የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ያለው ርሃብ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አሳወቀ

ታኀሳስ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዓለም የምግብ ድርጅት በኢትዮጵያ ያለው የድርቅ ሁኔታ እየከፋ መምጣቱንና ዜጎች አፋጣኝ እርዳታ ካልተደረገላቸው በአገሪቱ የሚደርሰው ሰብዓዊ ቀውስ እጅግ አደገኛ መሆኑን በሪፖርቱ ገልጿል። በኢትዮጵያ በተከሰተው የአየር መዛባት ኤሊኖ ምክንያት ወቅቱን ጠብቆ ዝናብ ባለመዝነቡ በቂ ምርት መሰብሰብ ያልተቻለ ሲሆን እንስሳትም በድርቁ ሰበብ ሞተዋል። ቁጥራቸው ከ10 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ...

Read More »

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለአለም የጤና ድርጅት መሪነት ሊወዳደሩ ነው

ታኀሳስ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ስልጣናቸውን በመልቀቅ ለአለም የጤና ድርጅት መሪነት ሊወዳደሩ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል። ዶ/ር ቴዎድሮስ ሰሞኑን ወደ ጄኔቫ የሚመጡ ሲሆን፣ ለመመረጥ የቅስቀሳ ( ሎቢ) ስራ ይሰራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የድርጅቱ ሰራተኞች ዶ/ር ቴዎድሮስ የንጹሃን ዜጎችን ደም በማፍሰስ የሚወነጀለው የህወሃት/ኢህአዴግ አንዱ ከፍተኛ መሪ በመሆናቸው ኢትዮጵያውያን ተቃውሞዋቸውን ፊርማ በማሰባሰብና ለድርጅቱ ደብዳቤ በመጻፍ እንዲገልጹ ጥሪ ...

Read More »

77 ኢትዮጵያዊያዊያን ስደተኞች በዛንቢያ ተያዙ

ታኀሳስ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዛንቢያ የስደተኞች ጉዳይ ከፓሊስ ጋር በመተባበር በሕገወጥ መንገድ ወደ አገራችን ገብተዋል ያላቸውን ቁጥራቸው 77 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በዋና ከተማዋ ሉሳካ ካባንግዌይ አቅራቢያ በቁጥጥር ስራ ማዋሉን አስታውቋል። በአንድ ቶዮታ ሬጉስ መኪና ላይ ተጭነው ሲጓዙ የነበሩ 10 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ለመያዝ አሰሳ ሲያደርጉ በስፍራው ሌሎች ተጨማሪ 67 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከተደበቁበት መያዛቸውን ገልፀዋል። ከተያዙ ...

Read More »

የአዳማ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በአጋዚ ወታደሮች ግድያ፣ ድብደባና ወከባ ደረሰባቸው

ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2008) በኦሮሚያ እየተካሄደ ያለውን የመሬት ዘረፋና የጅምላ ጭፍጨፋን  በመቃወም ላይ በነበሩ በአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ተቃውሞውን ለማስቆም በተሰማሩ የጸጥታ ሃይላት መካከል ግጭት እንደተፈጠረ የአይን እማኞች ከስፍራው አስታወቁ። ሰኞ ጠዋት የተጀመረው ይህ ተቃውሞ፣ ተማሪዎቹ በአዳማ ዩንቨርስቲ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ በኦሮሚያ ክልልና በሌላው የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ እየደረሰ ያለው ጭፍጨፋና፣ ወከባና፣  እንግልትን እንዲቆም ሲጠይቁ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። አመጹን ለማስቆም ...

Read More »

ኢትዮጵያ ኪስማዩን ለማስለቀቅ ጦሯን ወደሶማሊያ አሰማራች

ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2008) የሶማልያ የወደብ ከተማ የሆንችዉን ኪስማዩ ከሶማሊያዉ ታጣቂ ሀይል አል-ሸባብ ለማስለቀቅ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወታደሮችንና ታንኮችን ወደ ስፍራዉ ማሰማራቷ ተገለጠ። የታጣቂ ሀይሉ ጠንካራ ይዞታ እንደሆነች የሚነገርላትን ኪስማዩ ለማስለቀቅም በአካባቢዉ በማንኛዉም ሰአት ከባድ ዉጊያ ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት መኖሩን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታዉቀዋል። እሑድ ወደ ወደባማ ከተማዋ የገቡት በመቶዎች የሚቆጠሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች በታጣቂ ሀይሉ ቁጥጥር ስር የምትገኘዉን ከተማ ነጻ ለማዉጣት ...

