በኦሮሚያ የክልል ከተሞች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አሁንም እንደቀጠለ ነው

ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2008) በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሰኞ በምስራቅና በምዕራብ ሃረርጌ አካባቢዎች መቀጠሉ ተገለጠ። በመለስተኛ ከተሞች በተካሄደው በዚሁ ተቃውሞ፣ ነዋሪዎችና ተማሪዎች ለእስር የተዳረጉ ተማሪዎች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጥያቄ ማቅረባቸው ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በምዕራብ ሃረርጌ ጭሮ ከተማና አካባቢዋ ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አለመርገቡንና ተመሳሳይ ተቃውሞዎች በምስራቅ ሃረርጌ በሚገኙ ከተሞች ሲካሄድ ማርፈዱም ታውቋል። በምዕራብ ሃረርጌ ሜዔሶ ወረዳና አካባቢው ...

Read More »

የአፋርና የሶማሌ ክልል በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ወደርሃብ ሊቀየር ይችላል ተባለ

ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2008) በደቡብ የአፋርና የሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን የሚገኙ ቀበሌዎች ውስጥ ተከስቶ የሚገኘው የድርቅ አደጋ በቀጣዮቹ ሁለት ወራቶች ወደርሃብ ሊቀየር እንደሚችል አንድ አለም አቀፍ ተቋም አሳሰበ። በደረጃ ሶስት የድርቅ አደጋ ውስጥ ተፈርጀው የሚገኙት እነዚሁ አካባቢዎች አፋጣኝ እርዳታን ካላገኙ ወደ “ረሃብ” ደረጃ በሚመደበው ደረጃ አራት ሊሸጋገሩ ኣንደሚችሉ ድርጅቱ አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለአስችኳይ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎችን ቁጥር 10.2 ...

Read More »

በአርባምንጭ ከተማ ወጣቶች  በህወሃት/ ኢህአዴግ ሃይሎች በገፍ እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው ተባለ

ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2008) በአርባምንጭ ከተማ ብዙ ወጣቶች የግንቦት 7 አባል ናችሁ በሚል ሰበብ ተጠርጥረው ዕርቃናቸውን ግርፋትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደተፈጸሙባቸው ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ። 20 አመት እድሜ ላይ የሚገኙ ዮሴፍ ይስሃቅና፣ እንዳሻው ወንድይፍራው ከዚህ በፊት በአርባምንጭ ከተማ ከጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ እያንዳንዳቸው በ2ሺ ብር ዋስትና እንደተለቀቁ፣ “ወያኔን ሰድበዋል፣ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ግንኙነት አላቸው” በሚል ሰበብ እንደተደበደቡ በስፍራው ...

Read More »

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያዊ ስደተኞችን ይዞ ይጓዝ የነበረ ጀልባ ሰጥሞ 112 ስደተኞች ሞቱ

ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2008) በጎረቤት ሶማሊላንድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያዊ ስደተኞችን ይዞ ይጓዝ የነበረ ጀልባ የመስጠም አደጋ አጋጥሞት በትንሹ 112ቱ መሞታቸውን የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ሰኞ አስታወቁ። ራሷን ነጻ ሃገር አድርጋ ባወጀችው ሶማሊላንድ በደረሰው የጀልባ አደጋ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩንም የነብስ አድኑ ሰራተኞች ገልጸዋል። በጀልባው ላይ ከደረሰው አደጋ 75 ሰዎችን መታደግ እንደተቻለና ስደተኞቹን ይዞ ይጓዝ የነበረው ጀልባ የቴክኒክ ችግር ...

Read More »

በኦሮምያ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህዝባዊ ተቃውሞውን ግንባር ቀድም ሆነው እየመሩት ነው

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወር በላይ ያስቆጠረው በኦሮምያ የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደገና በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሃይሉን ጨምሮ ሲካሄድ ሰንብቷል። መንግስት ከፍተኛ ሰራዊት በማሰማራትና ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በመውሰድ ተቃውሞውን ለማብረድ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም በክልሉ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሚጫወቱት የመሪነት ሚና ተቃውሞ አድማሱን አስፍቶ ቀጥሎአል።በጀማ፣አሮማያ፣ መዳወላቡ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች በክልሉ እየተፈጸሙ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ከማወገዛቸውም በላይ፣ ተቃውሞውን ተከትሎ ...

