ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት መስተዳድሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ያወጣውን ህግ የተቃወሙ አሽከርካሪዎች የ3 ቀናት የስራ ማቆም አድማ ካደረጉ በሁዋላ፣ የተወሰኑ አሽከርካሪዎች ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አሽከርከሪዎች እንደሚሉት ፣ ወደ እስር ቤት ከተወሰዱ በሁዋላ ጨማቸውን አውልቀው፣ እጆቻቸው በሲባጎ ገመድ ወደ ሁዋላ ታሰሮ የወስጥ እግራቸውን ተገርፈዋል። ምንም እንኳ አሽከርካሪዎቹ በግዴታና ...
Read More »በጉጂ ዞን ንግድ ባንክ ስራ በማቆሙ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ መውሰድ አልቻሉም
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በቀድሞዋ ክብረመንግስት በአሁኑ አዶላ ወዮ ከተማ የሚገኘው ክብረመንግስት የኢትጵያ ንግድ ባንክ ካለፉት 9 ቀናት ጀምሮ ስራ በማቆሙ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ለመውሰድ ተችግረዋል። ቤተሰቦቻችን ለችግር ተዳርገዋል የሚሉት ሰራተኞች፣ አቤቱታ ቢያቀርቡም፣ የኔትወርክ ችግር ነው ጠብቁ ከመባል ውጭ መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም። ፖሊሶችን ጨምሮ ሁሉም የመንግስት ስራተኞች ደሞዛቸው በንግድ ባንክ በኩል ...
Read More »በየመን በተከሰተ አውሎ ንፋስ ሳቢያ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች አስከፊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በምህጻረ ቃል UNHCR ዛሬ ከዋና ጽሕፈት ቤቱ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ እንዳስታወቀው በየመን ነፋስና ቀላቅሎ በጣለው ኃይለኛ ዝናብ ሳቢያ በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን፣ ሶማሊያዊያንና የኤርትራ ዜጎች በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። በሳኡዲ አረቢያ የሚመራው የጥምረት ጦርና አገሪቱን ተቆጣጥረው የነበሩት በኢራን የሚደገፉት የሃውቲ አማጽያን መሃከል በሚደረገው ውጊያ ሳቢያ ...
Read More »በሶማሊያ ለተገደለ አንድ የሴራሊዮናዊ ወታደር ለቤተሰቦቹ የሃምሳ ሽህ ዶላር ካሳ ተሰጠ
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም ስር እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2012 ዓ.ም የሴራሊዮን መከላከያ ሰራዊት አባል በመሆን በደቡባዊ ሶማሊያ በግዳጅ ላይ እያለ ሕይወቱን ላጣው ሴራሊዮናዊ ወታደር ፣ የአፍሪካ ሕብረት የሰጠውን የሃምሳ ሽህ ዶላር የደም ካሳ የሴራሊዮን የመከላከያ ሚንስቴር የሆኑት ሌቴናል ጄኔራል ሳሙኤል ኦማር ዊሊያምስ ለሟቹ ባለቤት በክብር ስነስርዓት ገንዘቡን አስረክበዋል። ...
Read More »ሰመጉ ከአንድ አመት በፊት 65 ሰዎች የየረር ጎሳ አባላት መገደላቸውን አረጋገጠ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የአሁኑ ሰመጉ ኢሳት ከአንድ አመት በፊት የሰራውን፣ በሶማሊ ክልል በየረር ጎሳ አባላት ላይ የደረሰውን እልቂት የተመለከተውን ዘገባ ሰራተኞቹን ወደ ስፍራው ልኮ ያረጋገጠበትን ዘገባ ይፋ አድርጓል። ኢሳት ጥቃቱ እንደተፈጸመ ወዲያውኑ ዜናውን ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን ፣ በታህሳስ ወር 2006 ዓም የየረር ባሪ የአገር ሽማግሌዎችን አነጋግሮና ለጠቅላይ ሚኒስትር ...
