(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 21/2011)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በብሔር ሳንከፋፈልና አንድ ሆነን በመስራት ሃገራችንን እናበልጽግ ሲሉ ጥሪ አቅርቡ። በጀርመን ፍራንክፈርት ከኢትዮጵያውያን ጋር በስታዲየም ውስጥ የታደሙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በርትተን በመስራት የበለጸገችውን የነገን ኢትዮጵያን መገንባታችን አይቀርም ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል። ለዚሁም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ብቁ ሰዎችን በመመደብ የፍትህና የዲሞክራሲ ተቋማትን የማሻሻል ርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ተሰባስበው ...
Read More »መንግስት በሃገሪቱ ለሚከሰቱ ግጭቶችና ችግሮች መፍትሄ መስጠት አለበት ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 21/2011) የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት በሃገሪቱ አንዳንድ ክፍሎች ለሚከሰቱ ግጭቶችና ችግሮች መፍትሄ መስጠት አለበት ሲል አሳሰበ። ሲኖዶሱ ከጥቅት 11 እስከ 21/2011 ሲያካሄድ የነበረውን መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቋል። ሲኖዶሱ ከጉባኤው መጠናቀቅ በኋላ በሰጠው መግለጫ እንደ ሃገር የሚታዩ ችግሮች እየተባባሱ የሚሄዱ ከሆነ ችግሮቹ ከዚህም በላይ ሊባባሱ ይችላሉ ብሏል። ይህን ችግር ለመቅረፍ ቤተክርስቲያኗ የበኩሏን ጥረት እንደምታደርግና ...
Read More »የቴፒና አካባቢው ነዋሪዎች ድብደባና እንግልት እየበዛብን ነው አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 21/2011)የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ድብደባና እንግልት እየፈጸመብን ነው ሲሉ የቴፒና አካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። በአካባቢው የሸካና ማጃንግ ብሔረሰብ አባላት የማንነት ጥያቄያችን ይፈታ በሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ግጭት ተፈጥሯል። በዞኑና በአካባቢው ያሉ አመራሮች ወጣቶችን ከጀርባችሁ ሌላ ሃይል አለ በማለት በልዩ ሃይል እያስደበደቧቸው መሆናቸው ታውቋል። በግጭቱ አንድ ሚስጥሩ ሲሳይ የተባለ ወጣት በጥይት መቁሰሉም ታውቋል። በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ...
Read More »መንግስት አደጋ ላይ የሚጥሉ እንቅስቃሴዎችን አይታገስም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 20/2011)መንግስት የሕዝቡን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ እንቅስቃሴዎችን እንደማይታገስ አቶ ለማ መገርሳ አስጠነቀቁ። በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በምዕራብ ኦሮሚያ ዞንና በቄለም ወለጋ በኦነግ ስም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት በአፋጣኝ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ መንግስት በሕዝባችን ላይ ከፍተኛ የሰራዊት ሃይል በማሰማራት ግድያና ዘረፋ እየፈጸመ ነው ሲል ከሷል። ...
Read More »በበሁሌ ሆራ በመከላከያና ኦነግ መካከል የተኩስ ለውውጥ ተካሂዷል የተባለው ስህተት ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጹ
በበሁሌ ሆራ በመከላከያና ኦነግ መካከል የተኩስ ለውውጥ ተካሂዷል የተባለው ስህተት ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጹ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ/ም ) ነዋሪዎች እንደገለጹት ባለፈው አርብ ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓም ወጣቶች ከቡሌ ሆራ ወደ ሞያሌ፣ ከቡሌሆራ ወደ አዲስ አበባና ወደ ሻኪሶ የሚወስዱ መንገዶችን የዘጉ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው በመሄድ የሞያሌን መንገድ አስከፍተዋል። መንገድ አስከፍተው ሲመለሱ የነበሩ ...
Read More »በሃረር ለረጅም ጊዜ ሲያገለግል የነበረው ቄራ ተዘጋ
በሃረር ለረጅም ጊዜ ሲያገለግል የነበረው ቄራ ተዘጋ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ/ም ) በከተማው ቀበሌ 8 የሚገኘው ቄራ በመዘጋቱ እርድ መቆሙን የከተማ ነዋሪዎች ገልጸዋል። አንዳንድ ነዋሪዎች ቄሮዎች እንዳዘጉት የገለጹ ሲሆን፣ የቀበሌ 8 የቄሮ ተወካይ ወጣት ሚስባህ ግን ቄሮ ቄራው እንዲዘጋ አለመስደረጉንና የወረዳው መዘጋጃ ከጤና ጋር በተያያዘ መዝጋቱን ገልጿል። የሸንኮር ወረዳ አስተዳደሪ አቶ አብዱረህማን አሰፋም እንዲሁ ቄራው የተዘጋው ...
Read More »በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በምስራቅ ጉጂ የኦነግ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት እርምጃ በመወሰድ ላይ ነው።
በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በምስራቅ ጉጂ የኦነግ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት እርምጃ በመወሰድ ላይ ነው። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ካለፈው አርብ ጀምሮ በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ላይ የመንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ በብዙ ታጣቂዎች ላይ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደርሷል። የኦነግ ወታደሮችን ትጥቅ መፍታት የተቃወሙ ወጣቶች በየአካባቢው የተቃውሞ ሰልፎችን ሲያደርጉ ሰንብተዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ...
Read More »ከአማሮ ወረዳ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ጉማይዴ ገቡ
ከአማሮ ወረዳ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ጉማይዴ ገቡ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከአማሮ ወረዳ ቡኒቲ ቀበሌ የተፈናቀሉ በርካታ የአማራ ተወላጆች በሰገን ዞን ዋና ከተማ ጉማይዴ ላይ መስፈራቸውን ወኪላችን ገልጿል። ነዋሪዎች እንደሚሉት በጉማይዴ ከተማ ጳጉሜ 2 ቀን 2010 ዓም በነበረው ሰልፍ ላይ የአማራ ተወላጆች ሰልፍ ሲወጡ የኮይሬ ተወላጆች ሰልፍ ባለመውጣታቸው የተጀመረው ጸብ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓም ...
Read More »በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተደረጉ
በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተደረጉ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ) የራያ እና ወልቃይት የማንነት ጥያቄ እንዲከበር፣ በጣና ሐይቅንና የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስያናትን እንታደግ በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ትዕይንተ ህዝብ ተደረገ። ካለ ህዝብ ውሳኔ ወደ ትግራይ ክልል የተካለሉት ወልቃይቶችና ራያዎች ማንነታቸው እንዲከበር፣ ሰብዓዊ መብታቸውን የሚጥሱ የትግራይ ክልል ልዩ ጦር አባላት አካባቢውን ለቀው ...
Read More »ኮለኔል ጎሹ ወልዴ ኢትዮጵያ ገቡ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011) በቀድሞ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኮለኔል ጎሹ ወልዴ ኢትዮጵያ ገቡ። ከ30 አመታት በላይ በስደት የቆዩት ኮለኔል ጎሹ ወልዴ የደርግን ስርአት በመክዳት እንዲሁም የሕወሃት/ኢሕአዴግን መንግስት በመቃወም ላለፉት 30 አመታት ያህል በአሜሪካን ሃገር በጥገኝነት ቆይተዋል። የደርግን ስርአት በመቃወም ለስራ ከሃገር እንደወጡ በዚያው የቀሩት ኮለኔል ጎሹ ወልዴ የሕወሃት ኢሕአዴግ መንግስት ወደ ስልጣን ሲወጣ ስርአቱ ኢትዮጵያን እያዳከመና እያፈረሰ ነው በማለት ...
Read More »