በረሃብ ለተጠቁ ወገኖች ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተጨማሪ ገንዘብ ያስፈልጋል ተባለ

ታኀሳስ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦክስፋም ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ በረሃብ ለተጠቁት ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የውጭ አገር መንግስታትና ድርጅቶች ቃል ከገቡት ተጨማሪ 1 ቢሊዮን 100 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ አፋጣኝ እርዳታ ያስፈልጋል ብሎአል።
እስካሁን ድረስ ቃል የተገባው 300 ሚሊዮን ዶላር ነው ያለው ኦክስፋም፣ አሁን ባለው የተረጅ ቊጥር የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን ግን 1 ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ዶላር ነው ብሎአል።ከ300 ሚሊዮን ዶላር ውስጥም እስካሁን የደረሰው 5 በመቶው ብቻ መሆኑን ገልጿል። ከባድ ቀውስ ማንዣበቡን የገለጸው ድርጅቱ፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ተማጽኗል።