ተሰባብረዋል፣እጄን ጠምዝዘው ዐይኔ ላይ የሚያቃጥል ካፕሱም እስፕሬይ ረጩብኝ፣የጎን አጥንቶቼን ረገጠውኛል ይህ ሳያንሳቸው ፀያፍ የሆኑ የዘረኝነት ስድቦችን ይሰድቡኝም ...

Read More »

ፕ/ት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችንና የሰብአዊ መብት ተማጋቾችን ማሰሯን በአደባባይ ነቀፉ

ሐምሌ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሜሪካዊው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በስልጣን ላይ ያለውን ገዢ ፓርቲ ” በዲሞክራሲያዊ ምርጫ” የተመረጠ ነው ብለው መናገራቸውን ተከትሎ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ተቃውሟቸውን ባሰሙ ማግስት፣ ይህንን ንግግራቸውን የሚቃረን ንግግር በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ተገኝተው አድርገዋል። ፕሬዚዳንቱ ስለኢትዮጵያ ዲሞክራሲ በመጀመሪያው ቀን የተናገሩትን ላለመድገም ጥንቃቄ ያደረጉ ሲሆን፣ ምርጫውን በተመለከተ ያነሱት ብቸኛ ጠንካራ ጎን ያለ ...

Read More »

አንድ የልዩ ሃይል አባል 6 ጓደኞቹን አቁስሎ ገንዘብ ይዞ ተሰወረ

ሐምሌ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ድርጊቱ የተፈጸመው ንብረትነቱ የቱርክ የሆነና በጥጥ ማምረት ስራ ላይ የተሰማራውን የቶረን የእርሻ ኩባንያ ገንዘብ ጭኖ በመጓዝ ላይ ባለ መኪና ላይ ነው። የኩባንያው ሃላፊዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአሜሪካ ዶላርና ብር ይዘው በ7 የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት ታጅበው ወደ ወንዶ ጎጊ ወረዳ በሚጓዝበት ወቅት፣ አንደኛው ወታደር ለመጸዳዳት በሚል መንገድ ላይ ...

Read More »

በጋሞጎፋ ዞን ከብሄር ግጭት ጋር በተያያዘ ከ100 በላይ ሰዎች ታሰሩ

ሐምሌ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ወኪላችን እንደገለጸው ከሁለት ሳምንት በፊት በአርባምንጭ ከተማ ሊደረግ የታቀደው የተቃውሞ ሰልፍ በገዢው ሃይል የጸጥታ አባላት እንዲበተን ከተደረገ በሁዋላ፣ ከ120 በላይ ሰዎች ተይዘው በአርባምንጭ እስር ቤት ታስረዋል። አንድ የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆነ ሰው የጋሞን ብሄረሰብ ታሪክ አንቋሾ መጽሄት አሳትሟል በሚል የተጀመረው ተቃውሞ እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ፣ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞ ሊያሰሙ ይችላሉ ...

Read More »

ፕ/ት ኦባማ ” ኤርትራ ያለ ተቃዋሚ ድርጅትን በአሸባሪነት ለመፈረጅ ” የሚያስችል በቂ መረጃ የለንም አሉ

ሐምሌ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሜሪካዊው ፕ/ት ባራክ ኦባማ ይህን የተናገሩት ” በአሜሪካና በኤርትራ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመወጋት የምታደርገውን ጥረት እያደናቀፉ በመሆኑ የእርስዎ መንግስት የኢትዮጵያን መንግስት ለመርዳት ምን ያክል ዝግጁ ነው ተብሎ ከኢቢሲ ጋዜጠኛ ” ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ነው። ጋዜጠኛው የድርጅቱን ስም በግልጽ ከመግለጽ ቢቆጠብም፣ ፕ/ት ኦባማ የሰጡት መልስ ፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም ...

Read More »

ከጎንደር ከተማ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍኖ የተወሰደው የሰማያዊ ፓርቲ አባል መምህር አለላቸው አታለለ የት እንደሚገኝ አልታወቀም ተባለ

ሐምሌ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሀምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ጎንደር ከተማ ውስጥ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍኖ የተወሰደው የሰማያዊ ፓርቲ አባል መምህር አለላቸው አታለለ የት እንደሚገኝና በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ እንዳልቻሉና ከፍተኛ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል በጎንደር መምህራን ኮሌጅ የአይ ሲቲ መምህርና የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ የሆነው መምህር አለላቸው አታለለ ፣ ሀምሌ 1 ቀን 2007 ...

Read More »