Read More »

በሶማሌ ክልል በሊበን ዞን በሚገኙ ወረዳዎች የዉሃ-ወለድ ተላላፊ ወረርሽኝ ተከሰተ

ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2008) በሶማሊያ ክልል እየተባባሰ የመጣዉን የድርቅ አደጋ ተከትሎ በሊበን ዞን በሚገኙ ወረዳዎች የዉሃ ወለድ ተላላፊ በሽታዎች ወረርሽኝ መከሰቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኞ አስታወቀ። በሽታዉን ለመቆጣጠርም የተለያዩ የጤና ተቋማት ርብርብን እያደረጉ እንደሚገኙና ወረርሽኙ ወደ ተጎራባች ዞኖች ለመዛመት ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ድርጅቱ ገለጿል። ባለፈዉ ወር ተመሳሳይ ወረርሽኝ በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ አካባቢ ተቀስቅሶ የነበር ሲሆን፣ በጤና ድርጅቶች በተደረገ ...

Read More »

የኖርዌይ ኤምባሲ ዜጎቹ በኦሮሚያ ሲንቀሳቀሱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ

ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃዉሞ ጋር በተገናኘ መቀመጫዉን በኢትዮጵያ ያደረገዉ የኖርዌይ ኤምባሲ፣ ዜጎቹ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ከተሞች በሚያደረጉት እንቀሰቃሴ ላይ ጥንቃቄን እንዲያደርጉ ሰኞ በድጋሚ አሳስቧል። ተቃውሞው ከቅርብ ጊዜ ተቃውሞ ረገብ ያል ቢመስልም በማንኛውም ሰአት በድጋሚ ሊከሰትና የደህንነት ስጋት ሊያጋጥም ይችላል ሲል ኤምባሲዉ ገለጿል። በዚሁ ክልል አሁንም ድረስ አለመረጋጋት መኖሩን የገለጸዉ ኤምባሲዉ ዜጎቹ ሊያደርጓቸዉ ያሰቧቸዉን ጉዞዎች ...

Read More »

በኢትዮጵያ የምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ማሻቀቡን የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ

ኢሳት (ታህሳስ 26 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለዉን የድርቅ አደጋ ተከትሎ የሀገሪቱ የምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጦች የዋጋ ግሽበት ከ11.5 በመቶ ወደ 12.1 በመቶ ማሻቀቡን የማእከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሰኞ አስታወቀ። ወተትና ፓስታን ጨምሮ በተለያዩ የምግብ ዉጤቶች ላይ በየእለቱ የዋጋ ጭማሪ እየተመዘገበ መምጣቱንም መንግስታዊ ተቋሙ በወርሃዊ ሪፖርቱ አመልክቷል። በተለይ በስድስት ክልሎች ጉዳትን እያደረሰ የሚገኘዉ የድርቅ አደጋ በሀገሪቱ የምግብ ነክ ሸቀጣሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በማድረግ ...

Read More »

በኦሮሚያ የመለስ ፓርኮችና የአደባባይ ፎቶግራፎች ተቃጠሉ

ኢሳት (ታህሳስ 25 ፣ 2008) በኦሮሚያ ክልል ከማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ የተነሳው ተቃውሞ ሰሞኑን እንደገና አገርሽቶ በተለይም በምስራቁ የአገራችን ክፍል ከፍተኛ አለመረጋጋት መከሰቱን ከስፍራው የሚወጡ ዘገባዎች አመለከቱ። በምዕራብ ሃረርጌ ዞን ሂርና ከተማ እና በምስራቅ ሃረርጌ ዞን በደኖ ወረዳዎች በህወሃት/ኢህአዴግ ታጣቂዎችና በነዋሪው ህዝብ መካከል ከፍተኛ ግጭትና ፍጥጫ እንደነበር የአይን እማኞች ከስፍራው ለኢሳት ተናግረዋል። በበደኖና በሂርና አርብ የጀመረው ተቃውሞው እስከዛሬ ሰኞ ድረስ ...

Read More »

በጋምቤላ ክልል 9 የልዩ ሃይል አባላት ከእነሙሉ ትጥቃቸው ሸማቂ ቡድንኑ መቀላቀላቸው ተሰማ

ኢሳት (ታህሳስ 25 ፥ 2007) የጋምቤላ ልዩ ሃይል አባላት ከእነሙሉ ትጥቃቸው የህወሃትን መንግስት በመክዳት ተቃዋሚዎችን መቀላቀላቸው ከአገር ቤት የደረሰን ዜና አመለከተ። የልዩ ሃይል አባላቱ የታጠቁትን የጦር መሳሪያ በመያዝ የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ጥምረት ግንባር የተባለው ሸማቂ ቡድን መቀላቀላቸውየኢሳት ምንጮች ከአገር ቤት ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ብዛት ያላቸው የስርዓቱ መከላከያ ሃይል አባላት ስርዓቱን እየከዱ ሸማቂ ቡድኑን እየተቀላቀሉ ናቸው ተብሏል። የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ጥምረት ...

Read More »