በበሁሌ ሆራ በመከላከያና ኦነግ መካከል የተኩስ ለውውጥ ተካሂዷል የተባለው ስህተት ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጹ

በበሁሌ ሆራ በመከላከያና ኦነግ መካከል የተኩስ ለውውጥ ተካሂዷል የተባለው ስህተት ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጹ
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ/ም ) ነዋሪዎች እንደገለጹት ባለፈው አርብ ጥቅምት 16 ቀን 2011 ዓም ወጣቶች ከቡሌ ሆራ ወደ ሞያሌ፣ ከቡሌሆራ ወደ አዲስ አበባና ወደ ሻኪሶ የሚወስዱ መንገዶችን የዘጉ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው በመሄድ የሞያሌን መንገድ አስከፍተዋል። መንገድ አስከፍተው ሲመለሱ የነበሩ የክልሉ ፖሊሶች በድንገት በተከፈተባቸው ጥቃት 3 ፖሊሶች ወዲያውኑ ሲሞቱ፣ 7 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። መኪናዋም ተመትታ ወድቃለች። በማግስቱ በዱጋ ዳዋ ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎችን ለማደን መጠነኛ ተኩስ የነበረ ቢሆንም፣ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጉዳት አለመድረሱን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ኢሳት ትናንት ከመከላከያና ከኦነግ ታጣቂዎች የሞቱ መኖራቸውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ጠይቆ ዘገባ አቅርቦ ነበር። የክልሉ ም/ል የጸጥታ ሃላፊ ኮ/ል አበበ ገረሱ፣ በተባለው አካባቢው ከመከላከያ ጋር የተደረገ ጦርነት እንዳልነበረ መግለጻቸው ይታወሳል።