የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኦራል መኪና ተገልብጦ በትንሹ 20 ወታደሮች ህይወታቸው ሲያልፍ በርካቶችም ቆስለዋል

ኀዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ህዳር 2፣ 2008 ዓም ከጎንደር ወደ መተማ ሲጓዙ ከነበሩ ኦራል መኪኖች መካከል አንደኛው ግንድ መጣያ ቀበሌ ልዩ ስሙ ባለእግዚብሄር ቦታ ላይ ሲደርስ ባጋጠመው የቴክኒክ መበላሸት የተነሳ በመገልበጡ በሸራ ተሸፍነው ሲጓዝ ከነበሩት ወታደሮች መካካል 20 የሚሆኑት ወዲያውኑ ሲሞቱ፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች ቆስለው ወደ ጎንደር ሆስታል ተወስደዋል። ቦታው ላይ የነበሩ የአይን ...

Read More »

በኮንሶ ውጥረቱ ተባብሶ ብዙዎች በጅምላ እየታሰሩ ነው

ኀዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ሰገን ዞን ኮንሶ ወረዳ የሚገኙ ነዋሪዎች በዞን ደረጃ ራሳቸውን ለማስተዳደር እንዲፈቅድላቸው ጥያቄ በማቅረባቸው ብቻ የብሔረሰቡን አባላት ማሳደድ፣ ማሰር፣ መደብደብ ዘመቻው የቀጠለ ሲሆን፣በአካባቢው ያለው ውጥረት ተባብሷል፡፡ የደቡብ ክልል መንግስት የኮንሶን ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ጥያቄውን በኃይል ወደማፈን በመሸጋገሩ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከጉዳዩ ጋር እጃቸው አለበት የተባሉ በርካታ ሰዎች ከያሉበት ...

Read More »

በወልድያ ታዋቂ ባለሃብቶች ታሰሩ

ኀዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማው ከሚገኙና በአብዛኛው የገዢው ፓርቲ ዋነኛ ደጋፊ ባለሃብቶች ተብለው ከሚታወቁት መካከል 14 ቱ በአራጣ ማበደር ወንጀል ተከሰው ከሶስት ቀናት በፊት ታስረዋል። ከተያዙት ባለሃብቶች መካከል አቶ ስማቸው፣ አቶ ዘገየ መላኩ፣ ዶ/ር በቀለ፣ ሞላ ጌታሁን፣ አውዱ፣ ኪዳኔ ካህሳይ፣ አበበ ደመቀ፣ አቶ እስራ፣ ፖለስ ጌታው አበሬ፣ እንዲሁም አቶ ካሳሁን ይገኙበታል። ባለሀብቶቹ የብአዴን ባንክ ከሆነው ...

Read More »

ገዢው መንግስት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ባለማድረጉ ለችግር መዳረጋቸውን ከአረብ ሃገር ተመላሾች ተናገሩ፡፡

ኀዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑ ወጣት ከስደት ተመላሾች ከዓመታት በፊት ወደ ሐገራቸው እንዲመለሱ በከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተደረገ ቅስቀሳ በመታለል ለረጅም ዓመት ያፈሩትን ሐብትና ንብረት በአግባቡ ሳይዙ ከተመለሱ በኋላ በማህበር ተደራጅተው ያለምንም ድጋፍና ክትትል በመተዋቸው ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ወጣቶቹ የብድርና የመስሪያ ሸድ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ ቢባሉም ፤ ከሁለት አመት በላይ ተሰርተው ያለ ...

Read More »

ኢህአዴግ አባሎቹን ሂሳዊ ደጋፊና እና ጽንፈኛ ተቃዋሚ ሲል ከሁለት ከፈላቸው

ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሲመክር አሉኝ የሚላቸውን ደጋፊዎች በሁለት እንደሚከፍላቸውና ሁለቱም ለግንባሩ በስልጣን ለመቆየት ቀዳሚ የስጋት ምንጭ ናቸው ሲል ፈርጇቸዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች አቶ በረከት ስምኦን፣ የጠ/ሚኒስትሩ ሌላው አማካሪ አቶ አለበል ደሴ፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፣ የመረጃ መረብ ደህንነት የህዝብ አስተያየት ትንተና ክፍል ፣ የሁሉም የፖለቲካ ድርጅት ጽ/ቤት ሃላፊዎች በተወያዩበት መድረክ ላይ ...

