በባህርዳር እስረኞች ለ2 ቀናት በቤተሰብ እንዳይጠየቁ ተደረጉ

ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው እሁድ የእስር ቤቱ ሃላፊዎች ” በእስር ቤቱ ውስጥ ቦንብ ገብቷል” የሚል መረጃ ደርሶናል በሚል እስር ቤቱን በአድማ በታኝ ፖሊሶች አጥለቅልቀውና ዋናውን መንገድ በመዝጋት ጠያቂዎች እንዳይገቡ ከልክለዋል። በዚሁ ሰበብ በእስረኞች ላይ ከፍተኛ እግልት የደረሰ ሲሆን፣ ለሁለት ቀናት ያክል እስረኞች በቤተሰቦቻቸው እንዳይጠየቁ አግደዋል። በእስር ቤቱ ውስጥም ከፍተኛ ፍተሻ ተካሂዷል። ዛሬ ታህሳስ 28 ...

Read More »

በትግራይ አርሶአደሮች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታህሳስ 22፣ 2008 ዓም በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮች ተቃውሞውን ያካሄዱት የበለስ ምርታችን በተሳሳተ ምርምር ወድሞብናል በሚል ምክንያት ነው። አርሶአደሮቹ ከዋጅራት ተነስተው በእግራቸው ወደ መቀሌ የገሰገሱ ሲሆን፣ አዲግዶም ላይ ፖሊሶች በሃይል በትነዋቸዋል። አርሶአደሮቹ እንደሚሉት ለምርምር በሚል የገባው በሽታ ፣ የበለስ ምርቱን በከፍተኛ ሁኔታ በመጉዳቱ በህልውናቸው ላይ አደጋ ፈጥሯል። መንግስት በሽታውን ያመጡትን ተመራማሪዎች ለፍርድ ...

Read More »

በኒውዚላንድ የሚኖሩ ሴቶች ገንዘብ አሰባስበው ለአርበኞች ግንቦት7 ለገሱ

ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኒዉዚላንድ ዌሊንግቶን የሚኖሩ ሴቶች ፣ በበረሃ ውስጥ ያሉ ሴቶችን ለመርዳት በሚል ተነሳስተው ለአርበኞች ግንቦት ሰባት የሴት ታጋዮች ፍጆታ የሚዉል ገንዘብ መለገሳቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። ሴቶቹ ይህ ጅማሪ እንጂ የመጨረሻዉ እንደማይሆን፣ ለወደፊቱ ራሳቸዉን በማደራጀት ቀጣይ የሆነ እርዳታ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በገና በዓል ቀን ሴት እሕቶቻችን በጫካ ለኛ ነፃነት ሲታገሉ እኛ የተመቻቸ ...

Read More »

የድርቅ አደጋ ወደአሳሳቢ ደረጃ ተሸጋግሯል ተባለ

ኢሳት (ታህሳስ 27 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ከ180 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች ውስጥ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ወደአሳሳቢ ደረጃ እየተሸጋገረ መምጣቱንና ድርቁ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልገው ፍጆታ በሶስት እጅ እጥፍ ማደጉን የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ገለጠ። በተያዘው ወር ለተረጂዎች ከሚያስፈልገው የእርዳታ አቅርቦት ውስጥ ከአምስት በመቶ ብቻ የሚሆነው መገኘቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ሽቴፈን ዱጃሪክ አስታውቀዋል። በወቅታዊው የኢትዮጵያ የድርቅ ሁኔታ ...

Read More »

የአባይ ግድብ የዲዛይን ማሻሻያ ሊደረግበት በሚችል ሁኔታ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

ኢሳት (ታህሳስ 27, 2008) ረቡዕ በአዲስ አበባ ምክክርን የጀመሩት የኢትዮጵያና የግብፅ የባለሙያዎች ቡድን የአባይ ግድብ የዲዛይን ማሻሻያ ሊደረግበት በሚችል ሁኔታ ላይ ኣንደሚወያዩ የግብፅ ባለስልጣናት ይፋ አደረጉ። አምስት የባለሙያዎች ቡድንን ያካተተው የሃገሪቱ ልዑካን ለሁለት ቀን በሚቆየው ድርድር ላይ ይህንኑ ሃሳበ በማቅረብ ሰፊ ገለፃን እንደሚያደርግ የግብፅ የመስኖ ልማት ሚኒስትር ሆሳም ሞግሃዚ ለአል-አህራም ጋዜጣ ገልጸዋል። ረቡዕ በአዲስ አበባ ስለጀመረው የሁለቱ ወገኖች ድርድር በተመለከተ ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ሃይሎች የቤት ለቤት ፍተሻንና የጅምላ እስርን እያካሄዱ ነው

