በኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ውስጥ ፍርሃት ነግሷል

ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በነሃሴ ወር ባካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ የመልካም አስተዳዳር ችግሮችን ለመፍታት ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ እርምጃ እንደሚወድድ ውሳኔ ቢያሳልፍም አብዛኛው አመራር የችግሩ ሰለባ በመሆኑ በግንባሩ እርስበእርስ ከፍተኛ መፈራራትና መጠባበቅ መከሰቱ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት በሚለው ጉዳይ ላይ ልዩነት ያላቸው ሁለት ቡድኖች በግልጽ መውጣታቸው ታውቆአል፡፡ራሱን ንጹህ አደርጎ የሚያየው ቡድን ድርጅቱ አጥፊዎችን ...

Read More »

በሰሜን ሸዋ 23 እስረኞች አመለጡ

ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ማክሰኞ ሸዋ ሮቢት በቀወት ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ እስረኞች በሙሉ ያመለጡ ሲሆን፣ እስረኞቹ እስካሁን አልተያዙም። አብዛኞቹ እስረኞች በህገወጥ መንገድ ትነግዳላችሁ ተብለው የተያዙ ነበሩ። እስረኞቹ ሌሊት ላይ የጭቃ ቤቱን ግድግዳ በውሃ አርሰው ከቀደዱት በሁዋላ ሁሉም በአንድ ላይ አምልጠዋል። ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ እስረኞችን ለመያዝ ፍተሻ በመካሄድ ነው። የወረዳው ነዋሪዎች እስረኞችን አምጡ በማለት ...

Read More »

የዞን 9 ጦማሪ ዘላለም ክብረት ከአገር እንዳይወጣ ታገደ

ኀዳር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም ዓለማቀፍ የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን የነጻነት ሽልማት በሲቲዝን ጆርናሊዝም ጋዜጠኝነት ምድብ አሸናፊ በመሆን ተሸላሚ የሆኑትን ዞን 9 በመወከል ጦማሪ ዘላለም ክብረት ሽልማታቸውን ለመውሰድ ወደ ፈረንሳይ ሊያደርገው የነበረው ጉዞ በኢትዮጵያ የደኅንነት ኃይሎች ፓስፖርቱን በመነጠቁ መታገዱ እንዳሳሰበው ዓለምአቀፉ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ገልጿል። ”የጉዞ እገዳው በዘላለም ክብረት ...

Read More »

አሁን ያለው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ ከሁለት ሳምንት ጊዜ በላይ እንደማያቆይ ታወቀ

ኢሳት (ህዳር 9 ፣ 2008) የአለም ምግብ ፕሮግራም (FAO) በድርቁ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን የሚያቀርበው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሊያልቅበት እንደሚችል ትናንት ረቡዕ አሳሰበ። የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት የሚያደርገው የእርዳታ አቅርቦት ከፍተኛ እጥረት አጋጥሞት እንደሚገኝ የገለጸው ድርጅቱ፣ የምግብ አቅርቦቱ በተያዘው የፈረንጆች ወር መጨረሻ ላይ ሊቋረጥ እንደሚችል ይፋ አድርጓል። የአለም የምግብ ፕሮግራም እስከፊታችን ሰኔ ድረስ ከሚያስፈልገው የ228 ሚሊዮን ዶላር ...

Read More »

በቤንሻንጉል ጉሙዝ 12 የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተገኙ

ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጊቱ የተፈጸመው ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን የቀብሩ ስነስርዓት የተፈጸመው ግን ባሳለፍነው ሳንምት ነው። በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ 12 የአማራ ተወላጆች ለቀን ስራ ተብለው ከተወሰዱ በሁዋላ በወረዳው አስተዳደሪ ትእዛዝ ኮከል ቀበሌ ላይ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተረሽነዋል።አስከሬናቸው ተቆራርጦ በጆንያ ተጠቅሎ መገኘቱንና የቀብር ስነስርዓታቸውም መፈጸሙን ምንጮች ገልጸዋል። የተገደሉት ነዋሪዎች 20 የሚደርሱ ሲሆን፣ እስካሁን አስከሬናቸው ...