Read More »

መንግስት በትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ እድገት ማምጣቱን ቢናገርም አገራዊ ግቡ ዝቅተኛ ነው ተባለ

ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት አጠቃላይ የትምህርት ተደራሽነት ክንውን 43 ነጥብ 2 ብቻ መሆኑንና አሃዙ ከክልል ክልል እንደሚለያይ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ አንድ ሰነድ አመልክቷል። የትምህርት ተሳትፎው በአዲስአበባ 88 በመቶ፣በትግራይ 75 በመቶ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉምዝ 45 በመቶ ሲሆን ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ 3ነጥብ 6፣ አፋር 4 ነጥብ 5 እንዲሁም በጋምቤላ 17 ነጥብ8 በመቶ ብቻ ነው። በተለይ በአፋርና ...

Read More »

በፌደራል ጉዳዮች ሚንስቴር ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ተመጣጣኝ ልማት ለማረጋገጥ የተዘጋጀ እቅድ አልተሳካም የሚል ሪፖርት ለአዲሱ ሚንስትር ካሳ ተ/ብርሐን ቀረበላቸው፡፡

ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዲሱ ሚንስትር በአዲሱ የስልጣን ወንበራቸው ተገኝተው ከሚንስትሩ መስሪያቤት ሰራተኞች ጋር ባደረጉት ትውውቅ ያለፉትን አምስት አመታት ሂደት በመገምገም እና የሰራተኛውን የመልካም አሰተዳደር ችግር እንዲያቀርቡ በውይይት ስራ ጀምረዋል፡፡ ሰራተኞች በግልፅ የሚንስትር መስሪያ ቤቱ ክንዋኔዎች እንዲገመግሙ እና ስሀተት ካለ ታርሞ እንዲቀጥል በሰጡት እድል በሚኒስቴሩ የተመጣጣኝ ልማት የማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ያስበነውን ግብ መምታት አልቻልንም ሲሉ ...

Read More »

ለአባይ ግድብ በግድ መዋጮ እንዲከፍሉ የተገደዱ ሰራተኞች በፍርድ ቤት ክስ ከፈቱ

ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ቻላቸው ሞላ የግብርና ባለሙያ ሰራተኞችን ሳያነጋግሩና ፈቃዳቸውን ሳይጠይቁ፣ ከተወሰኑ ሀላፊዎች ጋር በመመካር የግብርና ባለሙያዎች በሙሉ ለአባይ ግድብ እንዲከፍሉ አድርገዋል። የግብርና ባለሙያዎች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ታውቋል።

Read More »

የብሪታንያ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጤንነት ያሳስበኛል አለ

ኢሳት (ጥቅምት 30 2008) የብሪታኒያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙትን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የጤንነት ሁኔታ  አሳስቦት እንደሚገኝ በድጋሚ ገለጠ። የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ አስመልክቶ ትናንት ሰኞ በዚህ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኘው የብሪታኒያ ኤምባሲ ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ምላሹን በጽሑፍ የሰጠው ኤምባሲው አቶ አንዳርጋቸው ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ያሉበት ሁኔታ በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በአጠቃላይ አሳሳቢ መሆኑን አስታውቋል። በኢትዮጵያና በብሪታኒያ መካከል የአቶ አንዳርጋቸው ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ዞን በርካታ የልዩ ሃይል አባላትና ሰላማዊ ዜጎች ተገደሉ

ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅማንት ብሄረሰብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአርሶ አደሩና በክልሉ ልዩ ሃይል መካከል ከማውራ 15 ኪሜ ርቃ በምትገኘዋ ሮቢት አካባቢ እንዲሁም በላይ አርማጭሆ ዋና ከተማ ትክል ድንጋይ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶአል። እስከትናንት ድረስ በአርሰዶ አደሩና በልዩ ሃይል መካከል በተደረገ የተኩስ ለውጥጥ ከ100 በላይ የልዩ ሃይል አባላት ሲገደሉ፣ ከ36 ያላነሱ ንጹሃን ዜጎች ደግሞ በልዩ ሃይል አባላት ...

Read More »