ኢሳት  (ታህሳስ 27 ፣ 2007) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ከተሞች ዳግም የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች የቤት ለቤት ፍተሻንና የጅምላ እስርን በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የተለያዩ አካላት ገልጸዋል። የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ተቃውሞን ሲያስተባብሩ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች የዚሁ ሰለባ መሆናቸውንም ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ሂውማን ራይትስ ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ግድያ ከተፈጸመባቸው ሰዎች በተጨማሪ በርካታ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ለእስር እየተዳረጉ እንደሆነ አስታውቋል። የኦሮሞ ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ አገረሸ፣ ወደሃረር ድሬዳዋ የሚወስደው መንገድ ተዘጋ

ኢሳት (ታህሳስ 27 ፣ 2008) በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ከትናንት ጀምሮ በጭሮ (አሰበ ተፈሪ) እና በሒርና በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ እና ሃረር የሚወስዱት መንገዶች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸው ታወቀ። መንግስት ተቃውሞውን በጠመንጃ ሃይል ለማስቆም በወሰደው እርምጃ በርካታ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን መዘገቡ ይታወሳል።  በተቃውሞው ከተሳተፉት ሰዎች ውስጥ በጥይት ተመተው ህይወታቸው አስጊ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች ቁጥር እጅግ በርካታ ...

Read More »

በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ መቀጠሉ የመንግስት ባለስልጣናትን ግራ አጋብቷል

ታኀሳስ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገር ቤት የሚገኙ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በመንግስት የክትትል መረብ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የጎላ ተሳትፎ በማያደርጉበት ሁኔታ፣ ህዝቡ ራሱን እያደራጀ ተቃውሞውን መቀጠሉ መንግስት ለሚወስደው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ሰበብ እንዲያጣ እንዳደረገውና በኢህአዴግ ውስጥ ቅራኔ እየፈጠረ መምጣቱን ምንጮች ገልጸዋል። ከአሁን ቀደም ተቃውሞውን ጸረ-ሰላም ሃይሎች እንዳዘጋጁት ተደርጎ ይነገር የነበረው ዜና፣ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት አለማግኘቱና ተቃውሞውም ...

Read More »

የደቡብ ክልል ተወላጅ መምህራን “በ25 አመታት አንድ ጀኔራልን ማፍራት ያልቻልነው ለምንደነው?” ነው ሲሉ ጠየቁ

ታኀሳስ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተጠርቶ በነበረው ስብሰባ ላይ የደቡብ ክልል መምህራን ” አሁን ስለሰላም ፣ ስለመልካም አስተዳደርና ስለልማት ብታወሩ ማን ይሰማችሁዋል? እኛ ባለፉት 25 ዓመታት አንድ ጄኔራል ማፍራት ያቃተን ምን ስለሆንን ነው?” ሲሉ ጥያቄ አቀርበዋል። በአንድ የህወሃት መሪና በዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት የተመራው ስብሰባ ከፍተኛ ጭቅጭቅ የታየበት እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጿል። ከደቡብ ክልል የመጡ መምህራን ስሜታዊ ...

Read More »

በረሃብ ለተጠቁ ወገኖች ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልጋል ተባለ

ታኀሳስ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦክስፋም ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ በረሃብ ለተጠቁት ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የውጭ አገር መንግስታትና ድርጅቶች ቃል ከገቡት ተጨማሪ 1 ቢሊዮን 100 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ አፋጣኝ እርዳታ ያስፈልጋል ብሎአል። እስካሁን ድረስ ቃል የተገባው 300 ሚሊዮን ዶላር ነው ያለው ኦክስፋም፣ አሁን ባለው የተረጅ ቊጥር የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን ግን 1 ቢሊዮን ...

Read More »