Read More »

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ 2 መምህራን ታሰሩ

ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህር ወንድማገኝ አንጆሎ እና መምህር መስፍን በላይ የታሰሩት ባለፈው ሳምንት ሲሆን፣ ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ እስር ቤት ተወስደዋል። ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር በተያያዘ መታሰራቸውን ምንቾች ገልጸዋል። መምህራሩ ከሰው ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። መምህር ወንድማገኝ ከመታሰራቸው በፊት ዩኒቨርስቲው የስራ እና የእግድ ደብዳቤ ጽፎላቸው ነበር። በመምህር ወንድማገኝ ላይ የቀረበውን ክስ መነሻ፣ የየኑቨርስቲ ...

Read More »

አለማቀፍ የአፋር ዲያስፖራ በአፋሮች ላይ የሚደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ለጅቡቲው ፕሬዚዳንት ደብዳቤ ጻፈ

ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእንግሊዝኛ አጭር አጠራሩ ፊዳ የተባለው የአፋር ድርጅት ለጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ በጻፈው ደብዳቤ በአፋር ህዝብ ላይ የዘር ማጽዳት በመፈጸም፣ የራስዎን ዘሮች በቦታው ላይ እያስቀመጡ ነው ሲል ከሷል። ድርጅቱ እንዳለው የአፋር ተፈጥሮአዊ መኖሪያ በሆነው ድክሂል ፣ አርታ፣ በታጁራ ከተማና በኦቦክ በሚገኙ አፋሮች ላይ የጸታ ሃይሎች እስር ግድያ፣ አፈና አስገድዶ መድፈርና ሌሎችንም ...

Read More »

ብአዴን ህዝቡን በግዳጅ ሰልፍ እያስወጣ በአሉን እያከበረ ነው

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-35ኛ አመት በአሉን በማክበር ላይ ያለው ብአዴን ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች፣ ነጋዴዎችና በተለያዩ ሙያ የተሰመራዩት ሁሉ ስራቸውን አቁመውና ድርጅታቸውን ዘግተው በአሉን እንዲያከብሩ ተገደዋል። በበአሉ ላይ ባልተገኙት ላይ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው ቀጣቶች እንደሚተላለፍባቸው የድርጅቱ ካድሬዎች ሲቀሰቅሱ መሰንበታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በኮምቦልቻ፣ ደሴ ጎንደርና ሌሎችም ቦታዎች ህዝቡ ለብአዴን ሰልፍ እንዲወጡ ተገደዋል። በተለይ ተማሪዎች በበአሉ ...

Read More »

የህወሃት ድጋፍ ያለው ቡድን በአፋር ስልጣኑን ተቆጣጠረ

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል ራሳቸውን ከህወሃት ተጽኖ ለማላቀቅ በሚፈልጉ የአቶ ጣሃ አህመድ ቡድኖችና ህወሃት ከጀርባ ሆኖ በሚመራቸው በአቶ ስዩም አወል መካከል ሲካሄድ የነበረው የስልጣን ሽኩቻ ፣ በህወሃት የሚደገፉት አቶ ስዩም የአፋር ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው በመመረጥ አሸንፈዋል። ከጥቅምት 30 / 2008 ዓ.ም እስከ ሕዳር 03/ 2008 ዓ.ም ድረስ ከቀመሌ ወደ 40 ኪሜ ርቀት ...

Read More »

የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የቅርብ ቤተሰብ በበርካታ ዜጎች ላይ የፈጸሙት ማጭበርበር ተጋለጠ

ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለቤት አባት የሆኑት አቶ አሰፋ ሩዎ ሂወራ በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ነዋሪዎችን የቤት ካርታ በመቀበል በአመት ከ25 ሺ እስከ 30 ሺ ብር እንደሚከፍሉ አስታውቀው የባንክ ብድር ከወሰዱ በሁዋላ፣ ብድሩን ለመመለስ ሳይችሉ በመቅረታቸው የቤታቸውን ካርታ ያስያዙ ሰዎች ቤታቸው በሃራጅ ሊሸጥባቸው መሆኑን ተናግረዋል። ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ ሚኒስትሩን ከለላ በማድረግ አቶ ...

Read More »