Read More »በአዲስ አበባ በርካታ ፖሊሶች መልቀቂያ አቀረቡ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የፖሊስ ምንጮች እንደገለጹት አንድ የአየር ጤና የፖሊስ ባልደረባ በህክምና እጦት መሞቱን ተከትሎ፣ የክፍለከተማው ፖሊሶች ስራ በማቆም ተቃውሞአቸውን ከገለጹ በሁዋላ፣ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ፖሊሶች መልቀቂያ አስገብተዋል። የመቀሌ ከተማ ተወላጅ የሆነው ኦፊሰር የማነ በኩላሊት ህመም ሲሰቃይ ከቆዬ በሁዋላ፣ በፖሊስ ሆስፒታል ተገቢውን ህክምና ባለማግኘቱ፣ በግል ለመታከም 16 ሺ ብር ቢጠይቅም ለማግኘት አልቻለም። ይህን ...
Read More »አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ በፈጠረው ጥቃት በርካታ የሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ ሆኑ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሂራን ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው በለደወይኒ ፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ወታደሮችን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ አልሽባብ ባደረሰው የደፈጣ ውጊያ ጥቃት ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ወታደሮች መገደላቸውን የአካባቢውን የዓይን እማኞችን ጠቅሶ ሸበሌ ሬዲዮ ዘግቧል። ከማክሰኞ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ ረቡዕ ጠዋት ድረስ በአካባቢው አዲስ ውጊያ መቀስቀሱንና በሁለቱ አንጃዎችና በሕዝቡም መሃከል ...
Read More »በመንግስት ወጪ ለብአዴን ከተማ አቀፍ ድግስ ተዘጋጀ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ መስተዳድር ስር ባሉ የመንግስት መ/ቤት ውስጥ የሚገኙ የብአዴን አባላትና ደጋፊዎች ስለ ብአዴን የትግል ታሪክ እና ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ለኢህአዴግ እያደረገ ስላለው አስተዋጽኦ፣ ከዚህ ቀደም ብአዴን ስላበረከተው ድርጅታዊ አስተዋጽኦ እንዲሁም የክልሉ ህዝብ ለድርጅቱ ያበረከተው አስተዋጽኦ የጎላ ነበር የሚል አጠቃላይ ይዘት ያለው እውቅና ለመስጠት በሚል የተዘጋጀውን ከተማ አቀፍ ድግስ የአዲስ አበባ ...
Read More »የልማት ኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ከአዲስ ዘመን ጋዜጠኞች ጋር በፈጠሩት ጸብ ሰራተኛው እየታመሰ ነው
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ ዘመን ጋዜጠኞች ለዜና ዝግጅት በፌደራል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ ባመሩበት ወቅት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ” ልማታዊ ጋዜጠኛ ማሟላት የሚገባውን ስነ ምግባር ፈጽሞ የላችሁም የሚል ቁጣና ማስፈራሪያ አዘል” ንግግር የተናገሩዋቸው ሲሆን፣ ጋዜጠኞችም ” በድርጅቱ ውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ ብለው ሰራተኞችን አነጋግረው ከዘገቡ በሁዋላ፣ ዋና ዳይሬክተሩ በገዛ ስልጣናቸው ...
Read More »በደቡብ አፍሪካ ታግተው የተወሰዱ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ለጥቂት ከሞት ተረፉ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት በደቡብ አፍሪካ በአስከፊ ሁኔታ በስደተኞች ላይ ያነጣጠረው ግድያና ዝርፊያ ድጋሜ የማገርሸት አዝማሚያው ምልክቶች ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ እየታየ ሲሆን፣ በቀድሞዋ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ ውስጥ ታግተው የተወሰዱ ሁለት ኢትዮጵያዊያን በፖሊስ ጣልቃገብነት ለጥቂት ከሞት ተርፈዋል። የግል ሱቅ በመክፈት ሥራ የሚተዳደረው ፈይሳ ሊሬና ጓደኛው በሁለት አጋቾች ከስራ ቦታቸው ታግተው ከከተማ ውጪ ከተወሰዱ በኋላ ...
Read More »