Read More »

የወልቃይትን ህዝብ ለማሳመን የተላከው ቡድን እስካሁን አልተሳካለትም

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለፍለጎታቸውን ወደ ትግራይ ክልል በመጠቃለላችን ወደ አማራ ክልል እንዛወር በማለት የጠየቁ የወልቃይት ነዋሪዎችን ሲያግባባ የነበረው ከአማራ ክልል ከልዩ ልዩ መስሪያ ቤቶች የተወጣጣው ቡድን ለአንድ ወር ያክል ጊዜ በአካባቢው ተሰማርቶ የማሳመን ስራ ለመስራት ቢሞክርም እስካሁን ተልዕኮው ባለመሳካቱ ለተጨማሪ ጊዜ በወልቃይት ለመክረም ተገዷል፡፡ የክልሉ ጸጥታ ጉዳዮች፣ ፍትህ፣ፖሊስና መከላከያን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ተሿሚዎችን ያካተተው ቡድን ...

Read More »

ኢትዮጵያ በተመድ የልማት ፕሮግራም መስፈረት የ174ኛ ደረጃን ያዘች

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት የልማት ፕሮግራም UNDP ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ከ188 የአለም አገራት 174ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጿል። ድርጅቱ የኢኮኖሚ እድገትን፣ ልማትን፣ የጸጥታ ጉዳዮችን ፣ የፖለቲካ ነጻነትንና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮችን በማጥናት የሚያወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ካለፈው አመት ከነበረችበት ደረጃ ዘንድሮ አንድ ደረጃ ዝቅ ብላለች። በአለማ ላይ ካሉት አገራት ኢትዮጵያ መብለጥ የቻለችው 14 አገራትን ብቻ ሲሆን፣ ሁሉም ...

Read More »

ወደ የመን በጀልባ ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች ውስጥ 122 የሚሆኑት ሕይወታቸውን አጡ

ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መነሻቸውን በሶማሌላንድ ሳናጋ ግዛት አድርገው በተጨናነቀ ጀልባ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ባሕር አቆራርጠው ወደ የመንና የገልፍ አገራት ለመግባት ሲጓዙ ከነበሩት ኢትዮጵያዊያንና ሶማሊያዊያን ዜጎች ውስጥ አብዛኞቹ መሞታቸውንና ከሟቾቹ ውስጥ 122 የሚሆኑት አስከሬናቸው በባህር ዳርቻዎች መገኘቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከአደጋው ሕይወታቸው የተረፈ 80 ኢትዮጵያዊያን መኖራቸውንና በድንበር ጠባቂዎች መያዛቸውን ዘገባው ገልፆ ፣ ከተያዙት ውስጥ አብዛኞቹ በምግብ ...

Read More »

በማስተር ፕላን ሰበብ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል፥ የመማር ማስተማር ሂደትን አስተጓጉሏል

ኢሳት (ታህሳስ 29 ፥ 2008) ከቀናት በፊት ዳግም ያገረሸው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ አርብ በምዕራብ ሃረርጌ በምትገኘው የጭሮ ከተማና አካባቢዋ ቀጥሎ መዋሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በሌሎች አካባቢዎች የተወሰደው አይነት የመንግስት ታጣቂዎች እርምጃም በከተማዋ ተካሄዶ በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል። ከቀናት በፊት በዚሁ በምዕራብ ሃረርጌ በምትገኘው የሂርና ከተማ ተቀስቅሶ የነበረው ተቃውሞ አለመብረዱንና አርብ በከተማዋና በዙሪያው ባሉ የገጠር መንደሮች ...

Read More »

በኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን የቤት እንስሳት በረሃብ መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ

ኢሳት (ታህሳት 29 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በሚገኙ ስድስት ክልሎች ጉዳትን እያደረሰ ባለው የድርቅ አደጋ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ የቤት እንስሳት በረሃብ ምክንያት መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጠ። በዚሁ የድርቅ አደጋ ወደ ሁለት ሚሊዮን የቤት እንስሳት ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህይወት የመቆየት እድላቸውም አደጋ ውስጥ መሆኑን ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው ረፖርት አመልክቷ። ድርቁ ከፍተኛ ጉዳት ባስከተለባቸው የአማራ፣ ኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች ...

Read More »