የኢትዮጵያና የኤርትራ ወዳጅነት የውጭ ሃይሎችን ምኞት ያመከነ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 26/2011) በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተፈጠረው ሰላምና የተከተለው ወዳጅነት የውጭ ሃይሎች ቀጠናውን ለመቆጣጠር የነበራቸውን ምኞት ያመከነ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ገለጹ። በሌላም በኩል በኤርትራ ላይ ለአመታት ተጭኖ የነበረውን ማዕቀብ ለማንሳት እንቅስቃሴ መጀመሩም ተመልክቷል። የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቄ በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ ጥቅምት 24/2011 ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ከኢትዮጵያ ጋር የተደርገው የሰላም ስምምነት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ለቀጠናው ...

Read More »

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ አሁንም አንዲት ኢትዮጵያ መቀጠል ይገባታል አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 23/2011) ኢትዮጵያ ታላቅ መሪዎች የነበሯት፣ በአለም ላይ የታወቀች ሃገር ስለሆነች አሁንም አንዲት ኢትዮጵያ መቀጠል ይገባታል ሲሉ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ጥሪ አቀረቡ። እውቁ ፖለቲከኛና የንግድ ሰው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በኢትዮጵያ በተከሰተው ለውጥ መርካታቸውን የገለጹ ሲሆን በእድሜዬ መጨረሻ ይህንን በማየቴም ደስተኛ ነኝ ብለዋል። በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት በሚኒስትርነት እንዲሁም በአለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ በመሆን ያገለገሉት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተባበሩት መንግስታት ...

Read More »

የሲዳማ ዞን የክልላዊ መንግስት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 23/2011) የሲዳማ ዞን የክልል መንግስት እንዲሆን የቀረበውን ጥያቄ የደቡብ ክልላዊ መንግስት በመቀበል በሁለት ሶስተኛ ድምጽ ማጽደቁ ተነገረ። የደቡብ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው ጉባኤ ሲዳማ በሕገመንግስቱ መሰረት ያቀረበው ጥያቄ ሕጋዊ በመሆኑ ክልላዊ የመሆን መብቱ እንዲረጋገጥ ወስኗል። የሲዳማ ዞን ምክር ቤት ወደ ክልል መንግስትነት ለማደግ በሙሉ ድምጽ ይታወሳል። የደቡብ ክልል ምክር ቤት የሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ ህገ መንግስታዊ ...

Read More »

በሶማሌ ክልል ለመፍጠር የታቀደው ቀውስ ከሸፈ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 23/2011) በጄነራል አብረሃም ወልደማርያም ኳርተርና በጄነራል ገብሬ ዲላ የታቀደው ቀውስ መክሸፉን የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ገለጹ። ፕሬዝዳንቱ አቶ ሙስጠፋ ዑመር ለኢሳት እንደገለጹት በህወሀት ጄነራሎች የሚመራው የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች ኔትወርክ የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተደርሶበታል። ሰሞኑን በእነዚሁ የህውሀት ጄነራሎች አስተባባሪነት በተፈጠረ ቀውስ  የሁለት ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ለማወቅ ተችሏል። በጄነራል አብረሃምና ጀነራል ገብሬ የሚመራው ኔትወርክ ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎችን ...

Read More »

ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ድብደባ ሊፈጽሙ ነበር ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 22/2011)የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ድብደባ ለመፈጸም ሙከራ በማድረጋቸው በህግ ሊጠየቁ ነው ተባለ። ዶክተር አሸብር የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሁለት አባላትን በስብሰባ ላይ ለመደብደብ መሞከራቸው ተገልጿል። በዶክተር አሸብር የድብደባ ሙከራ ከተደረገባቸው አንዷ ኮለኔል ደራርቱ ቱሉ መሆኗም ታውቋል። ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሊያመራ መሆኑን የገለጹት ምንጮች በዶክተር አሸብር በኩል የሽምግልና ጥያቄ መቅረቡን ጠቅሰዋል። ኢሳት ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ...

Read More »

በጋምቤላ የቦምብ ጥቃት ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 22/2011)በጋምቤላ የቦምብ ጥቃት ደረሰ። በአንድ የክልሉ ባለስልጣን ጠባቂ ፖሊስ ትላንት የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የሁለት ሰዎችን ህይወት ማጥፋቱ ተገልጿል። አዲሱ የጋምቤላ አመራር ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ ያኮረፉ ሃይሎች የሽብር ተግባር ሊፈጽሙ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳለም ታውቋል። ቦምቡን ያፈነዳው ግለሰብ የህወሃት አባል እንደሆነም የኢሳት ምንጮች ያደረሱን መረጃ አመልክቷል። ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ በተደረገው የጋምቤላ ገዢ ፓርቲ ግምገማ የክልሉ ፕሬዝዳንትና ምክትላቸው ...

Read More »

ወደ ሃገር ቤት የተመለሱ ታጣቂዎችን ለማቋቋም የጀርመን መንግስት ቃል ገባ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 22/2011)በትጥቅ ትግል ላይ ቆይተው በመንግስት ጥሪ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ወስነው ወደ ሃገር ቤት የተመለሱ ታጣቂዎችን ለማቋቋም የጀርመን መንግስት የልማትና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱ ተገለጸ። በአጠቃላይ ትጥቅ ፈተው ወደ ሃገር ቤት የተመለሱ ታጣቂዎች ቁጥር 35ሺ ያህል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከተመራው የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን ጋር በፈረንሳይና በጀርመን ቆይተው ሲመለሱ መግለጫ የሰጡት ...

Read More »

ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 22/2011)ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ። የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርን በመመስረትና በመምራት ለረጅም አመታት ያገለገሉት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ እንስት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነዋል። አቶ ሰለሞን አረዳ ደግሞ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው በዛሬው እለት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የወሰዱት ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ በአሜሪካ ኬንታኪ ...

Read More »

አለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ሰጠ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 21/2011) አለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ድጋፍና ብድር አጸደቀ። ከገንዘቡ መካከል 6 መቶ ሚሊየኑ ብድር ሆኖ ቀሪው ደግሞ እርዳታ መሆኑ ተነግሯል። ድጋፉና ብድሩ የጸደቀው የባንኩ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ባካሄደው ስብሰባ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። የአለም ባንክ እንዳስታወቀው ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ድጋፍና ብድር አጽድቋል። ከዚሁም ውስጥ 6መቶ ሚሊየን ዶላሩ ድጋፍ ሲሆን፥ ቀሪው ግማሹ 600 ...

Read More »

አዲስ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሊሾም

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 21/2011) የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ተነስተው በምትካቸው አዲስ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እንደሚሾም ተገለጸ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እንዳስታወቀው ፓርላማው በነገ ውሎው አዲስ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ይሾማል። በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን የሚያገለግሉት አቶ ዳኜ መላኩ በፖለቲካ አመለካከታቸው በተከሰሱ ንጹሃን ላይ በሕግ ስም የፖለቲካ ውሳኔ ሲያሳልፉ የቆዩና ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባቸው ዳኛ መሆናቸውንም ...

Read More »